Get Mystery Box with random crypto!

#ቁርጥራጭ ሀሳቦች በየቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yetisolomon — #ቁርጥራጭ ሀሳቦች በየቲ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yetisolomon — #ቁርጥራጭ ሀሳቦች በየቲ
የሰርጥ አድራሻ: @yetisolomon
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 895
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የተለያዩ ፅሁፎችን ፣የመፅሀፍ ጥቆማዎች ፣ ቁርጥራጭ ሀሳቦች ፣ በንባብና በመፅሀፍት ዙሪያ እንፅፋለን ፣እናጋራለን ፣ የተለያዩ ሀሳቦችን እናሸራሽራለን !

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-01 23:35:02
680 views20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 22:42:39 አንድ መጠጥ ቤት አንድ ፀይም ወጣት ቁጭ ብሎ እየጠጣ ይዝናናል ።ከዳንሱ መድረክ ላይ የአፍሪካዊ ጥቁር ገፅታ ያላቸው ጥንዶች ይደንሳሉ ድንገት አንድ ነጭ መጣና እንስቷን ከአጋሯ በሀይል አላቆ መደነስ ይጀምራል ። የተቀማው ወጣት ቃል ሳይተነፍስ ወደ ወንበሩ ይመለሳል ጠይሙ ወጣት ግን ወደ መደነሻው ተንደርድሮ ነጩን በቦክስ ያጓነዋል ይሄን ነጩ ያወጣው ቃል አንዲት ነበር " ኢትዮጵያዊ ነህ?" (በውቀቱ ስዮም ፕሮፌሰርን መስፍን የህይወት ታሪክ ሲቀነጭብ ከሰማሁት ።)

ኢትዮጵያዊነት አልበገር ባይነት ለነጭ አለማጓብደድ እንደሆነ ለአለም ያሳዩን ከኛ አልፎ ጥቁር ህዝቦችን ሁላ የሚኮራ ታላቅ ተጋድሎ ያደረጉ ጀግኖች አባቶቻችን ያቆዩልን የነፃነት ችቦ ስሙ "ዓድዋ " ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን ፣ክብር ህይወታቸውን ሰጥተው ላስከበሩን አባቶች ፣ክብር ለመሪው አፄ ሚኒልክ ፣ክብር ከስንቅ እስከ ወኔ ያስታጥቁ ለነበሩ እናቶች --- ሞታችሁ ኩራት ሆኖናልና ስንዘክራችሁ እንኖራለን!!!!!



#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_126
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia
623 views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 15:42:11
501 views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 15:42:04 ሁሉን ጠርጣሪ የስብዕና ህመም
(Paranoid Personality Disorder)
==========================
የፓራኖይድ ስብዕና ህመም ( ሁሉን ሰው የመጠራጠርና ያለማመን) የስብዕና ህመም በስብዕና ህመሞች ስር ከመጀመርያው ምድብ የሚመደብ ሲሆን ታማሚዎቹ ላይ በዋነኝነትም የሚታየው ሰዎች እንደሚበዘብዙአቸው እንደሚጎዷቸውና እንደሚያተልሏቸው የሚያስቡና በዚህም ምክንያት ማንንም ሰው ያለማመንና መጠራጠር ነው።

ምን አይነት ምልክት ያሳያሉ?
==================
-እነዚህ ሰዎች ሌሎችን ሲጠራጠሩና ታማኝ እንዳልሆኑ ሲናገሩ ጥቂት ወይም ምንም ማስረጃ አይኖራቸውም።
-ብዙ ጊዜም የሚሰማቸው ጥልቅ የሆነና ሊቃና በማይችል ሁናቴ በሌሎች ሰዎች እንደተጎዱ የሚያስቡ ሲሆን ለዚህም ምንም ዓይነት ማስረጃ አይኖራቸውም።
ከዚህ በተጨማሪ የሚከተሉት ምልክቶች ይኖሯቸዋል
-በጓደኞቻቸው/ባልደረባዎቻቸው ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ጥርጣሬ
-ሌሎች ሰዎች ዕምነት ሲያሳዩአቸው የሚደነቁ ቢሆንም ሊያምኗቸው አይችሉም
-የሆነ ችግር ውስጥ ሲገቡ በጓደኞቻቸው/በባልደረቦቻቸው
በደረሰባቸው ጉዳት/መተው እንደሆነ ያስባሉ
-ሰውን ከቀረቡ የቀረቧቸው ሰዎች የነሱን መረጃ በመውሰድ /በመጠቀም ይጎዱናል ከሚል መነሾ መቅረብ አይፈልጉም
-ስለራሳቸው ጥያቄ ከሰዎች ቢነሳላቸው "ይሄ የማንም ጉዳይ" አይደለም ከሚል እሳቤ ምንም አይነት መረጃ አያወጡም
-እነዚህ ሰዎች ቂመኞች ሲሆኑ የሰደባቸውን: የጎዳቸውንና የናቃቸው የመሰላቸውን ሰው ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አይሆኑም
-የትዳር አጋራቸውን/የፍቅር ጓደኛቸውን ያለምንም ማስረጃ ይጠራጠራሉ
-አንዳንድ ጊዜ ግትርነት ከሌሎች ጋር ያለመተባበርና ነቀፌታን ያለመቀበል ይታይባቸዋል
-እራሳቸው በፈጠሩት ክፍተት ሌሎቹን ሲወነጅሉ ይታያሉ
አጋላጭ ሁኔታዎች
============
በቤተሰብ የስኪዞፍሬኒያ ህመም/Schizophrenia/
Delusional disorder/persecutory type ያለበት ቤተሰብ ያላቸው ልጆችበተለዬ ሁኔታ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ

ህክምና ይኖረዋል?
============
ይሄ ህመም ያላቸው ሰዎች ባብዛኛው የህክምና እርዳታ ሲፈልጉ አይታይም። ነገር ግን የትዳር አጋሮቻቸውና ቀጣሪዎቻቸው ወደ ህክምና ሲያመጧቸው ይስተዋላል።
1. ሳይኮቴራፒ (psychotherapy)
ለዚህ ህመም በግለሰብ ደረጃ የሚሰጥ (ታካሚውና የስነ-ልቦና/ስነ-ዓዕምሮ ባለሙያው) የሚሰጥ የንግግር ህክምና
Individual psychotherapy
2. የስብዕና ህመምን በመድሃኒት ለማከም አዳጋች በመሆኑና ለስብዕና ህመም የመድሃኒት ህክምናው በዋነኝነት ያተኮረ ባይሆንም ተጓዳኝ ለሆኑ የህመም ምልክቶች ለምሳሌ ለጭንቀት ብስጭትና ተያያዥ ምልክቶች(Delusional thinking) የሚከተሉትን መድሃኒቶች ለአጭር ጊዜ ይታዘዛል።
1. Diazepam(Valium)
2. Haloperidol (Haldol)

#የዚህ ህመም ተጠቂዎች በራሳቸው ጊዜ የህክምና ዕርዳታ ሲፈልጉ ስለማይስተዋል የምታውቁት ጓደኛ/የስራ ባልደረባ ካላቸው
የስነልቦና ባለሙያዎች (Clinical psychologist) ወይም የስነ-ዓዕምሮ ባለሙያ እንዲያገኙ እንርዳቸው::
አድራሻዎች
=======
-አማኑኤል የአዕምሮ ልዩ ሆስፒታል***
-ጥቁር አንበሳ የስነ-ዓዕምሮ ህክምና ክፍል
-ቅዱስ ጳውሎስ ስነ-ዓዕምሮ ህክምና ክፍል
-ኤካ ኮተቤ ፣ሚኒሊክ፣ ዲላ፣ባህርዳር፣ጎንደር፣ ሀዋሳና ሌሎችም
የስነልቦናና የስነ-ዓዕምሮ ባለሙያዎች ታገኛላችሁ!

በክፍለሀገር ከዚህ ቀደም የተጠቀሱ የስነ-ዓዕምሮ ህክምና ሆስፒታሎችን ተጠቀሙ።

ብሩህ ጊዜ
ቃልኪዳን
479 views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 13:13:19
346 views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 13:13:18 ስዊፍት/SWIFT ምንድነው?
__
ሰሞኑም አሜሪካ እና አጋር የአውሮፓ ሀገራት በዓለም የንግድ ታሪክ ከኢራን በመቀጠል የተወሰኑ የሩሲያ ባንኮች የስዊፍት ስርአትን እንዳይጠቀሙ አግዷል። ለመሆኑ ስዊፍት/SWIFT ምንድነው?

SWIFT የሚለው ቃል ምህጻረ-ቃል ሲሆን የሚወክለው Society of Worldwide Interbank Financial Telecommunications የሚለውን ነው። ይህ ስርአት በቤልጂየም ውስጥ እ.ኤ.አ. በ1973 የተመሠረተ ተቋም ነው። የስዊፍት ስርአት ፋይናንስ ነክ መረጃዎች በፍጥነት፣ በአስተማማኝ ሁኔታ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በአለም ላይ በሚገኙ 200 ሀገራት ውስጥ ያሉ 11,000 ባንኮች እንዲላላኩ ያስችላል። ስዊፍት ባንኮችን ተክቶ ለደንበኞች ገንዘብ የሚያስቀምጥ ተቋም አይደለም። ከእዚያ ይልቅ ባንኮች እርስ በእርስ የሚያደርጉትን ፋይናንሺያል ትራንዛክሽኖችን የተመለከቱ ፋይናንስ ነክ ምስጢራዊ መልእክቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ያቀባብላል። በአጭሩ የአለም አቀፍ ባንኮች አስተማማኝ gmail በመሆን ያገለግላል።

ለምሳሌ ያህል ባንኮች የመተማመኛ ሰነዶች/Letter of Credits ለመከፈት፣ የገንዘብ ዝውውር ትእዛዛትን ገንዘባቸውን ካስቀመጡባቸው ባንኮች ለማዘዝ፣ ኮርፖሬሽኖች የከበሩ ማእድናትና የአክሲዮን ግዢዎችን ለመፈጸም የSWIFT ስርአትን ይጠቀማሉ።

የሩሲያ ባንኮች ከSWIFT ስርአቱ ተቆረጡ ማለት የሩሲያ የአለም አቀፍ ንግድ ላይ ከፍተኛውን ጫና ይፈጥራል። የሩሲያ ባንኮች ወደ ድንጋይ ዘመኑ የቴሌግራም እና የፋክስ ስርአት ለመመለስ ይገደዳሉ። ኢራን ከSWIFT ስርአት የተሰረዘች ጊዜ የወጪ ንግዷ በ2/3 ቀንሷል።

SWIFTን የሚቆጣጠሩት የG-10 ሀገራት ማእከላዊ ባንኮች ሲሆኑ እነዚህም ሀገራት ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኢጣልያ፣ ኔዘርላንድ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ እና ስዊዲን ናቸው። የእነዚህን ሀገራት ማእከላዊ ባንኮች በበላይነት የሚመራው የቤልጅየሙ ማእከላዊ ባንክ ነው።

Tilahun Girma Ango
377 views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 00:38:59

የደራሲ መሀመድ አሊ/ ቡርሐን አዲስ/ "የመሲሖች እድር " መፅሃፍ ሁለተኛው እትም ያለፍቃዱ በገበያ ላይ እየተሽጠ ነው።ከራሱ እስከምንሰማ ድረስ ይህንን መፅሃፍ ባለመግዛት እንተባበረው።

መልዕክቱን እንዳደርስ ከ @

Debo A. Aster
715 views21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 01:15:25
680 views22:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 01:15:21 ዴንማርክ በሚገኙ ቤተመፃህፍት በመፅሀፍ ፈንታ ለ30ደቂቂቃ ሰዎችን ተውሳቹ የህይወት ታሪካቸውን ታደምጣላቹ።ዓላማው ጭፍን ጥላቻን መዋጋት ነው።

እያንዳንዱ ሰው ታይትል አለው - “ሥራ አጥ”፣ “ስደተኛ” “ባይፖላር” ወዘተ – ታሪካቸውን ሰምተህ ግን ምን ያህል “መጽሐፍን በሽፋኑ መፍረድ” እንደሌለብህ ትገነዘባለህ። ይህ ፈጠራ እና ብሩህ ፕሮጀክት ከ 50 በላይ በሆኑ አገሮች ውስጥ ይሠራል እሱም "የሰው ቤተ መጻሕፍት" ይባላል።

እና ዛሬ ከአንድ ሰው ፊትና ልብስ ባሻገር ታሪካቸውን - የህይወት ልምዳቸውን- የህይወት ትርጉማቸውን- ድክመት ብርታታቸውን- አድምጡ።

My friend bio reads
(Be the love you never received )

Aynalem Z Otoro
665 views22:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 18:20:57 ድህረ-እውነት (post-truth)
===================
* በሰው ልጅ እና በገሃዱ ዓለም መካከል የነበረው ግንኙነት ተበጥሷል፤
* የእውነት ጥያቄም አልፎበታል!! ጠንካራ የሆነ ወሬ ሁሉ እውነት ነው!!
አሁን የምንኖረው የድህረ-ዘመናዊው ዓለም አካል ‹‹Hyper Reality›› ወይም post-truth ይባላል፡፡ ይሄም ዘመን ‹‹ማንነት፣ እውነት…›› የሚባሉ ጥያቄዎችን መመለስ የማያስፈልግበት ዘመን ነው፡፡ አሁን ባለው ዓለም ውስጥ ዋናው ጥያቄ የእውነት ጥያቄ ሳይሆን አብሮ የመኖር ጥያቄ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊው ነገር ዲስኩር ነው፤ ጠንካራ የሆነ ወሬ ሁሉ እንደ እውነት የሚቆጠርበት ዘመን ላይ ነን ያለነው፡፡ በመሆኑም፣ ከባህል ውጪ፣ ከፖለቲካ ውጪ፣ ከዲስኩር ውጪ፣ ከቋንቋ ውጪ ምንም ዓይነት እውነት የለም።
በድህረ-ዘመናዊው ዓለም ውስጥ አንድ ነገር እውነትም ሐሰትም መሆን ይችላል፤ ለምን? ምክንያቱም ከኋላ ማጣቀሻ ሪፈረንስ ስለሌለን፤ ነባራዊ የሆነ ሜታፊዚካዊ መሰረት ስለሌለን ፡፡ ስለ አንድ ነገር እውነት ወይም ሀሰት ለማለት በመጀመሪያ ስለ ገሀዱ ዓለም መስማማት አለብን፡፡ በድህረ-ዘመናዊው ዓለም ላይ ግን እንደዚህ ዓይነት ስምምነት የለም፤ We don’t have objective metaphysical foundation.
ይሄ ምን ማለት እንደሆነ የዘመናችንን የዕለተለት ህይወት እንደ ምሳሌ ወስጄ ላስረዳ፡፡ ለምሳሌ፣ አንድ ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ጎግል ውስጥ ገብተህ ያንን ነገር Search ስታደርግ ብዙ ጊዜ ካገኘኽው፣ ያ ነገር እውነት ነው ማለት ነው፡፡ የዚያን ነገር እውነትነት የግድ ገሀዱ ዓለም ውስጥ ወጥህ ‹‹ይሄ ነገር ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረም›› ብለህ መጠየቅ የለብህም፤ ወይም ደግሞ ዛሬ ፌስቡክ ላይ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች አንድን ፖስት ሼርና ላይክ ካደረጉት ያ ፖስት እውነት ነው፡፡ አሁን ዓለም እየሰራበት ያለው እውነታ ይሄ ነው። ‹‹ድህረ-እውነት (Post-truth)›› ማለት ይኼ ነው፡፡ በገሃዱ ዓለም እና በሰው ልጅ መካከል ያለው ግንኙነት ተቆርጧል፤ እውነትን ፍለጋ ወደ ገሃዱ ዓለም መሄድ አያስፈልግም፡፡
በድህረ-ዘመናዊው ዓለም ውስጥ “Rationality, Objective Truth, Universal Knowledge” ለሚባሉ ነገሮች ቦታ የለውም፤ እነዚህን ጥያቄዎችና ፍለጋዎች already አልፈናቸዋል፡፡ ድህረ-ዘመናዊው ዓለም ውስጥ universal የሆነ ዕውቀት የለም፤ መስማማት የሚባል ነገር የለም፡፡ ‹‹ወንበሩ አለ? ወይስ የለም? እኔ አለሁ? ወይስ የለሁም?›› የሚለው ጥያቄ ከ500 እና ከ600 ዓመታት በፊት የነበረ የእነ ዴካርት ጥያቄ ነው፡፡ አሁን ያንን ጥያቄ ትተነዋል፤ አልፈነዋል፡፡ አሁን ያለው ጥያቄ ‹‹ፍፁማዊ የሆነ እውነት በሌለበት፣ Legitimation Crisis ወይም ደግሞ የእሴት ግጭት ባለበት ዓለም ውስጥ እንዴት መኖር እንችላለን?›› የሚለው ጥያቄ ነው የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ የመጣው።
ከፍልስፍና ትምህርት አንድ እንደቃረምኩት የከተብኩት
484 views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ