Get Mystery Box with random crypto!

«የቲምን አደራ» የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣ ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣ | አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

«የቲምን አደራ»

የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣
ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣

አባት የሞተበት ገና በልጅነት፣
እናቲቱም ብትሆን አቅሟ የከዳት፣

እጅግ ተቸገሩ ማንም በሌለበት፣
በጣሙን ተራቡ የለም ሚጠይቁት፣

በቀን አንድ ግዜ እሱንም ካገኙት፣
አንድ ልጅ ነበረ አባት የሞተበት፣

ከእናቱ የሚኖር እሷ አቅም የሌላት፣
ነበር በረመዳን በተራዊህ ሰአት፣

እናቱን ጠራና እንደዚህም አላት፣
ሰዎች ተመለሱ ከተራዊህ ሰላት፣

እኛ ሳናፈጥር ይሄሁሉ ሰአት፣
እናቱ ምን ትበል ምን ጉድጓድ ይዋጣት፣

ለነፍስያ ሳይሆን ለልጇ አሳስቧት፣
ሚበላም ሚጠጣ ምንም ቁራሽ የላት፣

የዚ አይነትም አለ እይ አንተ ባለሀብት፣
አንተ የምትበላው በቀን 9አይነት፣

ሌላው ይሰቃያል ቁራሽ ዳቦ ጠፍቶት፣
የቲምን በመርዳት አኼራን ገንባበት፣

ነቢ ተናገሩ በዛ ውድ አንደበት፣
የቲምን የረዳ ከሀተይን ያሉት፣

ካልቻልክም በእጅህ ፀጉሩን እሽለት፣
የነብዩን ትዛዝ ምትተገብርበት፣

ሀብትህንም ቢሆን በረካ ሚያደርጋት፣
ለቸገረው የቲም እጅን በመዘርጋት፣

የአኼራ ቤትን የምታድስበት፣
አላህ ይመድበን የቲም ከሚረዱት።



'' መልካም ተግባራት ምንንም አሳንሰህ አተመልከት
ወንድምህን በብሩ ፈገግታ መገናኘት አንኳ ''
ነቢዩ (ሶ,ዐ,ወ)

https://t.me/ALHidayaTv/19942