Get Mystery Box with random crypto!

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayatv — አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ
የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayatv — አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ
የሰርጥ አድራሻ: @alhidayatv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.07K
የሰርጥ መግለጫ

ኑ ተባብረን ባለን አቅም የቲሞችንና የተቸገሩ ሙስሊም ወገኖቻችንን እንርዳ
በልብስ👕👖 በገዘብ በአስዜዛ በጉልበት በሀሳብና
በተለያዩ በቤት ቁሳቁሶች መርዳት ትችላላቹ
ንግድ ባንክ
1000375043298
ሪድዋን ሙሀመድ
አባል መሆን ለምትፈልጉ
ለበለጠ መረጃ
251993632424
ወይም የቢሮ ቁጥር
251703136300
ወይም በኢቦክስ
@RidAmirsab
ሰደቃ ወጀልን ታብሳለች ረሱል (ﷺ)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-12-03 15:36:57 ውጫዊ አካላችን ጉዳት እናዳይነካው ከምንሰጋለት በበለጠ ለውስጣዊው አካላችን(ቀልባችን) ልንሰጋለት ይገባል። ለውጫዊው አካላችን ንፅህና ከምናደርገው በላይ ለውስጣዊው አካላችን ንፅህና ትጋት ልናደርግ ይገባል። ውስጣችን በጌታችን መመካት ጎድሎት ፣ምቀኝነትና ጥላቻ ቋጥሮ፣ በሃሜት እና በንቀት ተሞልቶ፤ለላይኛው አካላችን ብቻ መጨነቃችን ትልቅ ስህተት ነው።



Copy
467 viewsእንደ አበባ ፈክተሽ ወንድ ከምታፈዢ ሂጃብሽን(ኒቃብሽን) ለብሰሽ ጌታሽን ተገዢ!!!, 12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 15:36:48 አላማርርህም

ጌታዬ በየትኛው ኒዕማህ ልማረር
  ሸልመኸኝ ለግሰህ እጅ እግር
  ጌታዬ አንተን እንዳመሰግንህ
ፈጥረኸኛል ውብ ሙሉ አድርገህ
ረቢ እንድጠራህ አንደበቴን ከፍተህ
ያንተን ፀጋ እንዳይ ብርሃኔን ሰተህ
ቆይ በየትኛው ኒዕማህ ላማርርህ
ብሶቴን መግለጫ እንባዬን ለግሰህ
ነፍሴን በቁርአን አንፀህ  አድሰህ
ሰላትን የሰላም መንገድን ዘርግተህ
አልቻልኩምስልህ ሰብርን ሸልመህ
ሲከፋኝ ስናደድ ደስታን ምትሰጠኝ
መንገዴንስስትወዳንተምትመልሰኝ  በእዝነትህብዛትሳጠፋይቅር አልከኝ               
ትልቁን ስጦታ እስልምናን ሰጥተህ
የነቢ ወዳጅ እንድሆን አድርገህ
አላህዬ ብሎ ያፈረብክ የለም  ስለዚህ ጌታዬ አላማርርህም
የማይገባኝንም ስጠኝ አልልህም
ቢጠፋም ቢጎድል  አላማርርህም።
                  
                          አልሃምዱሊላህ
466 viewsእንደ አበባ ፈክተሽ ወንድ ከምታፈዢ ሂጃብሽን(ኒቃብሽን) ለብሰሽ ጌታሽን ተገዢ!!!, edited  12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 07:41:39 ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ

#ልጄ_ሆይ ፧ በዝምታየ ተፀፅቼ አላውቅም፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ከጠጣህበት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አታስገባ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ምላስክን ‘አላህ ሆይ ማረኝ ‘ ማለትን አለማምድ ለአላህ ጠያቂን የማይመልስበት ሰዓታት አሉትና፡፡

#ልጄ_ሆይ፧ ከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ከመገረም ጋር አትሳቅ; ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ሁለት ነገሮችን አታውሳ ፧ ሰዎች ወዳንተ ያደረጉትን በደልና ፣ ለሰዎች ያደረከውን መልካም ነገር፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ በጣም ጣፋጭ አትሁን ከንቀት እንዳትበላ መራራ አትሁን እንዳትተፋ ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ አትመገብ ; ከምትመገበው ለውሻ ብጥለው የተሻለ ነው ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ የአላህን ፈራቻ ንግድ አድርገህ ያዘው ; ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ ይመጣልሀል፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ጥበብ (እውቀት ) ምስኪኖችን የነገስታት ደረጃ አድርሳለች፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ አደራህን በብድር ላይ ; ብድር የቀን ውርደት የማታ ጭንቀት ነው ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ የማይረዳን ከማስረዳት ቋጥኝን ከቦታው ማንሳት ይቀላል ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ ባወከው ነገር እስከምትሰራ ያላወከውን አትማር ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ መጥፎ ጎረቤት ከከባድ ብረት በላይ ይከብዳል ;መራራ ነገሮችን ሁሉ ቀምሻለሁ ከድህነት በላይ መራራ ነገር አልቀመስኩም፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ አንድን ሰው ወንድም ለማድረግ ከፈለክ መጀመሪያ አስቆጣው በቁጣው ጊዜ ካለፍክ …ካልሆነ ተጠንቀቀው ፡፡

#ልጄ_ሆይ ፧ በሰው ቤት ውስጥ ከሆንክ አይንህን ጠብቅ፤ በስብስብ መካከል ከሆንክ ምላስክን ጠብቅ ፤ በሰላት ውስጥ ስትሆን ልብህን ጠብቅ ፡፡


የእብነ ከሲር ‘ቢዳያህ ወንኒሀያህ’ ከሚለው መፅሀፋቸው ውስጥ ከ40 በላይ የሉቅማን ምክሮች ተጠቅሰዋል፡፡ ሉቅማን ፡ ቁርዓን ውስጥ የተጠቀሰ በስሙም ምዕራፍ ያለው ፡ ነብዩ አለይሂ ሰላም ሰለሱ ”
☞አሰተሳሰቡ ሰፊ፣
☞መልካም አሳቢ፣
☞ዝምታን የሚያበዛ፣
☞አላህን የሚወድ አላህም የወደደው ፣ ☞ጥበብም የቸረው ነው ” ብለውለታል

ሉቅማን አፍሪካ ውስጥ ‘ኑባ’ የምትባል ቦታ የኖረ ሲሆን ‘ጦብሪያ’ የምትባል ቦታ እንደተቀበረ ይነገራል።

--------------------------------------
ሞት ማሠታወሠ
--------------------------------------
t.me/mame0999
--------------------------------------
295 viewsSELADIN BASET, 04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 07:41:39 የአላህ ባሮች መገለጫዎች
➪➩➪➩➪➩➪➩➪➩

❶ እርጋታና ክቡር መሆን፤ ለአላህ መተናነስ እንዲሁም ለባሮቹ በሚገባቸው ልክ መተናነስ

❷ ሶላትን - በተለይም የሌሊት ሶላቶችን - ተጠባብቆ መስገድ

❸ ከእሳት ቅጣት መፍራታቸውና መጨነቃቸው

❹ በማባከን እና በንፉግነት መካከል ላይ ሆነው ገንዘባቸውን የሚለግሱ ናቸው

❺ ከከባድ ወንጀል እና ከታላላቅ ሐጢያቶች መራቃቸው

❻ ጸያፍ ተግባራት ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች መራቅ

❼ ለአላህ ንግግር ክብር ይሰጣሉ፣ በውስጡ ያለውን መልእክትም ይቀበላሉ

❽ በዱዓ ላይ ትኩረት መስጠታቸው፣ ለአላህ መተናነሳቸው

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ከነዚህ መገለጫዎች መካከል የትኛው ከኛ ህይወት ጋር ይዛመዳል? እያንዳንዱን በራሳችን ላይ ለማምጣት መታገል ተገቢ ነው።

•════••• •••════•
ሼር JoiN & Share
https://t.me/mame0999
https://t.me/mame0999
239 viewsSELADIN BASET, 04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ