Get Mystery Box with random crypto!

አስተሳሰባዊ አብዮት /Attitudinal Revolution

የቴሌግራም ቻናል አርማ tekitlehagerachin — አስተሳሰባዊ አብዮት /Attitudinal Revolution
የቴሌግራም ቻናል አርማ tekitlehagerachin — አስተሳሰባዊ አብዮት /Attitudinal Revolution
የሰርጥ አድራሻ: @tekitlehagerachin
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.09K
የሰርጥ መግለጫ

ለውጥ ዛሬ ይጀምራል ከዛሬም አሁን!
ከማን? ከራስ ይጀምራል።
ህይወት የአስተሳሰብ ውጤት ነች የማትፈልገውን/የማትፈልገውን ህይወት እየኖርክ /እየኖርሽ ከሆነ አስተሳሰብህን / አስተሳሰብሽን ቀይሪ!
አንዴት ??
ያላችሁን መልዕክት ጥያቄ በ @Tekit_leEthiopia_bot እና @Great_Abyssinia ማድረስ ይችላሉ

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-24 21:18:12 መፅሀፉ እንዴት ተፃፈ እንዲሁም የባለፀግነት መለኪያዎች ምን ምን ናቸው። ብዙዎች ገንዘብን ቅድሚያ ይሰጣሉ እውነቱ ግን ምንድን ነው
215 viewsErmiyas Hayilye, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:18:11 THINK & GROW RICH

መግቢያ

211 viewsErmiyas Hayilye, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:01:25 ሰላም ውድ ጓደኞቼ ;

የምንሻውን ለማግኘት ;
1. የምንፈልገውን በግልፅ ማስቀመጥ
2. በየዕለቱ የምንፈልገው ላይ ትኩረት ማድረግ / በፅሁፍ ፣ በምስጋና፣ በምናብ እናተኩር
3. ተግባራዊ ዕቅድ አውጥተን በየቀኑ መሰረታዊ ተግባር ላይ በወጥነት እንተግብር
4. በማንኛው ሰዓት ንቁ ሆነን የሚሰጠንን የመሻታችንን መልስ ለመቀበል ፍፁም አገልጋይ እንሁን
5. ሁሌም ማስታወስ ያለብን የዘራነው እንደሚበቅል ነው - ገበሬ ዘሩ እንዴት መሬቱን ሰንጥቆ እንደሚወጣ አያውቅም የሚያውቀው ቢኖር የዘራው ካጠጣው ፣ ከተንከባከበው ፣ አረሙን ከነቀለ ፣ ግብዓቱን ከሰጠ እንደሚበቅል ብቻ ነው። እንዴት የሚለው የተፈጥሮው ባለቤት( የፈጣሪ ) ነው ። የእርሱ ትልቅ ድርሻ ዘር መምረጥ ላይ ነው ። በየቀኑ ምን እየዘራን እንደሆነ አስተውለን የምንሻውን ብቻ እንዝራ ከዛም ፈጣሪም ለተፈጥሮ ዘርም ለመዳረሻው ምን ያህል የታመኑ እንደሆኑ እንገነዘባለን ።

ግንቦት 24,2013
ሲሳይ ምህረት

ህይወት ምርጫ ፣ ሂደት እና ውብ ናት ! ! !
1.1K viewsErmiyas Hayilye, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 23:03:14
1.2K viewsErmiyas Hayilye, 20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 21:44:27 ስኬትን ምን ያህል እንፈልገው ይሆን ?

አንድ ሰው ከመጠን በላይ ስኬታማ መሆን ይመኝ ነበርና ወደ አንድ አዋቂ ዘንድ ይሄዳል። ለአዋቂውም ታላቅ ሰው መሆን እንደሚፈልግ እና እርዳታውን እንደሚሻ ይነግረዋል። አዋቂውም መልሶ “ እሺ ስኬታማ ሰው መሆን ከፈለግክ ነገ ባህር ዳርቻ እጠብቅሃለው በጠዋቱ ና” ሲል መለሰለት። ሰውየው ግራ ተጋብቶ “እኔ ስኬታማ ሰው አድርገኝ አልኩኝ እንጂ ዋና አስተምረኝ አላልኩሁም እኮ” ይለዋል።

አዋቂውም “ወንድሜ ስኬታማ መሆን እፈልጋለው ነው ያልከው …… ነገ ጠዋት ከባህር ዳርቻው ጋር እንገናኝ” ብሎት መልሱን ሳይጠብቅ ጥሎት ሄደ። በበነጋታው ሰውየው ከባህሩ ዳርቻ ተገኘ ፤ሙሉ ልብሱን ሽክ ብሎ ነበር የመጣው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ሰውየው መጀመሪያ የጠየቀውን ጥያቄ አንደገና ጠየቀ “ስኬታማ ሰው ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ?” አለው።

አዋቂው በዝምታ ተመለከተው… “ና ተከተለኝ” ብሎ ወደ ባሕሩ ተጓዙ…ሰውየው ግራ ገባው..ነገር ግን አዋቂ የተባለው ሰው እጅግ የተከበረ ነበረና የሚሰራውን ያውቃል በማለት ዝም ብሎ ተከተለው….ወደ ባሕሩ ዘለቁ…መጀመሪያ ውሃው እስከ ጉልበታቸው ደረሰ…ቀጥሎ እስከ ወገባቸው….ቀጥሎ እስከዳረታቸው…..የሰውየው ልብ ተረበሸ….ስኬታማ መሆን ከዚህ ጋር ምን እንደሚያገናኘው ግራ ቢገባው “ይህ ነገር ስኬታማ ከመሆን ጋራ ምን አገናኘው?” ሲል ጠየቀ
አዋቂውም “ስኬታማ መሆን እፈልጋለው ነው ያልከኝ ወዳጄ?” አለው
ሰውየው “አዎ” ሲል መለሰ
አዋቂው የሰውየውን መልስ እንደሰማ የሰውየውን ጭንቅላት ይዞ ወደባሕሩ ደፈቀው። ሰውየው እራሱን ለማዳን ቢንፈራገጥም አልቻለም….አዋቂው የሰውየውን ጭንቅላት ለሴኮንዶች ውሃ ውስጥ ካቆየው በኋላ ቀና አደረገው…ይሄኔ ሰውየው በሃይል እየተነፈሰ
“እኔ….ስኬታማ አድርገኝ ባልኩኝ ለምን ልትገለኝ ፈለግክ?” ሲል ጠየቀ
“ስኬታማ መሆን ትፈልጋለህ?” አለው አንገቱን እንደያዘ
“አዎ”…ብሎ ሲመልስ ደግሞ ከባሕሩ ነከረው፤ እንደቅድሙ ትንሽ አየር እስኪያጥረው ካቆየው በኋላ ቀና አድርገው እንዲህ ሲል ጠየቀው
“አሁን በዚህች ቅፅበት በጣም የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?”
ሰውየው..ቁና ቁና እየተነፈ ….. “አየር” አለ
“አየህ አሁን አየር እንደፈለግከው ያህል….ስኬትን ክፉኛ ካልፈለግካት መቼም አታገኛትም…ይህ ነው የስኬት ሚስጥር” አለና አሰናበተው ይባላል። አንዳንዶች የፈለጉትን ሲያገኙ እናያለን አንዳንዶች ደግሞ እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ይቀራል።

የሁለቱን ሰዎች ልዩነት እድል በሚባለው ነገር ልናስታርቀው ብዙ ጊዜ ብንጥርም እውነታ ግን ሌላ ነው…..ስኬት ጥቂቶች ብቻ የሚታደሏት አይደለችም..ሁላችንም እንድንደርስባት በእኩል ቦታ የተንጠለጠለች ፍሬ እንጂ…እጅግ የተራባት ሰው ማድረግ ያለበትን ሁሉ አድርጎ ያገኛታል…. ብዙዎቻችን ስኬታም መሆን ብንፈልግም እጅግ ከስኬት በላይ አብዝተን የምንወዳቸው ሌሎች ጥቃቅን ነገሮች ህይወታችንን ሞልተውታል።

ሁሉም ስኬታማ ሰዎች ወደ ስኬት የመጡበት መንገድ ይለያያል፤ አንድ ፍጹም የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ግን ሁሉም ይቻላል ብለው ማመናቸውና ላመኑት ነገር ያላቸውን ሁሉ ሳይሰስቱ መስዋት ማደረጋቸው ነው። አሁን በሌሎች ሰዎች አይን “ስኬታማ” ተብለው የሚጠሩ ሰዎች በአንድ ወቅት እንደማንኛችንም አይነት አቅም እና ችሎታ ነበራቸው…የአስተሳሰብ ሁኔታ ግን አንዳችንን ወደ ኋላ አንዳችንን ወደፊት እንድንራመድ አደረገን።

አይምሮዋችን እንደ እርሻ ነው….የዘራንበትን ያሳጭደናል…አይምሮ እኛ ምን እንዝራ ምን እንትከል ግድ የለውም። መሬት በቆሎ ተዘራ ጤፍ ተዘራ ግድ አለው እንዴ?….አናም አይምሮዋችን ላይ መልካሙን ሰብል መርጠን እንዝራ….

{ በቅንነት ሼር አድርጉ)
1.6K viewsErmiyas Hayilye, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 15:31:18
ወርቅ ይቆሽሻል እንጂ ግራሙ አይቀንስም
ሰውም ይፈተናል እንጂ ወድቆ አይቀርም
977 viewsErmiyas Hayilye, 12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 08:18:05
<<የእኔ የህይወት ፍልስፍና... ምንም መፍራት አይደለም። በጥሩ መንገድ ከተጫወትኩኝ አሪፍ፤ በጥሩ ሁኔታ ካልተጫወትኩኝ እማራለሁ ከውድድሩ እና ወደሌላ እቀጥላለሁ። >> ሳይና አህዋል(አትሌት)

መልካም ቀን
998 viewsErmiyas Hayilye, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-07 08:04:48

እኛ ድንቅ ገበሬዎች ነን።
ዘሩ ህልማችን ነው።ፍሬው ስኬቱ ነው።አረሙ ደሞ ፈተናው ነው።

ህይወት መልካም ካሰብክ መልካም ጥሩ ከሰራህ ጥሩ ይሆናል ያሰብከውን ሁሉ እንዳሰብከው ጊዜ በፈለከው መጠን ይሰጥሀል ዋናው ነገር ምን ትፈልጋለህ?ምን ዘርተህ ምን ማጨድ ምን ማግኘት ትፈልጋለህ??ምንስ እየዘራህ ነው??

ስለዚህ የምትፈልገውን ለማግኘት ለቃልህ(ለዘርህ) ተጠንቀቅ ያንን መልካም ዘር ለማግኘት መልካሙን በመልካም መሬት ዝራ ሰው የዘራውን ያኑኑ ያጭዳልና የመለወጥ ግዜው ነገ አይደለም አሁን ነው ።ለዘራኸው ዘር የሚገባውን ሁሉ አድርግ ከዛም ግዜ ታማኝ ነው ልክ እንደ መልካም ገበሬ ፍሬውን ያለገደብ ይሰጥሀል።

መልካም የተባረከና ስኬታማ ቀን ይሁንልን።
947 viewsErmiyas Hayilye, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 23:00:06 ከዕለታት አንድ ቀን ህጻን ቶማስ ኤዲሴን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለእናቱ «እማየ ፣ ይህን መልዕክት ላንቺ እንዳደርስ ከመምህራችን የተሰጠኝ ነው» በማለት በእጁ የያዘውን ወረቀት ሰጣት። ወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ፅሁፍ ስታነብ አይኖቿ እንባ አቀረሩ። ለህጻኑ ቶማስ ኤዲሰንም መልዕክቱ «ልጅሽ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ነው፤ ስለሆነም የኛ ትምህርት ቤት ከርሱ አቅምና ብቃት አንጻር የሚመጥነው ባለመሆኑ በቤት ውስጥ አስተምሪው» ይላል በማለት አነበበችለት። እናት ልጇን በራሷ ስልት በቤት ውስጥ ማስተማር ጀመረች። ራሱም በራሱ እንዲማር አተጋችው፡፡ ጊዜዋን ሰውታ ከርሱ ጋር ሌት ከቀን በማሳለፍ አበረታችው፡፡

ዓመታት አለፉ። የቶማስ ኤዲሰን እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ህጻኑ ቶማስ ኤዲሴን የህይወት ፈተናዎችን ተጋፍጦ የወጣነት የዕድሜ እርከን ላይ ደረሰ። ለአገሩ አሜሪካና ብሎም ለዓለም ብዙ የፈጠራ ትሩፋቶችን አበረከተ። በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ አምፑል «ፈጣሪ» ሆነ። ዓለምን ከ«ጨለማ» ወደ «ብርሃን» አሸጋገረ። የሰው ልጅ ከኩራዝ ብርሃን ወደ ኤሌክትሪክ ብርሃን እንዲተዋወቅ መሸጋገሪያ ድልድይ ፈጠረ።

አንድ ቀን ቶማስ ኤዲሰን የእናቱን ሳጥን እየፈተሸ ሳለ አይኖቹ ከአንዲት ወረቀት ላይ ተተክለው ቀሩ። ወረቀቱን አንስቶ በውስጡ የያዘውን መልዕክት ሲያነብ ክው አለ። ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ «ልጅሽ ቂልና የማይገባው ዘገምተኛ ነው፤ ከነገ ጠዋት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ፈጽሞ አናስገባውም» የሚል ነበር። ቶማስ ኤዲሰን ለብዙ ሰዓታት በእንባ ጎርፍ ታጠበ። ይህች ወረቀት ቶማስ ኤዲሰን ህጻን እያለ ከመምህሩ ለእናቱ እንዲያደርስ የተሰጠው ወረቀት ናት። እናት የልጇን ስሜት ላለመስበር ጽሁፉን ያነበበችው በተቃራኒው ነበር ።.

ቶማስ ኤዲሰን ወረቀቷን ካነበበ በኋላ በማስታወሻው ላይ «ኤዲሰን ሞኝ እና የማይረባ ህጻን ነበር ፤ ግና ውድ በሆነች እናቱ እገዛ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ሊሆን ቻለ» በማለት አሰፈረ ።

በቅንነት ሼር አድርጉ
@the_secret_power
@the_secret_power
834 viewsErmiyas Hayilye, 20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ