2022-11-25 19:05:13
በጉራጌ ዞን ኮማንድ ፖስት የተከለከሉ ተግባራት እና የሚወሰዱ እርምጃዎች ምንድናቸው?
የደቡብ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ትላንት ሐሙስ በሰጡት መግለጫ ካነሷቸው ነጥቦች ውስጥ የተወሰዱ፦
“የትኛውም ቦታ ላይ፣ የትኛውም ኪስ ቦታ ላይ፣ የትኛውም መንደር ላይ፣ የትኛውም አዳራሽ ውስጥ ያልተፈቀዱ ስብሰባዎች ማድረግ፣ እንቅስቃሴዎች ማድረግ በፍጹም የማይፈቀድ ነው የሚሆነው።”
“አሁን እንደሚታወቀው አጥፊው ቡድን ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራል። ሲፈልግ ይከለክላል። ሲፈልግ ‘አቁሜያለሁ’ ይላል። ሲፈልግ ‘ቀን ቀይሬያለሁ’ እያለ በተለያየ መንገድ ህዝቡን እያወናበደ ነው ያለው። በዚህ መንገድ የመንግስት ተቋማት እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት አመራሮች ካልሆኑ በስተቀር፤ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚጠሩ ስብሰባዎች፣ ህዝባዊ ሰልፎች ካልሆኑ በስተቀር፣ በየትኛውም መንገድ በህገ ወጥ መንገድ በተከፈቱ (ፌክ) አካውንቶች የሚተላለፉ መልዕክቶች እና ጥሪዎች ተቀባይነት የላቸውም።”
“ከዚህ በኋላ ለጥፋት የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች፣ በህግ ያልተፈቀደላቸውን እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት፣ ኃላፊነት ከተሰጣቸው የመንግስት አመራሮች ውጪ ህጋዊ ባልሆነ በየትኛውም መንገድ የትኛውንም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ላይ የጸጥታ ኃይሎች ሁሉንም አይነት የህግ እርምጃ ይወስዳሉ።”
“እዚህ ሀገር ህግ ስላለ፣ ህግ ደግሞ ለሁሉም እኩል ስለሆነ፤ አጥፊ ድርጊት የፈጸመ ላይ በሙሉ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።”
“ህዝቡ ያነሳው ነባራዊ ሁኔታ እና በመሬት ላይ እየሆነ ያለው ጉዳይ የማይገናኙ እና ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶች ስለሆኑ በተደራጀ መንገድ ጥፋት ውስጥ ተቀላቅለው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ይውላሉ።”
“የጥፋት ይዘቱን ያቀደ፣ የመራ፣ ያስተባበረ፣ አጥፊ ድርጊት የፈጸመ፤ በግለሰብም፣ በቡድን ደረጃም እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች በደንብ በተደራጀ መንገድ ተለይተዋል። እነዚህን ኃይሎች በሙሉ ጸጥታ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ያውላል።”
[ በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተጠናቀረ]
509 viewsHusen Mohammed, 16:05