Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @assebpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-08 18:45:00 ዘመንና ጊዜ እየተቀየረ ሲሄድ የኅብረተሰብ አኗኗር፣ ፍላጎት፣ የመብት ጥያቄ ወዘተ አብሮ እየተለወጠ ይሄዳል። ሕዝብ አይናቅም። ሕዝብ የአሥተዳደርም ሆነ የአካታችነት ጥያቄ ሲያነሳ ወደ ጎን መግፋት መዘዙ ብዙ ነው።
525 viewsHusen Mohammed, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 14:56:37 ሆሳዕና

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን ለመመስረት የሀድያ ፣ሀላባ ፣ከምባታ ፣ጠምባሮ ፣ቀቤና ፣ማረቆ ፣ጉራጌ ፣ዶንጋ ፣ወለኔ ፣ስልጤ ፣የም ብሔረሰቦች በጋራ ድምፀ ውሳኔ ሰጥተው የክልልነትን እውቅና አገኝተዋል።የክልል ምክር ቤቱ የተመሰረተው በሆሳዕና ከተማ ዛሬ ነው።
ፈጣን ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት ይህንን የቴሌግራም ቻናል Join በማለት ይከታተሉ

https://t.me/AssebPress
367 viewsHusen Mohammed, 11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 15:47:01
አጭር የአገልግሎት ታሪክ!
ከ Maryamawit Henok Lemessa
እኚህ ሰው Ex አባ ሳዊሮስ በቀድሞ ስማቸው #ደምመላሽ #ሞገስ በምንኩስና ስማቸው አካለወልድ ሞገስ ቤተክርስቲያን ኦሮሚኛ የምችሉ መነኮሳት ጵጵስና ይሰጣቸው ብላ በ1997 ጵጵስና ሾማቸው ነበር።

ላለፉት 18 ዓመታት ኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ተመድበው ነበር። ተጨማሪ ሌሎች 4 በውጪ ያሉ ሀገረ ስብከቶችን ደርበው ያስተዳድሩ ነበር። ነገር ግን በዚህ በ18 ዓመት ሀገረ ስብከት የማስተዳደር እድሚያቸው አንድም የAfaan Oromoo አብነት ትምህርት ቤት አልከፈቱም። አንድም የAfaan oromoo የካህናት ማስልጠኛ አልከፈቱም። አንድም በAfaan oromoo መጻህፍ አልጻፉም። አንድም ቀን በAfaan oromoo ቀድሰው አያውቁም።
የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከትን እንዲያስተዳድሩ ሲጠየቁ ''ልታስገድሉኝ ነው ወይ? እዛ መሄድ አልፈልግም'' ብለው የቀሩ ሰው ናቸው።

እኚህ ሰውዬ ውሏቸውም አዳራቸውም 4ኪሎ ባለው መኖሪያ ቤታቸው ነበር። በዚህ 18 ያህል የጵጵስና ዘመናቸው አንድ የAfaan oromoo መጽሃፍ ያልጻፉ ሰውዬ የቋንቋን ችግር እነሰደክፍተት ተጠቅመወሸ እና ከብልጽግና መንግስትና ከፕሮቴስታንት ሀሰተኛ ነብያት ጋር መክረወሰ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የመክፈል፣ መፈንቅለ ፓትርያርክ የማድረግና ስልጣን የመያዝ እንጂ አንድም ለህዝቡ የማዘንና በቋንቋ የማስተማር ዓላማ የላቸውም።
537 viewsHusen Mohammed, 12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 12:21:29
መረጃ፦ሻሸመኔ የጳጳሳቱ አቀባበል በሰላም ሲጠናቀቅ ቡልቡላ መድኃኒያለም ቤ/ክቲያ በውጪ በኩል እሳት ተነስቷል....የነባሻ ሥራ ሳይሆን አይቀርም !!!
571 viewsHusen Mohammed, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 19:37:54
ሰበር ዜና

የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኙ !!

የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በሐላላ ኬላ ተገናኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አድርገዋል።

በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ግንኙነት ያደረጉት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሐላላ ኬላ ነው።
654 viewsHusen Mohammed, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 18:02:15 #ሰበር_ዜና #Breaking_News
የ2014 የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱበ 980 ሺሕ ተማሪዎች ውስጥ፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያገኙ ተማሪዎች 28 ሺሕ ብቻ መሆናቸውን አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ ለተጨማሪ ንባብ https://t.me/AssebPress
651 viewsHusen Mohammed, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 17:46:44 #ሰበር_ዜና #Breaking_News
ከ2014 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት (ከ50% በላይ) ያመጡት ሦስት በመቶ ብቻ ናቸው

ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኩረጃን ለማስቀረትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚል፣ በልዩ ሁኔታ ከተሰጠው የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል ውጤታቸው ከ50 በመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከ28 ሺሕ እንደማይበልጥ አዲስ ማለዳ ከአስተማማኝ ምንጮቿ ሰማች፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲ በተሰጠው ፈተና ከ980 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፣ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባውን ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 28 ሺሕ ገደማ መሆናቸው አዲስ ማለዳ ከትምህርት ሚኒስቴር ምንጮቿ ሰምታለች፡፡

ከፍተኛ ጥያቄ የሚነሳበትን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል እና የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ላይ የሚስተዋለውን ኩረጃ ለማስቀረት ወሳኝ ነው የተባለለት ፈተና በጥብቅ ቁጥጠር ከ50 በሚበልጡ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

የፈተና ውጤቱ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ በበይነመረብ ይፋ እንደሚደረግ፣ ተማሪዎችም በተሰጣቸው የመለያ ቁጥር ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የአዲስ ማለዳ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ በውጤቱ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር በነገው ዕለት መግለጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል፡፡

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር፣ ዩኒቨርስቲዎች ካላቸው የመቀበል አቅም ጋር በፍፁም እንደማይጣጣም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 130 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳላቸው የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው የቅበላ አቅም የ2014 ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡት ከዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበል አቅም ከ20 በመቶ የማይበልጥ ነው ማለት ነው፡፡

ከፍተኛ የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ማጋጠሙን የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሰሙ ሲሆን፣ ያጋጠመውን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ምን ይደረግ በሚለው ላይ ምክክር እየተደረገበት ነው፡፡ በውይይቱ የዩኒቨርስቲዎች መቀበል የሚችሉት አቅም ጋር የሚጣጣም ተማሪ፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ሊገባ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑንን ተከትሎ፣ ዩኒቨርስቲዎች በመቀበል አቅማቸው ልክ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ አማራጭ እየተፈለገ ነው፡፡ በዚህም በልዩ ሁኔታ ለማለፊያ የቀረበ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት ወስደው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረግ የሚለው አንዱ አማራጭ ሆኖ በመንግሥት በኩል እየታየ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲያውቁት የተደረገ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡

የ2014 የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ፣ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያለውን ስብራት ለማከም እንደ አንድ የመፍትሔ አቅጣጫ ተወስዷል፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግበራዊ የተደረገው የፈተና ስርዓት፣ በዩኒቨርስቲ መምሀራን አማካኝነት፣ ተማሪዎችም ከተማሩበት አካባቢ ርቀው በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢዎች ውስጥ የተሰጠ ነበር፡፡ ትኩስ መረጃ ለመከታተል ይቀላቀሉ https://t.me/AssebPress
655 viewsHusen Mohammed, edited  14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 00:16:46 ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ሊያወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ ምሁራን ጋር ነገ ውይይት ያደርጋሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ከምሁራን ጋር የሚያደርጉት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ነው ተብሏል።
865 viewsHusen Mohammed, 21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 15:58:50
ሰንበቴ

ሼር ያድርጉ
በአማራ ክልል ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ግጭት ተከስቷል!!

ከትላንት በስተያ ጀዉሀ አካባቢ የተጀመረው ግጭት አፋጣኝ ምላሽ ባለማገኘቱ  ዛሬ ተስፋፍቶ  ወሰን ቁርቁር፣ ባልጬ፣ በጤ እና አሁን ደግሞ ሰንበቴ ከተማን ያካተተ የተኩስ ልውውጥ እንደሚሰማ በስፍራዉ ያሉ ነዋሪዎች እጅግ በተሸበረ መንፈስ እየተናገሩ ነው።
በዚህ  ግጭት በርካታ  ሰው ተጎጂ ሆኖል ተብሏል። ከፀጥታ ሀይሉም የተጎዱ አባላት እንዳሉ ገልፀውልኛል።

የሚመለከተው የመንግስት አካላትና መረጋጋትን ማምጣት የሚችሉ ወገኖች ሁሉ በአስቸኳይ ደርሰው መታደግ ካልቻሉ ችግሩ ሊባባስና አስከፊ ጥፋት ማስከተሉ ስለማይቀር ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።


ሼር ሼር
984 viewsHusen Mohammed, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 17:22:42
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ 5 ከፍተኛ አባላቱን አገደ
(ቀልድ እና ቧልት የማይጠግብ ሕዝብ- መቼም ጨዋታ ነው፤ ውሽማሽ ማን ማን ነው )
*********
የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በነበረው ስብሰባ ተጠያቂነት እሰከሚረጋገጥ ድረስ ቱባ ቱባ መሪዎቹን ከማዕከላዊ ኮሜቴ አገደ የምትል ቧልት እየተዘዋወረች አስተዋልኩ።

ህወሀት (TPLF) ;
1. ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
2. ፈትለወርቅ ገብረዝጊሔር
3. ጌታቸው ኣሰፋ
4. ኣለም ገብረዋህድ እና
5. ጌታቸው ረዳን ከማዕከላዊ ስራ ኣሰፈፃሚ አባልነታቸው አግዷል የሚል ምንም ስሜት የማይሰጥ ኮተት እየተሰራጨ ነው ።

የ ህወሀት ማ.ኮሚቴ ከ 07-10/05/ 2015 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ስማቸው ከላይ የተጠቀሰውን አባላቱን ከተጠያቂነት ጋር በተያያዘ አግዷል።ማዕከላዊ ኮሚቴው ያገዳቸው በጦርነቱ ለደረሰው ኪሳራ ሁሉ ተጠያቂ እናንተ ናችሁ በሚል እንደሆነም የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል ይላል ሲዘዋወር የሚስተዋለው ሰበር ዜና። ተራቁጥር 3 ላይ ስሙ የተገለፀው ታጋጅ በጦርነቱ ወቅት በልብ ህመም ሳቢያ ሞተ አልተባለም እንዴ ነው ወይስ መቃብሩ መስኮት ነበረው

ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ- ማን ማንን ነው የሚያግደው
❝መቼም ጨዋታ ነው፤ ውሽማሽ ማን ማን ነው ❞

_
1.0K viewsHusen Mohammed, 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ