Get Mystery Box with random crypto!

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayatv — አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ
የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayatv — አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ
የሰርጥ አድራሻ: @alhidayatv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.07K
የሰርጥ መግለጫ

ኑ ተባብረን ባለን አቅም የቲሞችንና የተቸገሩ ሙስሊም ወገኖቻችንን እንርዳ
በልብስ👕👖 በገዘብ በአስዜዛ በጉልበት በሀሳብና
በተለያዩ በቤት ቁሳቁሶች መርዳት ትችላላቹ
ንግድ ባንክ
1000375043298
ሪድዋን ሙሀመድ
አባል መሆን ለምትፈልጉ
ለበለጠ መረጃ
251993632424
ወይም የቢሮ ቁጥር
251703136300
ወይም በኢቦክስ
@RidAmirsab
ሰደቃ ወጀልን ታብሳለች ረሱል (ﷺ)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-17 21:43:46
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረከትሁ

ዛሬ አልሂዳያ ጀማ 320ቁርአን ገዝተናል ኢንሻ አሏህ የፊታችን እሁድ ለሁዳ መስጀመድ ገቢ ይደረግላቸዋል

ይሄንን ቁርአን ለመግዛት የተባበራቹሁን እህት ወንድሞች ጀዛኩምሏሁ ኸይረን

https://t.me/ALHidayaTv/19970
336 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 15:45:08 አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረከትሁ

ዉድ የአል ሂዳያ ቤተሰቦችና አባላቶች ኢንሻ አሏህ ማታ ከኢሻ ሶላት በኋላ ሹራ ይኖረናል በተቻላቹ መጠን የጀማአዉ ወና አሚሮች ተሳተፉ
651 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 15:36:40 ከነብያት ታሪክ

ምድር ላይ የተፈፀመዉ የመጀመሪያዉ ወንጀል።

ቃቢል በተመሳሳይ እርግዝና አብራዉ የተወለደች እህቱን ማግባት ፈለገ ። በሌላ ጊዜ በሌላ እርግዝና ከተወለዱት እህቶቹ ዉስጥ አንዷን ማግባት እንዳለበት ለመፈፀም እያሰበ ያለዉ ግን ከመለኮታዊ ህግ ጋር በፍፁም እንደማይሄድ ሀቢል ሊያስረዳዉ ሞከረ። ቃቢል ግን የሀቢልን ማስጠንቀቂያ ግድ አልሰጠዉም። ድርጊቱ ምንም ችግር እንደሌለበት ተናገረ።

ሀቢል ለወንድሙ ቃቢል አንድ ሀሳብ አቀረበለት። ማንኛችን ትክክል እንደሆን ለአሏህ ቁርአን እናቅርብ አለዉ። በዚያ ጊዜ ሰዉ ሰርቶ ያገኘዉን ነገር ቁርባን ያቀርብ ነበረ። ለቁርባን የሚቀርበዉ ነገር ከተራራ ጫፍ ላይ ይቀመጣል እሳት ከሰማይ በመዉረድ በልታ የጨረሰቺዉ ቁርባን ከአሏህ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወቃል።

ሀቢል የፍየልና የበግ መንጋ ነበረዉ የሰባና ትልቅ ወጠጤ በግ መረጠ። ቃቢል ደሞ በእርሻ ይተዳደር ነበረ። ከምርቱ ዉስጥ ጥሩ ያልሆነዉን ለቁርባን አቀረበ። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ከተራራ ጫፍ ላይ ያስቀመጡትን ቁርባናቸዉን ለማየት ሔዱ የሀቢል ሙክት ተቀባይነት ሲያገኝ የቃቢሉ እንክርዳድ ግን እንዳስቀመጠዉ አገኘዉ። ቃቢል በጣም ተናደደ ሀቢልንም ለመግደል ወሰነ። ቁርአንም እኝዲህ ይተርከዋል።


۞ وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ابْنَيْ آدَمَ بِالْحَقِّ إِذْ قَرَّبَا قُرْبَانًا فَتُقُبِّلَ مِنْ أَحَدِهِمَا وَلَمْ يُتَقَبَّلْ مِنَ الْآخَرِ قَالَ لَأَقْتُلَنَّكَ ۖ قَالَ إِنَّمَا يَتَقَبَّلُ اللَّهُ مِنَ الْمُتَّقِينَ
በነርሱም ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ ቁርባንን ባቀረቡና (አላህ) ከአንደኛቸው ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለ ጊዜ (የኾነውን) በእውነት አንብብላቸው፡፡ «በእርግጥ እገድልሃለሁ» አለው፡፡ (ተገዳዩ) «አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው» አለ፡፡
{አል ማኢዳህ 27}


فَبَعَثَ اللَّهُ غُرَابًا يَبْحَثُ فِي الْأَرْضِ لِيُرِيَهُ كَيْفَ يُوَارِي سَوْءَةَ أَخِيهِ ۚ قَالَ يَا وَيْلَتَا أَعَجَزْتُ أَنْ أَكُونَ مِثْلَ هَٰذَا الْغُرَابِ فَأُوَارِيَ سَوْءَةَ أَخِي ۖ فَأَصْبَحَ مِنَ النَّادِمِينَ
የወንድሙንም ሬሳ እንዴት እንደሚሸሽግ ያሳየው ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር ቁራን ላከለት፡፡ «ወይ እኔ የወንድሜን ሬሳ እሸሽግ ዘንድ እንደዚህ ቁራ ብጤ መኾን አቃተኝን» አለ፡፡ ከጸጸተኞችም ኾነ፡፡
{ አል ማኢዳህ 31}


ኢንሻ አሏህ በቀጣዩ ክፍላችን
ጠቃሚ ትምርቶች ከቃቢልና ከሀቢል ታሪክ ። ይዘንላቹህ እንቀርባለን።

ቻናሉን ተቀላቀሉ
Al Hidaya TV
Al Hidaya TV
594 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 13:38:34 ሰበር መረጃ
_________
በጉራጌ ክልል ጉችሬ ወረዳ ካሁን በፊት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃባቹሁንና ሂጃባቹሁን ካላወለቃቹህ አትማሩም ሲባሉ ኒቃባችንንና ሂጃባችንን ከምናወልቅስ ትምርቱ ይቅርብን በማለት ብዙወቹ ትምርታቸዉን ትተዉ አቋርጠዉት ነበረ ታዳ በዚ ምክኒያት የአካባቢዉ ሙስሊም ማሀበረሰብ ትንሽ ትልቁ ሀ ሴት ወንዱና ህፃናትም ሳይቀሩ ታስረዉ ይገኛሉ

ነገር ግን ይሄንን ነገር የወረዳዉ አስተዳደር ወደ የፊታችን ሰኞ ኒቃብና ሂጃባቹሁን አዉልቃቹህ ትምርት ካልጀመራቹህና ካልቀጠላቹህ ከየቤታቹህ በየቤታቸዉ እየመጡ እንደሚያስሯቸዉና ጉልበትም እንደሚጠቀሙ መናገራቸዉን አል ሂዳያ ቲቪ ቦታዉ ድረስ በመሄድ ጉዳዩን አሰጋግጧል።

ታዳ ይሄንን ጉዳይ መጅሊስ ችላ ቢለዉም እኛ የምንመራዉ በመጅሊስ አይደለምና ሙስሊሙ ማሀበረሰብ የተቃዉሞ ድምፁን ሊያሰማ ይገባዋል

#አልሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መንገድ
Al Hidayah TV is the direct way

AlHIDAYA TV
AlHIDAYA TV
655 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 02:23:37
ዉዱ ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ኸይር ስራዉን አሏህ ይዉደድለትና

ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ሁልጊዜ በኸይርስራዉ ነዉ የሚታወቀዉ

የአል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ ዋና አሚር ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ዛሬም እንደተለመደዉ የማይታሰብ ትልቅ ኸይር ነገር ሰራ

ሁላችንም እንደምናዉቀዉ ካሁን በፊት ለዚ ኸይር ስራ ብሎ ከዉጭ የተላከለትን አይፎን ፎርቲን ፕሮማክስ ስልክ ሰዎች እየተራቡ እኔ የቅንጡ ስልክና ዉድ ስልክ ምን ይሰራልኛል በማለትና የተላከለትን ስልክ በመሸጥ ሌላም ከሰራበት ገዘብ ላይ በመጨመር 12 አቅመ ደካማ እናቶችን ስራ ማሲያዙና ወርሀዊ የቤት አስቤዛ ማስገባቱ ይታወቃል እንዲዲሁም ለ2መስጂዶችና መድረሳዎች ከ4600በላይ ቁርአንና ከ3230በላይ ኑራንያ ማስገባቱም ይታወቃል

ታዳ ይህ አሚራችንና ወንድማችን ዛሬም እንደተለመደዉ ለበረካ መስጂድ 1200ቁርአንና 400ኑራንያ ገዝቶ ገቢ ማድረጉን ልናሳዉቃቹ እንፈልጋለን

ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ኸይር ስራዉን አሏህ ይዉደድለትና አል ሂዳያ ጀማአን ከመሰረተበት ሰአትና ቀን ጀምሮ ይሰራል ተብሎ ከሚታሰበዉ በላይ እጅግ በጣም ትልቅ ኸይር ስራ እየሰራ ይገኛል ታዳ ለዚህ ምርጥና ለጋሽ ወንድሜችን ምን ብንሸልመዉና ምን ብናደርግለት ይገባዋል ትላላቹ

ታዳ ይሄንን ስራዉን ሶሻል ሚዲያ ላይ ኸይር ስራዉን አሏህጂ ሰዉ እንዲያዉቅ አልፈለገም ነበረ ነገር ግን እኔ የአል ሂዳያ ምክትል አሚር ኢክራም ሰኢድ ሌሎች ገዘባቸዉን ለሚቋጥሩ ሰዎች መነሳሻ ይሆን ዘንድ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሼር ማድረጌን ላሳዉቃቹ እፈልጋለዉ

ነገ ጥለህዉ ለምትሞት ገዘብ ዛሬ ብትሳሳ ከቱ ልፋትጂ ስኬት የለዉም ያደም ልጅ ሆይ ገዘብህን አጠቃቀሙን ከቻልክበት ጀነት ያስገባሀል ካልቻልክበት ግን ጀሀነም ያስገባሀል

https://t.me/ALHidayaTv/19884
911 viewsAllah is great, edited  23:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 18:17:51
በገዘብ ካልሆነ ቁርአን አናስቀራም

በአሁኑ ሰአት ገዘብ ካልተከፈላቸዉ በስተቀር ቁርአን አናስቀራም የሚሉ አካላት ሶሻል ሚዲያ ላይ እየበዙ መተዋል

ስንቶች ቁርአን መቅራት እየፈለጉ ቁርአንን ማዎቅ እየፈለጉ ነግር ግን አስቀሪ የተባሉ አካላት ወይም ድርጅቶች ምክኒያት ገዘብ ካልከፈላቹህ አናስቀራቹሁም በማለት በጣም ብዙወች ቁርአንን ከመቅራት ወደ ኋላ ብለዋል

መክፈል የቻለ ቁርአን ይቀራል ያልቻለ ደሞ በገዘብ ምክኒያት ከመቅራ ወደ ኋላ ይላል

ሙሉ መረጃዉን በቅርብ ቀን በአል ሂዳያ ቲቪ ይጠብቁን

https://t.me/HiDAYATV
https://t.me/HiDAYATV
467 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 13:31:00 ሱራ አል ካህፍ የተወሰነዉ ቁርአን ተፍሲር።

الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَنزَلَ عَلَىٰ عَبْدِهِ الْكِتَابَ وَلَمْ يَجْعَل لَّهُ عِوَجًا ۜ
ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው፡፡ {1}

قَيِّمًا لِّيُنذِرَ بَأْسًا شَدِيدًا مِّن لَّدُنْهُ وَيُبَشِّرَ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا حَسَنًا
ቀጥተኛ ሲሆን ከእርሱ ዘንድ የኾነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፣ እነዚያንም በጎ ሥራዎችን የሚሠሩትን ምእመናን ለነሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን ሊያበስርበት፤ (አወረደው)፡፡{2}

مَّاكِثِينَ فِيهِ أَبَدًا
በእርሱ ውስጥ ዘለዓለም የሚቆዩበት ሲኾኑ (ያላቸው መኾኑን)፡፡{3}

وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا
እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል» ያሉትን ሊያስፈራራበት (አወረደው)፡፡{4}

مَّا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ وَلَا لِآبَائِهِمْ ۚ كَبُرَتْ كَلِمَةً تَخْرُجُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ ۚ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبًا
ለእነሱም ለአባቶቻቸውም በርሱ ምንም እውቀት የላቸውም፡፡ ከአፎቻቸው የምትወጣውን ቃል ምን አከበዳት! ውሸትን እንጂ አይናገሩም፡፡{5}

فَلَعَلَّكَ بَاخِعٌ نَّفْسَكَ عَلَىٰ آثَارِهِمْ إِن لَّمْ يُؤْمِنُوا بِهَٰذَا الْحَدِيثِفًا
በዚህም ንግግር (በቁርኣን) ባያምኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን ይፈራልሃል፡፡{6}

إِنَّا جَعَلْنَا مَا عَلَى الْأَرْضِ زِينَةً لَّهَا لِنَبْلُوَهُمْ أَيُّهُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا
እኛ ማንኛቸው ሥራው ያማረ መኾኑን ልንፈትናቸው በምድር ላይ ያለን ሁሉ ለእርሷ ጌጥ አደረግን፤{7}

وَإِنَّا لَجَاعِلُونَ مَا عَلَيْهَا صَعِيدًا جُرُزًا
እኛም በእርሷ ላይ ያለውን (በመጨረሻ) በእርግጥ በቃይ የሌለበት ምልጥ ዐፈር አድራጊዎች ነን፡፡{8}

أَمْ حَسِبْتَ أَنَّ أَصْحَابَ الْكَهْفِ وَالرَّقِيمِ كَانُوا مِنْ آيَاتِنَا عَجَبًا
የዋሻውና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራቶቻችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን{9}

إِذْ أَوَى الْفِتْيَةُ إِلَى الْكَهْفِ فَقَالُوا رَبَّنَا آتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًا
ጎበዞቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና «ጌታችን ሆይ! ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን፤ ለእኛም ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡{10}

فَضَرَبْنَا عَلَىٰ آذَانِهِمْ فِي الْكَهْفِ سِنِينَ عَدَدًا
በዋሻውም ውስጥ የተቆጠሩን ዓመታት በጆሮዎቻቸው ላይ መታንባቸው፡፡{11}

ثُمَّ بَعَثْنَاهُمْ لِنَعْلَمَ أَيُّ الْحِزْبَيْنِ أَحْصَىٰ لِمَا لَبِثُوا أَمَدًا
ከዚያም ከሁለቱ ክፍሎች ለቆዩት ጊዜ ልክ ያረጋገጠው ማንኛው መሆኑን ልናውቅ አስነሳናቸው፡፡{12}

نَّحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ نَبَأَهُم بِالْحَقِّ ۚ إِنَّهُمْ فِتْيَةٌ آمَنُوا بِرَبِّهِمْ وَزِدْنَاهُمْ هُدًى
እኛ ወሬያቸውን በአንተ ላይ በእውነት እንተርካለን፡፡ እነሱ በጌታቸው ያመኑ ጎበዞች ናቸው፡፡ መመራትንም ጨመርንላቸው፡፡{13}

وَرَبَطْنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ إِذْ قَامُوا فَقَالُوا رَبُّنَا رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَن نَّدْعُوَ مِن دُونِهِ إِلَٰهًا ۖ لَّقَدْ قُلْنَا إِذًا شَطَطًا
(በንጉሣቸው ፊት) በቆሙና «ጌታችን የሰማያትና የምድር ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክን አንገዛም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላን ብናመልክ) ወሰን ያለፈን (ንግግር) በእርግጥ ተናገርን፡፡» ባሉ ጊዜ ልቦቻቸውን አጠነከርን፡፡{14}

هَٰؤُلَاءِ قَوْمُنَا اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً ۖ لَّوْلَا يَأْتُونَ عَلَيْهِم بِسُلْطَانٍ بَيِّنٍ ۖ فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا
«እነዚህ ሕዝቦቻችን ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙ፤ (እውነተኞች ከኾኑ) በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን ለምን አያመጡም በአላህም ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማነው» (አሉ)፡፡{15}

#ማታ_ይቀጥላል,,,,,,,,,,
#ቻናሉን_ተቀላቀሉ
https://t.me/HiDAYATV
https://t.me/HiDAYATV
592 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 22:19:40 አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረክሁ

ተቋርጦ የነበረዉ ስጦታ ለሙስሊሟ እህቴ የሚል አስተማሪ ተከታታይ ትምርት ቀጥሏል።

የዉበት ወጣትነት አድናቂዎች መበራከት ሌላም ሌላም ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ግን ይሄንን ሁሉ አሸንፎ በኒቃብ ሂጃብ መሸላለም ታላቅ ኢማንን እና ታዛዥነትን ከሚያንፀባርቁ ምልክቶች አንዱ ነዉ። በተለይ ደሞ ለየት ባለ መልኩ ኢስላማዊ ያልሆኑ ነገሮች ላይ ወይም ሂጃብ እንደ ባይተዋር ከሚታይበት አካባቢ ላይ ሂጃባቸዉን ኒቃባቸዉን ግጥም አድርገዉ ለብሰዉ የሚኖሩ እህቶቻችን ምን ያህል የኢማንና የጨዋነት ደረጃ ላይ እንዳሉ በቂ ምስክር ነዉ። እኔም በበኩሌ ላቅ ያለ አድናቆት ልነግራቸዉ እወዳለዉ።

በእርግጠኝነት ደሞ የምለዉ ነገር ቢኖር እንደናተ አይነቱ ነገር አለሙ ለሂጃብ ከተመቻቸለት ሰዉ ጋር እኩል እንዳልሆነ ነዉ። እዉነት ነዉ የምልሽ እህትዬ አንቺ በዚህ ጥንካሬ መታየትሽ አንቺ ለስቶቹ መቃናት የሂጃብና የጨዋነት ካባ እንዲደርቡ ለማድረግ ሰበብ ሁነሻል መሰለኝ። አሏህን ሱብሀነሁ ወታአላ በዚያ ባማሩትና በተዋቡት ስምና ባሀሪወቹ እለምነዋለዉ። የበለጠ ጥንካሬና ፅናት ያላብስሽ። ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅሽ ይህንን ታላቅ ንፅህና ልጓምሽን ለማስጣል ። የሚያሴር ሁሉ አሏህ በራሱ ሴራ የሚጠለፍ ያድርገዉ። አሏሁመ አሚን።

በእዉነቱ የዉበት ዋናዉ መገለጫ ፊት ነዉ። አንድ ሰዉ ስለሚወዳት ወይም ስለሚመኛት ሴት ሲያስብ ከሁሉም በፊት ፊቷን ነዉ የሚቀርፀዉ የሚያስጨንቀዉ። ለማየትም የሚቋምጠዉ ። ዳሌ ሽንጥ ወገብ እጅ እግር ሌላም ሌላም ከፊት በኋላም የሚመጡ ነገሮች ናቸዉ። ታዲያ ይህ የዉበት መገለጫ ሳቢ ከሆነ ንዴት መሸፈን የለበትም ይባላል??? መልሱ ለማንም ግልፀ ነዉ አሏህ ሁላችንንም በዉስጣዊም በዉጫዊም ሂጃብ ያስጊጣቹ ። አንቺ ዉዷ እህቴ እንግዲህ ኒቃብሽን በመልበስ ደረጃሽን የበለጠ ከፍ ልታደርጊ ይገባሻል።

ኒቃብ መልበስ ከነገር አለሙ የሚያሰናብት አድርገዉ ለሚመለከቱ እንዲሁም ለሚሰብኩ ለዉጪም ይሁን ለዉስጥም ጠላቶችሽ ኒቃብሽን ለብሰሽ ለራስሽም ይሁን ለሌሎች መልካም ነገር በማበርከት ላይ ፍፁም እንደማያቅብሽ በተግባር አሳያቸዉ።

አዎ በያቸዉ ። ኒቃቤ ሰዉነቴንጂ አእምሮየን አስተሳሰቤን አልሸፍነዉም እስኪ ይችን ግጥም ልጋብዝሽ አሏህ ያግዝሽ እህትዬ።

ኒቃቤ

አዎ ንቁ ነኝ ሽልምልም በኒቃቤ ኩሩ
ጠላት ቢንገበገብ ቢቆጩብኝ ቢያሩ
ድንጋይን ፈንቅለዉ ጉድጓድ ቢቆፍሩ
ይመክትልኛል ወልዩ ከቢሩ
ሰሚነኝ ታዛዥ ነኝ ጌታየን አፍቃሪ
ነብዬን ተከታይ በሱናቸዉ ሰሪ
ይህ ነዉ መሰረቴ የመኖሬ አላማ
አሏህን ብቻ ማምለክ በዱንያዉ አድማ
ነገ እንዳጭድበት የአኼራዉን ምንዳ
ፍፃሜዬ እንዳይበላሽ እንዳይሆን ነዳማ
ኒቃቤ! መማሬን አያቅብ መስራቴን አይገታ
ሀራም የሌለበት ድብልቅ ጋጋታ
አዎ አበርካች ነኝ መልካም አስተዋጾ
ትዉልዶችን መልማይ በኢስላም አንፆ
ይህን የቸረኝ አሏህ ምስጋና ይገባዉ
እኔስ ተደነኩኝ ለታላቅ ልእልናዉ።

#ወንድም_ሪድዋን_ሙሀመድ

#አል_ሂዳያ ሚዲያ
#ይቀጥላል_ቻናሉን_ተቀላቀሉ
https://t.me/HiDAYATV
https://t.me/HiDAYATV
287 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 14:54:17 «              ጭንጎ ላይ ምን ተፈጠረ ?

በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን በአኔሌሞ ወረዳ በቀን 29/04/2015 ከንጋቱ 11:30 የአከባቢው ሙስሊም የዘውትር የንጋት ሷላቱን ለመስገድ ወደ መስጂድ እያመራ ባለበት ወቅት ከበንደሊቾ ፈቴና ከበንደሊቾ ቆንቦጣ የተወጣጡ ከ200 በላይ የምልቁ ፅንፈኘ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑ ግለሰቦች በህብረት ተሰባስበው የተለያዩ ለጥቃት የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን/ቁሳቁሶችን ማለትም ጦር ፣ ገሶ፣ ገጀራ እንዲሁም ድንጋይ በመታጠቅ ቤትለቤት እየዞሩ ምንም ባልተዘጋጁ እና ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ "ኢየሱስን ካልተቀበላችሁ እንገድላችኋለን ወይም ሀዲያ ዞን ውስጥ መኖር አትችሉም በማለት ከፍተኛ ድብደባ እና ጉዳት አድርሰዋል።
በዚህም ምክንያት ከ60(ስልሳ በላይ) ሙስሊሞች ከባድ እና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን በመሳት (comma) ውስጥ ያሉና ወራቤ ኮንፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በአከባቢው በሚገኝ ጤና ጣቢያ እርዳታ ተደርጎላቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ፅንፈኛ ሀይሎች በሴቶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ እና ማስፈራራት አልፎም አንቆ በመያዝ እምነትሽን ካልቀየርሽ እንጨርስሻለን እስከማለት የደረሰ በደል አድርሰዋል።
በመስጂዶችም ላይ የድንጋይ እሩምታ የተፈፀመባቸው። ይህ በንዲህ እንዳለ ከተደወለላት  ከሰኣታት ቦኃላ አከባቢው የደረሰው የወረዳው የፖሊስ ሀይል በጉዳዩ እጁ እንዳለበት በሚያሳብቅ መልኩ አንድም ወንጀለኛ በሰአቱ ተሯሩጦ ለመያዝ ፍላጎት አለሳየም። ይባስ ብሎ የተጎዱትንም ወደ ህክምና ተቋም ለማድረስ ከፍተኛ ዳተኝነት አሳይቷል። በተጨማሪም ከፖሊስ ስነምግባር በማይጠበቅ መልኩ
የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል እንዲያዳርሱ ስመፀኗቸው "ስትፈልግ በጭንቅላትህ አዝለሀው ዙር" የሚል እጅግ ሰቅጣጭ መልስ ሲሰጡ ነበር።

➞ ለመሆኑ ይህ የተጠና እና የተቀናጀ የሐዲያ ሙስሊሞች ሰቆቃ ማብቂያው መች ይሆን

#ፍትህ ለሐዲያ ሙስሊሞች»
ሌሎች መረጃዎች እንዲደርሳቹ ከጸለጋቹ ቻናሉን ተቀላቀሉ
https://t.me/HiDAYATV
https://t.me/HiDAYATV
637 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 22:32:40 የሴቶች ጋጋታ ምን ያረግልኛል አስተዋይ የሆኑ 4 ይበቁኛል
614 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ