Get Mystery Box with random crypto!

«              ጭንጎ ላይ ምን ተፈጠረ ? በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን በአኔሌሞ ወረዳ በቀ | አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

«              ጭንጎ ላይ ምን ተፈጠረ ?

በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን በአኔሌሞ ወረዳ በቀን 29/04/2015 ከንጋቱ 11:30 የአከባቢው ሙስሊም የዘውትር የንጋት ሷላቱን ለመስገድ ወደ መስጂድ እያመራ ባለበት ወቅት ከበንደሊቾ ፈቴና ከበንደሊቾ ቆንቦጣ የተወጣጡ ከ200 በላይ የምልቁ ፅንፈኘ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑ ግለሰቦች በህብረት ተሰባስበው የተለያዩ ለጥቃት የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን/ቁሳቁሶችን ማለትም ጦር ፣ ገሶ፣ ገጀራ እንዲሁም ድንጋይ በመታጠቅ ቤትለቤት እየዞሩ ምንም ባልተዘጋጁ እና ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ "ኢየሱስን ካልተቀበላችሁ እንገድላችኋለን ወይም ሀዲያ ዞን ውስጥ መኖር አትችሉም በማለት ከፍተኛ ድብደባ እና ጉዳት አድርሰዋል።
በዚህም ምክንያት ከ60(ስልሳ በላይ) ሙስሊሞች ከባድ እና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን በመሳት (comma) ውስጥ ያሉና ወራቤ ኮንፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በአከባቢው በሚገኝ ጤና ጣቢያ እርዳታ ተደርጎላቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ፅንፈኛ ሀይሎች በሴቶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ እና ማስፈራራት አልፎም አንቆ በመያዝ እምነትሽን ካልቀየርሽ እንጨርስሻለን እስከማለት የደረሰ በደል አድርሰዋል።
በመስጂዶችም ላይ የድንጋይ እሩምታ የተፈፀመባቸው። ይህ በንዲህ እንዳለ ከተደወለላት  ከሰኣታት ቦኃላ አከባቢው የደረሰው የወረዳው የፖሊስ ሀይል በጉዳዩ እጁ እንዳለበት በሚያሳብቅ መልኩ አንድም ወንጀለኛ በሰአቱ ተሯሩጦ ለመያዝ ፍላጎት አለሳየም። ይባስ ብሎ የተጎዱትንም ወደ ህክምና ተቋም ለማድረስ ከፍተኛ ዳተኝነት አሳይቷል። በተጨማሪም ከፖሊስ ስነምግባር በማይጠበቅ መልኩ
የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል እንዲያዳርሱ ስመፀኗቸው "ስትፈልግ በጭንቅላትህ አዝለሀው ዙር" የሚል እጅግ ሰቅጣጭ መልስ ሲሰጡ ነበር።

➞ ለመሆኑ ይህ የተጠና እና የተቀናጀ የሐዲያ ሙስሊሞች ሰቆቃ ማብቂያው መች ይሆን

#ፍትህ ለሐዲያ ሙስሊሞች»
ሌሎች መረጃዎች እንዲደርሳቹ ከጸለጋቹ ቻናሉን ተቀላቀሉ
https://t.me/HiDAYATV
https://t.me/HiDAYATV