2022-11-27 19:48:19
ፈጥናችሁ ወደ ሚሻለው ኪዳን ተሻገሩ !
ክፍል ስድስት
1ኛ ,መቅደሱ ተቀይሮአል !
" የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።"
(1ኛቆሮ 3:-16-17 )
2ኛ, ታቦቱ ተቀይሮአል !
" እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን።"(2ኛቆሮንቶስ 3:-3-4)
" ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር።"
(ወደ ዕብራውያን 8:7)
" አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል።"(ወደ ዕብራውያን 8:13)
3ኛ, ደሙ ተቀይሮአል !
" የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።"(ዕብራውያን 9:12)
" ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።"(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7)
4ኛ , ካህናቱ ተቀይረዋል !
አሁን በክህነት የሚያገለግለው የሌዊ ነገድ ሳይሆኑ በክርስቶስ አምነው የዳኑ ሁሉ ናቸው :: ሊቀ ካህኑም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ::
" እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤"(1ኛ የጴጥሮስ 2:9)
" ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።
"(ወደ ዕብራውያን 7:28)
5ኛ, ሕግ በጸጋ ተተክቶአል !
" አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤"(ሮሜ 3:-21-22)
6ኛ, ፊተኛው ኪዳን የተባለው:-
በብሉይ ኪዳን የተገለጸው በሲና ተራራ ለሙሴ የተሰጠው የመጽሐፍ ቅዱሱ ታቦት ነው። በውስጡ ሦስት ነገሮች አሉበት፡፡ በ(ዕብ.9:-1-10) አንብቡ፡፡
1ኛ- ሕጉ የተፃፈበት ጽላት
2ኛ- የለመለመችው የአሮን በትር
3ኛ- እስራኤላውያን በምድረ-በዳ የበሉት መና ያለባት መሶበ-ወርቅ ናቸው፡፡ ፊተኛው ኪዳን የአዲሱ ኪዳን ጥላ ነው።
" ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።"
(ወደ ዕብራውያን 7:18-19)
7ኛ,የአዲሱ ኪዳን ደግሞ :-
1ኛ, ቤተ መቅደሱ አማኙ እራሱ ነው (1ኛቆሮ 3:-16)
2ኛ, የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ አካላችን ነው (1ኛቆሮ 6:-19)
3ኛ, ሕጉ የተጻፈበት ጽላት ልባችን(2ኛቆሮ3:-3,ዕብ 8:-10)
4ኛ, የጸጋው የመለኮት ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው(ዮሐ1
:-1 , 14 )
8ኛ, አስተማማኝ መለኮታዊ ዋስትና የተሰጠውን አዲስ ኪዳን ተቀበሉ :-
" እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።"
(ወደ ዕብራውያን 7:22)
9ኛ, ኢየሱስ በሞት ሊሻር የማይችል ክህነት አለው :-
ሞት ሊሽረው የሚችልው የሰው ልጆች ክህነት ኪዳናዊ ዋስትና የለውም ። "እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤"(ዕብራውያን 7:-23-24)
10ኛ, ፍጹም የሆነው ዘላለማዊ ካህን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ተሾሞአል :-
" ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።"(ወደ ዕብራውያን 7:28)
11ኛ, ፊተኛው ኪዳን ለሁለተኛው አዲስ ኪዳን ስፍራውን ለቆዋል ! አርጅቶአልና ። የብሉይ የጥላ ኪዳን የአዲሱ የአካሉ ምስክር ብቻ ነው :-
" ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር።"(ወደ ዕብራውያን 8:7)
" አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል።"(ወደ ዕብራውያን 8:13)
12ኛ, ከአብ ጋር መታረቂያው መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው:-
" ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:18) " አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5)
13ኛ, ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢያታችንን ወስዶ የርሱን ጽድቅ ሰጥቶ አድኖናልና :-
" እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።
"(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21)
14ኛ, የብሉይ ኪዳን የሲናው ታቦት ለአዲስ ኪዳን ሕያው ታቦት ምሳሌ ብቻ ነው ። በ( ዕብራውያን 9:1 - 10)
ሐዋርያ ጳውሎስ ስለ ታቦቱ ሰፊ ትንታኔ ከሰጠ በኃላ :- በ(ዕብራውያን 9:9-10)" ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥"ይላል።
15ኛ,የብሉይ ኪዳን የሲናው ታቦት እና ስርዓቶቹ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና :-
" ....እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና "(ዕብራውያን 9:9 )
16ኛ, እነዚህ ስርዓቶች የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም።"(ዕብራውያን 9:10 )
17, ሕሊናችንን ፈጽሞ ከሞተ ሥራ ሊያነጻ የሚችል የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ነው :-
" የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?" (ዕብራውያን 9:-13-14)
" ..... የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።"(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7)
18ኛ,ኃጢያታችንን ወስዶ በመስቀል ላይ ጠርቆ ዳግም ላያስበው ከመንገድ አስወግዶታል :-
" በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2:14)
16 views16:48