2022-12-11 22:47:33
የኢስላምን ውላታ ለበላሿ እህቴ!!!
~~~~
ኢስላም ለሴት ልጅ እጅግ በጣም ዘርፈ-ብዙ ውለታዎችን ውሏል።ከዋላቸው ውለታዎች ትልቁና ዋነው በህይወት የመኖር መብቷን ማረጋጋጡ ነው።እንደሚታወቀው ነብዩ ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከመላካቸው በፊት(በጃሂሊያ ስርዓት) ሴት ልጅ እስከነ ነፍሷ ትቀበር ነበር።ኢንሳሳት ላይ እንኳን የማይወሰድ አሰቃቂ እርምጃ ነበር የሚወሰድባት።ይህንን እርኩስ ስርዓት ለዓለም ብርሃን የሆኑት ነብዩና ሙሐመድ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከተላኩ በኋላ ነበር ከስር መሰረቱ ገርስሰው ሴት ልጅ ከጌታዋ የተሰጣት ህይወት በነፃነት እንድትኖር ያደረጉት።
ዛሬ ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ሴት እህታችን ነብዩ ይዘውላት የመጡትን መንገድና ስርዓት በመጣስ ለምርኣባውያን ፋሽንና ሰይጣናዊ መንገድ አጎብድዳ የነርሱን መንገድ ኮቴ በኮቴ እስከመከተል ደርሳለች።ይህ ደግሞ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሒ ወሰለም ከዛሬ አንድ ሺ አራት መቶ አመት በፊት የተናገሩት ነው።("ለተተቢዑነ ሰነነ ሚን ቀብሊኩም ሐዝወል ቁዛ ቢል ቁዛ ሀታ ለው ደኸሉ ጁህረ ዷቢን ለደኽልቱሙህ")ከናንተ በፊት የነበሩትን መንገድ ትከተላላችሁ ኮቴ በኮቴ። የወከሎ(አርጃኖ)ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን ተከትላቹሃቸው ትገባለችሁ አሉ። ሶሃቦችም ጠየቁ፦"አል የሁዱ ወናሷራ ያረሱለላህ?" የሁዶችንና ነሷራዎችን ማለታችሁ ነው እንዴ የአላህ መልክተኛ? አሏቸው ነብዩም "ፈመን" ታዲያ ማንነው? አሉ። ልብ በይ እህቴ ነብዩ ይህንን ሀዲስ የተናገሩት ከስሜታቸው አይደለም።አላህ ወደፊት ህዝባቸው ላይ የሚከሰተው ስላሳወቀቸው ነው።ክስተቱን ይሀው ባለነበት ዘመን በተጨባጭ አየነው።
ልብ በይ እህቴ ድሮ በጃሒሊያ ዘመን ሴት ልጅ በግፍ ምንም በማታውቀው አፈር ውስጥ ነበር የምትቀበረው።ዛሬ ግን ምእራባውያን ባመጡልሽ ጦስ በበጎ ፈቃድሽ ጀሓነም ኢሳት ውስጥ እየቀበሩሽ ነው።ነብዩ ያመጡልሽን መከበሪያና ነፃነት ልክ እንደ አፈና ጭቆናና የሴትነት መብት ረገጣ አድርገው ባሳዩሽ የሰው አውሬዎች በምእራባውያን ተጠልፈሽ የዘለዓለም ፀፀት ውስጥ እየጣሉሽ ነው።
ከአለባባስሽ ጀምሮ ያለሽበትን ሁኔ በደንብ ካስተወልሽው ተፈጥሮሽና አሁን ያለሽበት ማንነትሽ የሰመይና ምድር ያክል መራራቁን ታገኚዋለሽ።ኢስላም የሴት ልጅ አለባባስ ሙሉ በሙሉ ትሸፈን ሲል እኮ ለራስሽ ከተለያዩ ሊደርሱብሽ ከሚችሉ ፆታዊ ትንኮሳዎች መጠበቂያ እንዲሆንሽ እንጂ አንቺን ለመበደል ወይም የበታች ለማድረግ እንዳልሆነ ጠንቅቀሽ እወቂ።
ዛሬ ግን ምእራባውያን ያሰቡልሽ መስሎሽ "ሴትን ልጅ ከሃይማኖትና ከበህል ተፅዕኖ ነፃ እናውጣት" ብለው ከመጡ የፍልስፍና ቂላቂሎች ወጥመድ ወድቀሽ የአኸራሽ ጉዳይ ምን ሊሆን እንደሚችል ግን ከወዲሁ አስቢበት።ዛሬ የነብዩን ሱና ጥሰሽ የከሃዲዎችን ኮተት ፋሽን እጎተትሽ ለመሆኑ በዚሁ ሁኔታ ጀነት ይታሰባልን? "ከላ" በፍፁም።
ሌላው ቀርቶ ስለ አለባባስሽ ሁኔታሽ በስሱ እንመልከት፦
አላህ ያከበረውን ሰውነትሽን በተከበረው ሒጃብ(ጂልባብና ኒቃብ) ተሸፋፍነሽ የራስሽንም የሙስሊም ወንድምሽን ከአስቀያሚው ዝሙት ታደጊ ብሎሽ ሲያበቃ አንቺ ግን ከካፍሮች በኮረጅሽው ፋሽንን ጋር በመገለባበጥ ከራስሽ ተፈጥሮ ጋር ተኳርፈሻል።አላህ በቁርኣኑ፦"አንተ ነብይ ሆይ ለምስቶችህ ለልጆችህና ለምእመናን ሴቶችም በላቸው ሒጃባቸውን(ጂልባብ ኒቃባቸውን) በራሳቸው ላይ እንዲለቁ እዘዛቸው" ይላል።እንግዲህ "ሙእሚን ሴት መሆን እፈልጋለሁ የነብዩ ተከታይ ነኝ"ብለሽ የምታስቢ ከሆነ አለባበስሽ ምን መምሰል አንዳለበት ከነብዩ ሚስቶችና ልጆች ተርታ አሰልፎሽ በነብዩ አንደበት እየመከረሸ ነው።ረቡና ተባረከ ወተዓላ!!!። በወርቃማው ምክር ቀደምት ሙእሚናት ሴቶች እንደተመከሩበት አንቺም ተመከሪበት።ከልብ ባልመነጨ ውዴታ ዝም ብለሽ "ፍዳካ ያረሱለላህ"እያልሽ ፕሮፋይል ማድመቂያ አትሰሪ።ውዴታሽን ትእዛዛቸውን በመፈፀም በተግባር አሳይ።
እንዲህ ሲባል አንዳንዷ እህት ያምታመጣው አንድ ንግግር አለች "ኢማን በልብ ነው በተከናነበ አይደለም።" ይቺህ እግርና ራስ የሌላት ከመሀል የተቀነጨበች ንግግር ብዙ ስሜት ተከታዮች የሚጠቀሙባት ነጣላ ንግግር ናት።ኢማን በልብ ብቻ ነው ወይስ በውጫው አካልም የሚታይ ነው? አብረን እንመልከት፦
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዳሉት፦"ሰውነታችን ውስጥ አንድ ቁራጭ ስጋ አለች እሷ ስትስተካከል መላው በሰውነታችን ይስተካከላል።እሷ ስትበላሽ መላው ሰውነታችን ይበላሻል።" ተመልከች እህቴ ነብዩ እንዳሉት ቀልቡ የተስተካከለ ውጫዊ አካሉም ይስተካከላል "።እያሉሽ ነው። አንቺ ግን ዳሌሽን ወንዶችን ለማማለል በጠባብ ልብሶች ወጣጥረሽ፣ጡትሽን ወደ ፊት ገትረሽ፣ፀጉርሽን እንደ ግመል ሻኛ ወደ ላይ ፎቆ ሰርተሽ፣አይንሽን በኩል አጥቁረሽ፣ከንፈርሽን ደም እንደላሰ ውሻ በቀለም ተነክረሽ....ወዘተ። እነዚህንና የመሳሰሉትን ቆሻሻ በህሪያትን ተላብሰሽ ኢማን አንዳለው አፍሽን ሞልተሽ ስለ ኢማን ስታወሪ ቲንሽ እንኳን አታፍሪም? ወይስ ያንቺ ኢማን ነብዩ ከተናገሩት የኢማን አይነት የተለየ ነው? ለነገሩ ስለ ኢማን ገና በቅጡ መች ገባሽና።ያንቺ ጭንቅላት ከእውቀት ነፃ የሆነ ማሽን ሆኗል።
ለመሆኑ አሁን ተወጣጥረሽ ወደ ሀራም የተጣራሽበት ሰውነትሽ ነገ ምን እንደሚጠብቀው አስበሽ ታውቂያለሽ???
አስቲ የተወሰነ ላስታውስሽ፦
ያው መቼም እዝህች ምድር ላይ ለተወሰነልሽና ለተፈቀደልሽ ግዜ ከኖርሽ በኋላ ሞት የሚባለው መመለሻ የሌለው በጣም ሩቅ ጉዞ መጓዝሽ አይቀርም። አንግዲህ እንደ ሚታወቀው ነፍስሽ ከአካልሽ ከተነጣጠለችባት ሰዐት ጀምሮ በሰው እጅ መገለባበጥሽ ይጀምራል። ስምሽ ሁላ "ሬሳ" ይባላል። ዛሬ ሰውነትሽን ሰትሪው አጅነብይ እንዳይመለከተው ስትባይ አምፀሽ ስትገላለጪ የነበረውን ያኔ ሳትወጂ አጣቢዎች ራቁትሽን አድርገው ያገለባብጡታል።አጥበው ሲጨርሱም ዛሬ በተለያዩ የቻይና ፋሽን ጨርቅ ስታሽሞነሙኚው የነበረውን አካልሽን በተወሰነች አቦጀዴ(ከፈን) ጠቅልለው ቁጭ።ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!!
ያንቺ ጣጣ መች በዚህ ያበቃል ገና የባሰው ሰቀቀን የተሞላበት ህይወት ከፊትለፊትሽ ተደቅኖ።እሱም የቀብር(በርዘኽ) ህይወትሽ ነው።ገና ሬሳሽን ተሸክመው ሲሄዱ "ወዴት ነው የምትወስዱኝ? መልሱኝ እንጂ" እያልሽ ገና ቀብሩን ሳትገቢ የከንቱ "ዋይታሽን" ታሰሚያለሽ። የሞተን መቅበር ግዴታ የሆነባቸው ቤተሰቦችሽና ወገኖችሽ ሳይወዱ ወስደው በዛች ከሁለት ሜትር ባልበለጠች የዘለዓለም ቤትሽ ሸለቆ ውስጥ ያስገቡሻል።ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!! እህቴ ዛሬ አንደፈለግሽ ስትወጣጥሪውና በተለያዩ የሜካፕ አይነቶች ስታኳኩይው የነበረው ሰውነትሽ ምን ላይ እንደሚወድቅ አስቢው።ቀጥታ አፈር ላይ ነው የምትነጠፊው።መኚታሽ አፈር፣ትራሱ አፈር፣ ግድግዳው አፈር፣ ጣሪያው አፈር፣ በላይሽ ላይ የሚመለሰው አፈር።ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!!።
ነኪርና ሙንከር መጥተው ሲጠይቁሽ ትክክለኛውን መልስ ከመመለስ ይልቅ አንደ አሂያ ነው የምትጮሂው። ሰባት ምድርን ቁልቁል እስክትገቢ ድረስ ነው አናትሽን በያዙ መዶሻ የሚያላትሙሽ።ቀድሞውንም በጠባቡ የተሰራቿ ቀብርሽ ይባስ ብላ የጎዲን አጥንትሽ የቀኙ በግራ የግራው በቀኝ እስከሚወጣ ሁለቱ ኩላሊቶችሽ ካፍንጫሽ እስከሚወጣ ቀብርሽ ስያጣብብሽ ምን ይውጠሽ ይሁን???
እህቴ "ሳይቃጠል" በቂጠል ነውና አሁንም አረፈደም ሞት ሳይቀድምሽ በተውበት ቅደሚው። የነብዩ ሱና ይግዛሽ።ዲናችን ሙሉእ የሆነ ዲን ነውና ተብቃቂበት።
ሼር ሼር
Abu Mahir (Abdurezak)
675 viewsእንደ አበባ ፈክተሽ ወንድ ከምታፈዢ ሂጃብሽን(ኒቃብሽን) ለብሰሽ ጌታሽን ተገዢ!!!, 19:47