Get Mystery Box with random crypto!

ዉዱ ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ኸይር ስራዉን አሏህ ይዉደድለትና ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ሁልጊ | አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ 0993632424//0703136300አዲስ አበባ

ዉዱ ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ኸይር ስራዉን አሏህ ይዉደድለትና

ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ሁልጊዜ በኸይርስራዉ ነዉ የሚታወቀዉ

የአል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ ዋና አሚር ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ዛሬም እንደተለመደዉ የማይታሰብ ትልቅ ኸይር ነገር ሰራ

ሁላችንም እንደምናዉቀዉ ካሁን በፊት ለዚ ኸይር ስራ ብሎ ከዉጭ የተላከለትን አይፎን ፎርቲን ፕሮማክስ ስልክ ሰዎች እየተራቡ እኔ የቅንጡ ስልክና ዉድ ስልክ ምን ይሰራልኛል በማለትና የተላከለትን ስልክ በመሸጥ ሌላም ከሰራበት ገዘብ ላይ በመጨመር 12 አቅመ ደካማ እናቶችን ስራ ማሲያዙና ወርሀዊ የቤት አስቤዛ ማስገባቱ ይታወቃል እንዲዲሁም ለ2መስጂዶችና መድረሳዎች ከ4600በላይ ቁርአንና ከ3230በላይ ኑራንያ ማስገባቱም ይታወቃል

ታዳ ይህ አሚራችንና ወንድማችን ዛሬም እንደተለመደዉ ለበረካ መስጂድ 1200ቁርአንና 400ኑራንያ ገዝቶ ገቢ ማድረጉን ልናሳዉቃቹ እንፈልጋለን

ወንድማችን ሪድዋን ሙሀመድ ኸይር ስራዉን አሏህ ይዉደድለትና አል ሂዳያ ጀማአን ከመሰረተበት ሰአትና ቀን ጀምሮ ይሰራል ተብሎ ከሚታሰበዉ በላይ እጅግ በጣም ትልቅ ኸይር ስራ እየሰራ ይገኛል ታዳ ለዚህ ምርጥና ለጋሽ ወንድሜችን ምን ብንሸልመዉና ምን ብናደርግለት ይገባዋል ትላላቹ

ታዳ ይሄንን ስራዉን ሶሻል ሚዲያ ላይ ኸይር ስራዉን አሏህጂ ሰዉ እንዲያዉቅ አልፈለገም ነበረ ነገር ግን እኔ የአል ሂዳያ ምክትል አሚር ኢክራም ሰኢድ ሌሎች ገዘባቸዉን ለሚቋጥሩ ሰዎች መነሳሻ ይሆን ዘንድ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሼር ማድረጌን ላሳዉቃቹ እፈልጋለዉ

ነገ ጥለህዉ ለምትሞት ገዘብ ዛሬ ብትሳሳ ከቱ ልፋትጂ ስኬት የለዉም ያደም ልጅ ሆይ ገዘብህን አጠቃቀሙን ከቻልክበት ጀነት ያስገባሀል ካልቻልክበት ግን ጀሀነም ያስገባሀል

https://t.me/ALHidayaTv/19884