2022-09-07 05:39:51
#በክርስቶስ_ኢየሱስ_በማመናችሁ_ብቻ_እንኳን_ደስ_አላችሁ_!!
“ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
— ሮሜ 11፥36
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳንም የጌታ ሆናችሁ ! ይህ ሁሉ ሆኖላችኃልና !
1.በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ የእግዚአብሄር ልጆች ናችሁ ።
“ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤”
— ዮሐንስ 1፥12
2. በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ የእግዚአብሄር ፅድቅ ናችሁ።
“እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥21
3. እናንተ የክርስቶስ ኢየሱስ ምስክር ናችሁ ።
“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”
— ሐዋርያት 1፥8
4. እናንተ የኢየሱስ የክርስቶስ ልብ አላችሁ።
“እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥16
5. እናንተ የምድርን ጣዕም የምትቀይሩ ጨው ናችሁ።
“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።”
— ማቴዎስ 5፥13
6. እናንተ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ናችሁ።
“ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥17
7.ከድቅድቅ ጭለማ ወደ ሚደነቅ ብረሃን ተጠርታችኃል ።
“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9
8.የንጉሱ ካህናት ሆናችኃል ።
"የተመረጣችሁ ትውልድ የንጉስ ካህን ቅዱስ ህዝብ ለርስቱ የተለያችሁ ወገን ምህረትን ያገኛችሁ ናችሁ።"
- 1ጴጥ 2፡9
9. እናንተ የእግዚአብሄር መንፈስ ማደሪያ ቤተ መቅደሱ ናችሁ።
“ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።”
— 1ኛቆሮ3፡16-17
10. የእናንተ ሀገር በሰማይ ነው።
“እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤”
— ፊልጵስዩስ 3፥20
11. በአለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ይበልጣል።
“ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።”— 1ኛ ዮሐንስ 4፥4
12. እናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁ።
“እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥27
13. ወደ አብ መግባትን አግኝችላችኃል።
“በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።”
— ኤፌሶን 2፥18
14. በሰማያዊ ስፍራ ተቀምጣችኃል።
“... በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።”
— ኤፌሶን 2፥6-7
15.ለፅድቅ ከክርስቶስ ጋር በህይወት ተነስታችኃል።
"ለኃጢያት ሞታችሁ ለፅድቅ ከክርስቶስ ጋር በህይወት ተነስታችኃል።"
-ሮሜ6፡8 -ቄላ3፡3
16. እናንተ የእግዚአብሄር ምርጥ ናችሁ።
“ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።”
— ኤፌሶን 1፥4
17.ብፁዓን ናችሁ።
“ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።”
— ማቴዎስ 5፥11
18.የዓለም ብርሃን ናችሁ።
“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።”
— ማቴዎስ 5፥14
19.የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳኑ ምስክሮች ናችሁ።
“እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።”
— ሉቃስ 24፥48 -ማቴ 28:-18-20
20. የጌታ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ ።
“ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤”
— ዮሐንስ 8፥31
21.በክርስቶስ ንጹሐን ናችሁ።
“እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤”
— ዮሐንስ 15፥3 — ዮሐንስ 13፥10
22.የኪዳን ልጆች ናችሁ።
“እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።”
— ሐዋርያት 3፥25
23.የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ።
“በእነርሱም መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ።”
— ሮሜ 1፥6
24.ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ።
“... ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ።”
— ሮሜ 6፥16
25.የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ።
“የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥9
26.በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና።
“በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤”
— ገላትያ 3፥26
27.በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።
“አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።”
— ገላትያ 3፥28
28.የተስፋውም ቃል ወራሾች ሆናችኃል።
“እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።”
— ገላትያ 3፥29
29.የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ።
“እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።”
— ኤፌሶን 2፥19
30.ከጭለማው አገዛዝ አምልጣችኃል ።
“ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤”
— ኤፌሶን 5፥8
31.እግዚአብሔር ምስክሮች ሆናችኃል።
“.....እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 2፥10
32. የብርሃን ልጆች ሆናችኃል።
“ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥5
33.አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ሆናችኃል።
“እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥10
34. አሸናፊዎች ተደርጋችኃል።
“ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥4
35. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።
“... ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥11
1 viewedited 02:39