2023-01-04 06:39:37
በእውነት በቅድስና በምሳሌነት በመሰጠት በትጋት ደቀመዝሙር በማፍራት እናገልግል ።
በዚህ ዘመን ያለው ግርግር በእጅጉ አስፈሪ ነው። አማኙ ማህበረሰብ አብሮ ያለው ትውልድ መልክ መለየት የቻለ አይመስልም ። ትውልዱ የበረከት ፣ የተዓምራት ፣ የኮንፍራንስና የሜጋ ቸርቾች አሳደጅ ሆኖአል። አማኙ የተያዘበት የሚማርበት አባል የሆነበት ቤ/ክ የለውም ። ዘመኑ ሁሉም አባል የሁሉም ቤተ ክርስቲያን ሁሉም ቤተ ክርስቲያን የሁሉም አባል ነው የተባለ የሚመስልበት ነው።
ጋጋታው የተአምራት እና በረከት ተኮር እንጂ ህይወት ተኮር አይደለም።
ብዙዎች ወደ ጌታ ከመጡ በኃላ በቤ/ክርስቲያን ተገኝት በየሳምንቱ ማምለክ እንጂ ጥሪው ደቀ መዝሙር የመሆን ጥሪ እንደሆነ የገባቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም አንድ አማኝ ጌታን የግል አዳኙ አድርጎ በሚቀበልበት ጊዜ የጌታ ደቀ መዝሙር ሊሆን ጭምር መጠራቱን ማወቅ ይኖርበታል፡፡
ደቀ መዝሙር ማለት ምን ማለት ነው ?
ደቀ መዝሙር ማለት የጌታ ተከታይ መሆን ማለት ሲሆን ደቀ መዝሙርነት የርሱ ተማሪ ሆኖ ጌታን ለመምሰል በጌታ ህይወት የመቅረፅ ሂደት እንጂ በቤተክርስቲያን በአምልኮ፣ በዝማሬ በአገልግሎት ሥም ግርግር ማብዛት አይደለም።፡፡ (ማቴ 28፡-18-21 ማቴ 4፡-19 ማቴ 11፡-28)
ዓላማውም:-
1ኛ,ጌታን ማወቅ ! በጌታ ህይወት መቅረፅ !
2ኛ, ጌታን መስሎ በእርሱ ህይወት መገኘት !
3ኛ, ያወቁት ጌታ መግለጥ /የጌታ ህያው ምስክር መሆን/ነው !
ይህ እውን ሲሆን የክርስቶስን ህይወት ለሌሎች የማካፈል አገልግሎት ይበዛልናል ።ጌታ እርሱን የሚከተሉትን ደቀ መዛሙርት 24 ሰዓት በህይወታቸው፤ በኑሮአቸው በአገልግሎታቸው የሚከተላቸው በእርሱ ህይወት ሊቀርፃቸው ነው፡፡ እርሱን እንዲመስሉ እርሱ ተልዕኮውን ፈጽሞ ሲሄድ በርሱ ሕይወት እንዲገኙ ነው ።
ጌታ ደቀመዛሙርትን የሚከታተልበት ዓላማ በሕይወታቸው የለውጥ ሂደትን ማካሄድ ነው። ስለዚህም ክርስቶስን እከታተላለሁ የሚል ሰው በእውቀቱ፤በሕይወቱ፤ በኑሮው የለውጥ ሂደት መካሄዱን ማረጋገጥ አለበት፡፡
አለበለዚያ የቤተክርስቲያን ተሳታፊ አባል እንጂ ደቀመዝሙር ሊሆን አይችልም። የደቀ መዝሙር ሕይወት እውቀቱ ከተግባራዊ ሕይወቱ ጋር የተጣጣመለትና ያወቀውን የሚኖር የኖረውንም የሚገልጥ ነው ። ዛሬ ላይ የክርስቶስ የሕይወት መዓዛ ሽታው ከቤ/ክ ለምን ጠፋ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ ? እውነታው ደቀ መዝሙር ያልሆኑ አገልጋዮች ፣ ደቀ መዝሙር ያልሆኑ መሪዎች፣ደቀ መዝሙር ያልሆኑ ዘማሪዎች መድረኩን ሞሉት ። ደቀመዝሙር በፊቱ ጌታን ሞዴል አድርጎ :-
1.ደቀ መዝሙር ከጌታው የሚማርና በመንፈሳዊ እውቀት የሚያድግ ነው ! ማደጉ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ
2. ደቀ መዝሙር ወደ ትክክለኛ የመንፈሳዊ ሕይወት የእድገት አቅጣጫ የገባ ነው ! በቃሉ ሥር ሰዶ ለማደግ
3. ደቀ መዝሙር ለዕድገት የሚያስፈልጉ ነገሮችን እንደሚሟሉለት ከጌታ ጋር የጠበቀ ሕብረት ያደረጋል ! የወይኑ ግንድና ቅርንጫፉ ያላቸውን አንድነት ያህል !
4. በዘመኑ ሁሉ የጌታ ተማሪ ሆኖ በእርሱ ሕይወት በመቅረፅ ወደ ሙላቱ ልክ ለመድረስ ዘመኑን ሁሉ የሚገሰግስ ነው
5. ግቡም የጌታ ሕይወት በሙላት መጎናፀፍ ነው !ዘወትር ቃሉ ከሕይወቱ ጋር እንዲዋሃድ ይተጋል !
6. ደቀ መዝሙር እንደጌታው የሚሆን የሚኖረውን የሚናገር የሚናገረውን የሚናገር ነው !
ስለዚህም ደቀ መዝሙር
1. ዘወትር የቃሉን ወተት የሚመኝ ነው !
2. የፅድቅና የእውነት ርሀብ ያለበት ነው !
3. በመንፈስ ቅዱሰ የሚመራ ለቃሉም እውነት የተገዛ ነው !
4. ከምንም በፊት ለእግዚአብሔር ቅድሚያ የሚሰጥና ከእርሱ ጋር የጠበቀ የፀሎት ህብረት ያለው ነው !
5. በተሰጠ አዲስ ሕይወት በብስለት ለማደግ ዕለት ዕለት የሚተጋ ነው !
6.
የጌታ ደቀ መዝሙር መታወቂያው ፍቅር ነው ዮሐ 13፡-35 ዮሐ 15፡-10 የጌታ *የጌታን አላማ አላማው ያደረገ ነው !
7.ደቀ መዝሙር መስዋዕትነት ለመክፈል የቆረጠ የተዘጋጀ ሕይወት ያለው ነው !
8.ደቀ መዝሙር መስቀሉን ዕለት ዕለት ተሸክሞ ጌታን ለመከተል የቆረጠ ነው! (ሉቃ 9፡23)
9.ደቀ መዝሙር ለጌታው እስከ ሞት ድረስ የታመነ ነው !
እስቲ እንጠያየቅ !
1ኛ, ዛሬ ቤተክርስቲያን የራሷ አባላት እንጂ እውነተኛ የጌታ ደቀመዛሙርት መፍለቂያ ናትን ?
2ኛ, ቤተ ክርስቲያን ቆም ብላ እራሷን ማየት አለባት ጌታ የሚደስትባት የአባላቶቿን ብዛት ስታሳየው ወይስ እውነተኛ ደቀመዝሙር በማፍራቷ ?
3. የጌታን ሞዴልነት የተከተለ እወውነተኛ አገልግሎት ለመፈፀም በእያንዳንዱ አማኝ
ሕይወት የለውጥ ሂደት የማካሄድ ከገልግሎት ሊኖረን አይገባምን ?
የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ችግር ምንጩ
እውነትኛ ደቀመዝሙር ያልሆኑ አባላት በቤተክርስቲያን መከማቸታቸውና መሪ አገልጋይ ዲያቆን ዘማሪ አብዛኛው ማለት
በሚቻልበት ሁኔታ ከአባላቶቿ የተመለመሉ እንጂ ከእውነተኛ ደቀመዝሙርነት የወጡ አለመሆናቸው ነው ።
ምን እናድርግ ?
በቅድሚያ እኛ እውነተኛ የጌታ ደቀ መዝሙር መሆናችንን እናረጋግጥ ።
ከዚያም የቤ/ክ አባላትን እውነተኛ
ደቀመዝሙር እናድርግ ።
በሕዝቡ ሕይወት ጌታ እንዲነግስ እንዲገለጥ እንዲከብር እናገልግል
እንጂ እኛ አንንገስ ፣ ጌታን እናክብር እንጂ እኛ አንክበር ፣ ሕዝቡን የከበረውን መንፈሳዊ ሕይወት እንዲጎናጸፍ እንጂ ለጥቅም አናገልግል ። በእውነት በቅድስና በምሳሌነት በመሰጠት በትጋት ብዙ ፍሬ በማፍራት ጌታን የሚያስደስት አገልግሎት እናገልግል ። ተባረኩልኝ !
2 views03:39