Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @assebpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 25

2022-08-05 20:15:21 #ሰብአዊ እርዳታ በጫነ ከባድ ተሽከርካሪ ሲዘዋወር የነበረ ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ተያዘ

#ሰብአዊ እርዳታ በጫነ ከባድ ተሽከርካሪ በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መያዙን በአፋር ክልል በጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ቅርጫፍ ሰርዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስታወቀ።

#የመቆጣጠሪያ ጣቢያው አስተባባሪ ኮማንደር አህመድ ሳልህ ለኢዜአ እንደገለጹት የእርዳታ እህል ሲጭኑ የነበሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከዚህ በፊት ነዳጅና ጨውን ጨምሮ የተለያዩ ህገወጥ እቃዎችን ለማሳለፍ ይሞክሩ ነበር።

ይህን ድርጊታቸው በፍተሻ ጣቢያው ሰራተኞች ጥብቅ ቁጥጥር ሲከሽፍ ፊታቸውን ወደ ህገወጥ ብርና ልዩልዩ ጌጣጌጦችን የማዘዋወር ስራ መግባታቸውን አብራርተዋል።

የመቆጣጠሪያ ጣቢያው ሰራተኞችና አመራሮች እየተለዋወጠ የመጣውን ህገወጥ ዝውውር ለመቆጣጠር በፈጠሩት መናበብ ተጨባጭ ውጤት እየታየ ለመሆኑ ሰሞኑ በጣቢያው የተያዙት ህገ ወጥ ብሮች በቂ ማሳያ ናቸው ብለዋል።

ዛሬም ከአዲስ አበበ ሰብአዊ እርዳታ ጭነው ይጓዙ የነበር ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ ከ7 ሚሊዮን 900ሺ ብር በላይ በፍተሻ መያዙን ገልጸዋል።

ከዚህም ውስጥ የመጀመሪያው 2 ሚሊዮን 85ሺ 200 ብር ዛሬ ጧት ሁለት ሰአት ኮድ3-64879 ኢ/ት ተሳቢ 25350 በሆነ ከባድ መኪና ላይ በጣቢያው ፈታሾች ገንዘቡ መያዙን አብራርተዋል።

በተጨማሪም ኮድ3-12806 ኢ/ት ተሳቢ 06037 በሆን ተሽከርካሪ ከጧቱ 4 ሰአት በጣቢያው ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ 5ሚሊዮን 815ሺ 400 ብር መያዙን ተናግረዋል።

ዛሬ የተያዘውን ጨምሮ በመቆጣጠሪያ ጣቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ሰብአዊ እርዳታ በጫኑ መኪኖች ላይ በተደረገ ፍተሻ መያዙን አስታውቀዋል።

አሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዉ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኘም የጣቢያ አስተባባሪ ተናግረዋል።


የምሰል መረጃዎች ለመከታተል follow በመደረግ ቤተሰብ ይሁኑ tiktok.com/@assebpress
150 viewsHusen Mohammed, 17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 20:03:02 https://vm.tiktok.com/ZMNbq61mK/?k=1
120 viewsHusen Mohammed, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:47:36
ዘመድኩን በቀለ ማታ አቢቹን በቴሌቪዥን መስኮት አይቶ እንዲህ ሆኖ ቀረ
246 viewsHusen Mohammed, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:37:30
አፋር
''በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ጥሬ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ''
በዛሬው እለት ሠርዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ የሠብአዊ እርዳታ ጭኖ ወደ መቀሌ በመጓጓዝ ላይ በነበረ ኮድ 3- 10298/23634 ኢት ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ የጥሬ ገንዘብ መጠን ብር 2,280,640.00/ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ ሽህ ስድስት መቶ አርባ ብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ገንዘብ በተሸከርካሪው ጋቢና ውስጥ ሆን ተብሎ በተሰራ ስውር ቦታ/ሻግ ውስጥ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
======================
የትኛውንም ሀገርዓቀፍ እና ዓለምዐቀፍ ፈጣን እና እውነተኛ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቻናላችን ቤተሰብ ብትሆኑ ይመረጣል፣ ትክክለኛ የቻናላችን ሊንክ ይሄ ነው የቴሌራምhttps://t.me/AssebPress

የቲክቶክ live ደግሞ ይቀላቀሉ መረጃዎች ያገኛሉ tiktok.com/@assebpress
261 viewsHusen Mohammed, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 04:04:10
አብይ ተቀጭቷል ለቀብር ተዘጋጅ እያለ ነው አዲሱ ተንታኝ

የአዲስ አበባ ሕዝብንም ደግሞ ከቀብር በኃላ ለሽግግር መንግስት እራሳችሁን አዘጋጁ
የትግራ መንግስት ደግሞ ከአብይ ተማሩ እሱም ከንቱ ሆኗል

#ColorsOfUnity
282 viewsHusen Mohammed, 01:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 03:53:39
የከንቲባ ፅ/ቤት የፀጥታ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን ሲያካሂዱ በቆዩት የክትትል ስራ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ወንጀለኞችንና አሸባሪዎችን ለማስገባት እና በህገወጥ መንገድ ወንጀለኞችን ከሃገር ለማስወጣት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ ሲደረግ በቆየው ክትትል በቁጥጥር ስር በዋሉት ገለሰቦች መኖርያ ይህንን ተግባራቸውን ለማሳካት የተለያዩ የፎርጅድ መታወቂያዎችን በመስራት ፤ የፌደራል መመንግስት ሰነዶችና ማህተሞችን በማዘጋጀት ፤ የጉዞ ሰነዶችን ማዘጋጀት እንዲሁም ዶላሮችን በእጃቸው ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 6 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ፀጋዬ ካሳ ፤ እስክንድር መላኩ፤ ሰይድ አሊ፤ ገሸና ገልገሉ፤ እድሪስ አደም፤ አቡበከር አህመድ የሚባሉ ናቸው፡፡
በግለሰቦቹ መኖርያ ቤት በተደረገ ምርመራ በግለሰቦቹ እጅ የተገኙ ነገሮች ዝርዝር
• 2200 የአሜሪካን ዶላር
• የተለያዩ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የነዋሪዎች መታዎቂያ
• ከአማራ ክልል እንደተላከ በማስመሰል የሚሰሩ መሸኛ
• በጅምር ስራ ያላለቀ የአዲስ አበባ መታወቂያ
• ለተለያዩ ህገወጥ ህትመት መስሪያ የህትመት መሳሪያና ቀለሞች
• የአዲስ አበባ COC ምዘና ማዕከል ሰነድ...
• የተለያዩ ፖስፖርቶች
• ሀሰተኛ የልደት ሰርተፊኬት
• የተለያየ ከለር ያላቸው ለህገወጥ ህትመት የሚጠቀሙበት ብዛት ያለው ወረቀቶች ..
• የተለያዩ የሀሰት የጉዞ ሰነድ
• የተለያዩ የግል ተቋማት ሀሰተኛ ማዕተም ያለበት ደብዳቤ ተገኝተዋል፡፡
ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጨማሪ የምርመራ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
281 viewsHusen Mohammed, 00:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ