Get Mystery Box with random crypto!

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayatv — አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ
የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayatv — አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ
የሰርጥ አድራሻ: @alhidayatv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.07K
የሰርጥ መግለጫ

ኑ ተባብረን ባለን አቅም የቲሞችንና የተቸገሩ ሙስሊም ወገኖቻችንን እንርዳ
በልብስ👕👖 በገዘብ በአስዜዛ በጉልበት በሀሳብና
በተለያዩ በቤት ቁሳቁሶች መርዳት ትችላላቹ
ንግድ ባንክ
1000375043298
ሪድዋን ሙሀመድ
አባል መሆን ለምትፈልጉ
ለበለጠ መረጃ
251993632424
ወይም የቢሮ ቁጥር
251703136300
ወይም በኢቦክስ
@RidAmirsab
ሰደቃ ወጀልን ታብሳለች ረሱል (ﷺ)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-19 22:49:06
ጉዳዩ ዱባይ ደረሰ ወላሂ ይገርማል


ይህ የምታዩት ትልቅ ስክሪን ቲቪ በዱባይ አንድ ትልቅ አደባባይ ላይ የተተከለ ስክሪን ነዉ።

እና አል ሂዳያ ቲቪ ከመዘጋቱ በፊት እገዛ ሲያደርግ ከነበረዉ አብዱል ሀኪም ወንድማችን ከአንድ ከሚመለከተዉ አካል ጋር በመነጋገር እንደዚ በዚ ትልቅ ስክሪን አንድ ስቲከር ለትንሽ ሰአታት እንዲታይና እንዲለቀቅ አድርጎታል ታዲያ ይሄ በርካታ የዱባይ ነዋሪና በስደት የሚገኙ እህቶችና ወንድሞች ሲያዩት ጉዳዩ ምን ያህል እየተባባሰ እንደሄደ ነዉ የተረዱት

ፎቶዉ ዱባይ ዉስጥ በስደት ከሚገኙ ከአንድ እህታችን የተላከ።

Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ
https://t.me/HiDAYATV
267 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 17:32:47
የቀን ሰራተኞች በተሰበሰቡበት ቦታ ውድ መኪናውን አቆመና በሩን ከፍቶ ወረደ ወደ ሰዎቹ ተጠጋና
"በቀን ሀያ ፓውንድ እየተከፈለው የጉልበት ስራ መስራት የሚፈልግ ካለ አብሮኝ ይምጣ" አለ።
Mahi Mahisho

ሰራተኞቹ በዚህ ትንሽ ብር ላባቸውን ማፍሰስ፣ ጉልበታቸውን ማድቀቅ አልፈለጉም "ድህነታችንን ብሎም ስራ ማጣታችንን አይተህ በትንሽዬ ክፍያ ጉልበታችንን ለመበዝበዝ እንዴት ትሞክራለህ?! እዚህ ከተማ ዝቅተኛው የቀን ክፍያ 100 ፓውንድ ነው" ሲሉ ተናገሩ።

እሱ ግን "ከ20 ፓውንድ በላይ አልከፍልም! ምርጫው የእናንተ ነው የፈለገ መጥቶ ይስራ" አለ። ክፍያውን ከፍ እንዲያደርግላቸው ቢማፀኑትም ፈቃደኛ አልሆነምና አብዛኞቹ ሰራተኞች ትተውት ቀድመው በነበሩበት ቦታ ተቀመጡ። አምስት አዛውንቶች ግን አብረውት ሊሄዱ መኪናው አጠገብ ቆሙ። ማጣት እንደተጫጫናቸው ከፊታቸው ያሳብቃል። የእነሱን እጅ የሚጠብቁ ቤተሰቦች እንዳሏቸው ያስታውቃል። ዕድሜያቸው የገፋ አዛውንቶች ናቸው። አካፋና ዶማቸውን ይዘው ከባዱን ድህነት ሊያሸንፉ አቀርቅረው በእሺታ ተቀበሉ።

መኪናው ጉዞውን ጀመረ። አንድ ትልቅ ሱፐር ማርኬት በር ላይ ሲደርስ አቁሞ ወደ ውስጥ ዘለቀ። ለእያንዳንዳቸው ዱቄት፣ ስኳር፣ ሩዝ፣ የምግብ ዘይትና ሙሉ የቤት አስቤዛን ገዛ። በእጃቸው አንድ አንድ ሺህ ፓውንድ ሰጣቸውና "ከእኔ ጋር የነበራችሁ ሥራ አልቋል አሁን ወደ ቤታችሁ መመለስ ትችላላችሁ" አላቸው።

በድንጋጤ እንደተዋጡ ምስጋናቸውን በቅጡ ሳያደርሱ መኪናውን አስነስቶ ጉዞውን ቀጠለ።
353 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 23:29:52
ይደመጥ
========
«የፍቅረኛሞች ቀን» (Valentine's Day) የሚባለውን በተመለከተ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ቤተል ሮም (አል-ፋሩቅ) መስጅድ ያደረገው ኹጥባ!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥቂት የማይባሉ ሙስሊሞችም በዚህ ኢ-ኢስላማዊ ድርጊት እየተለከፉ ነውና ይገሰጹ ዘንድ ለሌሎችም አስተላልፉት። ምናልባት በኛ አንድት ሼር ሳቢያ ይህን ሰምቶ ከድርጊቱ የሚቆጠብ አንድ እንኳ ሙስሊም ቢኖር ትልቅ አጅር ነውና!

Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ
||
https://t.me/HiDAYATV
246 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 05:48:15 የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ [radiallahu anuhu] የአላህ መልእክተኛ [sallallahu aleyhi wasallam] እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋሎህ አለ። “ስራዎች ሁሉ የሚመዘኑት በንያ (ባሰብከው ሃሳብ) ነው። ሁሉም ሰው (የነየተው ነገር) ያሰበው ነገር አለው። ሰው ሁሉ ደግሞ (የነየተውን) ያሰበውን ያገኛል። ስደቱ ወደ አላህ እና ወደ መልእክተኛው ከሆነ፥ ስደቱ ወደ አላህ እና ወደ መልእክተኛው ይሆንለታል። ስደቱ ደግሞ ሊያገኛት ወደሚፈሊጋት አለም(ዱንያ  ወይንም ሊያገባት ወደሚፈልጋት ሴት ከሆነ፥ ስደቱ ወደተሰደተለት ምክንያት ይሆንለታል”

ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
185 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 02:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 18:43:22
አንዲት እህታችንም ኸሳዉዲ 4000ሺብር አስገብታልናለች ጀዛኩምሏሁ ኸይረን እህታችን መልካም ስራዋን አሏህ ይዉደድላትና ጀነትንም አሏህ ይወፍቃት

እህታችን ዱአ አድርጉላት እናቷ ወደ አኼራ ሂዳለች ጀነትንም እንዲወፍቃት በዱአ ያጀማአ
300 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, edited  15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 18:40:20
አንድ ኑሩ ሁሴን ሙሃመድ ከሱውይድን swededn
50 ቁርአን ተገዝቶ ለመስጊድ ይሰጥልኝ ብሎ የ10000ሺብር አስገብቶልናል ወንድማችን መልካም ስራዉን አሏህ ይዉደድለትና በተቻላቹ መጠን ዱአ አድርጉለት
307 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 16:46:28 ሞት  ዝምተኛዉ መካሪ

የሰዉ ልጅ በዚህች ምድር ወጥቶ መንከላወስ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ የሞትን ያክል ክፉ ባላንጣ አልገጠመዉም። የሞትን ፀዋን መጎጨት ከካባዉ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነባር  ልማድ ቢሆንም ለሰብአዊዉ ፍጡር ግን ሁልጊዜምና አዲስ እንደሆነበት ነዉ የሚኖረዉ። ለመሆኑ ሰዉ ሞትን የሚፈራዉ ለምንድነዉ? ይህ ጥያቄ እንደዘበት የሚነሳ ይሁንጂ መልሱግን የዋዛ እንዳልሆነ ብዙ ሰወች አይገነዘቡትም።

ለመሆኑ ሞት ምንድነዉ? ከሞተና ከህይወት አዉድ ከተሰናበተ በኋላ የእሱ ነገር እስከወዲያኛዉ ከበቃለት ማለት ነዉ? ፋይሉስ ዳግም ተዘግቶ ላይታይ ተዘግቶ ይቀራል?
አንዳድ ሰዎች የሰዉ ልጅ ከሞተ በኋላ የመነሳቱንና በስራዉ የመጠየቁን ጉዳይ ወደ ጎን በማለት ከመቃብር በላይ ስሙን የሚያስጠራበት ሲሉ ይደመጣሉ። እናም

ፅድቅና ጉነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም ።

በሚሉት በሂል ፍልስፍናቸዉ እየተንደረደሩ ለህሊናቸዉ ሲሉ መልካም ነገሮችን መፈፀም እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። እናም መልካም ነገሮችን መፈፀም የኔ ህሊናህ እርካታን ይጎናፀፋል በማልት ከዚህች አለም አክራሞታቸዉን የህይወታቸዉን ግብ በዚሁ በመቋጨት ያሳርጋሉ።

ሌሎቹ ደግሞ ለሞት መድሀኒቱ መዉለድ ነዉ። የታባቱ ሞት በልጆቼ ድል አደርገዋለዉ እኔ ብሞት በልጆቼ እጠራለሁ ላልወለደና አይኑን ባአይኑ ላላየ ብቻ ይብላኝለት በማለት ። የሁሉም ነገር መነሻና መድረሻ ወልዶ መሳምና ዘር መተካት ብቻ እንደሆነ አድርገዉ የሚያስቡ ናቸዉ። ፈላስፋዎች ሀሳቢያንና የተለያዩ ማለቂያ የሌላቸዉ ሀተታዎችና የሀሳብ ድሪቶዎች በመደረት ስለ ሞት የየበኩላቸዉን ሀሳብ ይሰጣሉ ።

ሆኖም ግን ኢስላም የሰዉ ልጅ በህይዎት መኖሩና መሞቱ ለተለያዩ አላማና ፈተና የተዘጋጁለት ክስተቶች መሆናቸዉን አስተምሯል ይህን አስመልክቶም የአለማቱ ጌታ አሏህ ሱብሀነሁ ወታአላ። እንዲህ ይለናል።


الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ

ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡
(አል ሙልክ 2)

ሪድዋን ሙሀመድ

ይቀጥላል ቻናሉን ተቀላቀሉ

Al HiDAYA MidiA The straight road ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ አል ሂዳያ ቀጥተኛዉ መንገድ
364 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 22:40:22 https://t.me/AllHidAYATv
211 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 23:41:34 በአላህ አምናችሁ፣በሱ እርግጠኛ ሆናችሁ ተኙ። እሱ በአንዲት ምሽት ብዙ ነገር ይቀይራል። ብዙ ብዙ።

ችግራችሁ ተፈትቶ የምታድሩበት ምሽት ይሁን።
90 viewsእንደ አበባ ፈክተሽ ወንድ ከምታፈዢ ሂጃብሽን(ኒቃብሽን) ለብሰሽ ጌታሽን ተገዢ!!, 20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 23:30:18 የመልካም ሚስት ስብእና ።
•-•◈◉❒{ }❒◉◈•-•

____
አል ወሉድ።

(አል
ወሉድ) ማለት ብዙ የምትወልድ ማለት ነዉ። ይህ ለሴት ልጅ የተወደደ የተመሰገነ መልካም የሆነ መገለጫ እና መልካም ሴት ለመባል አንዱ ምክነመያት ነዉ።

ነገር ግን
ንዲት ሴት በመዉለድ ችግር ከተፈተነች ወይም በሽታ ከገጠማት ይህ ምንም አይጎዳትም ምክኒያቱም ይህ በእሷ ጥፋት ማጓደል ወይም ላለ መዉለድ ባደረገቺዉ ጥረት የተከሰተ ነገር ስላልሆነ ነዉ። በመሆኑንም አሏህ በዚህ ጉዳይ አይተሳስባትም። ይህ ነገር መከሰቱ እሷን አይጎዳትም ፤ መልካም ከመሆኗም ጋ ፍፁም የሚጋጭ አይደለም።

ሆኖም መ
ዉለድ እየቻለች ልጆችን የማትፈልግ ከሆነ ፤ እንዲሁም ፅንስን የምታቋርጥ ከሆነ ይህ በእሷ ላይ ጉዳት ያመጣል። ምክኒያቱም ረሱል ﷺ እንዲህ ብዋል።

ፍቃሪ እና ወላድ የሆነችን ሴት አግቡ፤ ምክኒያቱም እኔ የቂያማ እለት ከሌሎች ህዝቦች ጋር እፎካከርባቹሀለሁና።

ስለሆነም
አንዲት ሚስት ልጆችን ለመዉለድ ጥረት ማድረግና ለዚህም የሚያበቁ ሰበቦችንም ማድረስ ይጠበቅባታል፤ እንዲሁም ልጆችን ኮትኩቶ ማሳደግ ፤ መልካም ባሀሪ አንፃ ማብቃት ፤ መጠበቅና መንከባከብ ላይ ከፍተኛ ጥረትና ትግል ማድረግ ይገባታል። ይህን ስትፈፅም ከአሏህ የምታገኘዉን ምንዳ እያሰበች መሆን አለበት ማሀበረሰቡ ዉስጥ መልካም የሆኑ ልጆች ፤ የለዉጥ አርአያ የሆኑ አስተካካይ ዱአቶች ተጣሪዎች እንዲፈጠሩ ምክኒያት ለመሆን አቅዳ መነሳት ይገባታል ። ይህንን አላማ ወደ ትዳር ከገባችበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ግምት ዉስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።
እንዲህ በማለት በራሷና በአሏህ መካከል ቃል ትግባ።

ምናልባ
ትም አሏህ የቅን ጎዳና መሪ ወይም የሙስሊም ሙሁራንና ልሂቃን ወይም ወደ መልካም የሚጣሩ ዱአት በሆኑ ልጆች ያከብረኝና ያልቀኝ ይሆናል።

በዚህም መ
ልካምና ታላቅ እሳቤዋ እንዲሁም ልጆቿን በአግባቡ መንከባከቧና መጠበቋ ለዚህም በሰጠችዉ ትኩረት ታላቅ ምንዳ ይፃፍላታል።

ወን
ድም ሪድዋን ሙሀመድ

ኢንሻ አሏህ በቀጣዩ ክፍላችን
{አል ሙዋቲየቱ} አመለ መጥፎ የተሰኘዉን ሙሉ ዝርዝሩን ይዘንላቹህ እንቀሮባለን ዮቀጥላል ቻናሉን ተቀላቀሉ
https://t.me/HiDAYATV
https://t.me/HiDAYATV
367 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ