2022-12-03 15:37:07
ወንድሜዋ ፂምህን አሣድግ!!
ጺምን (ጢም ) ማሳደግ የነብያት፣ የሶሃቦችና የቀደምት የኢስላም አባቶች የዲናቸው (የእምነታቸው) አንዱ አካል ነው፡፡ ፂም ማሳደግ ዋጂብ ለመሆኑ መረጃ ከቁራን፤ከሐዲስ እና የኡለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) አለ፡፡
1) ቁራናዊ መረጃ
قال الله تعالى (( قال يبنؤم لا تأخذ بلحيتي ولا برأسي ))
قال العلامة الشنقيطي في أضواء البيان ( ج 4 ص 506 ) عند تفسير هذه الآية
(( فهي دليل قرآني على إعفاء اللحية وعدم حلقها ) اهـ .
"የእናቴ ልጅ ሆይ ጢሜንም ራሴንም አትያዝ" ኢማም ሙሐመድ አሚን አሽ-ሺንቂጢ በዚህ አያ ማብራሪያቸው ከሱረቱ-ጣሃ ‹አድዋዑል በያን› ላይ እንዲህ ይላል:-
"ይህ አያ ጺምን ማሳደግ ባለበት መተውና አለመላጨት ዋጂብ ለመሆኑ ቁራናዊ መረጃ ነው አለ"
2) ከሐዲስ መረጃ
"عن نافع عن ابن عمر عن النبي صلى الله عليه وسلم قال «خالفوا المشركين وفروا اللحى وأحفوا الشوارب » متفق عليه
“ አጋሪዎችን ተቃረኗቸው፤ ጺማችሁን አወፍሩት (ባለመላጨት አብዙት)፣ ከአፍንጫ ስር ያለውን (ቀድሞቀመስ) ደግሞ አሳጥሩት፡፡
عن زيد بن أرقم رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «من لم يأخذ من شاربه فليس منا» خرجه الترمذي في سننه وصححه الشيخ الألباني
ኢማም ቲርሚዚ በዘገቡት ሀዲስ ደግሞ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ይላሉ፡
“ ከአፍንጫው ስር ያለውን ጸጉር ያላሳጠረ ከእኛ አይደለም፡፡ ”
3) በኡለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) ደግሞ
قال العلامة الكبير والحافظ الشهير أبو محمد ابن حزم: (اتفق العلماء على أن قص الشارب وإعفاء اللحية فرض) ا.هـ.مراتب الإجماع
ታላቁ ኢማም አቡ ሙሐመድ ቢን ሐዝም- ኢብኑ ሐዝም በመባል የሚታወቁት ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ -"የቀደምት ኡለማዎች ተስማምቷል ፂም ማሳደግና ዋጂብ በሞሆኑና ከአፍንጫው ስር ያለውን ጸጉር ማሳጠር ግዴታ በመሆኑ ላይ።"
አሁን ደግሞ ፂም ማሳደግን በተመለከተ ታላላቅ የሱና ኡለማዎች ከነበሩት የስጧቸው ፈተዋዎች እንመልከት
ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ
https://t.me/tewihd/4780
ሼኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒ ረሒመሁላህ
https://t.me/tewihd/4777
ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አልዋዲዒ ረሒመሁላህ
https://t.me/tewihd/4781
ሸይኽ መሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል‐ዑሰይሚን ረሒመሁላህ
https://t.me/tewihd/4782
ሸይኽ ሷሊህ ፈውዛን አልፈውዛን
https://t.me/tewihd/4779
ሸይኽ ሉሀይዳን
https://t.me/tewihd/4782
https://telegram.me/tewihd
598 viewsእንደ አበባ ፈክተሽ ወንድ ከምታፈዢ ሂጃብሽን(ኒቃብሽን) ለብሰሽ ጌታሽን ተገዢ!!!, 12:37