Get Mystery Box with random crypto!

ከዕለታት አንድ ቀን ህጻን ቶማስ ኤዲሴን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለእናቱ «እማየ ፣ ይህ | አስተሳሰባዊ አብዮት /Attitudinal Revolution

ከዕለታት አንድ ቀን ህጻን ቶማስ ኤዲሴን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለእናቱ «እማየ ፣ ይህን መልዕክት ላንቺ እንዳደርስ ከመምህራችን የተሰጠኝ ነው» በማለት በእጁ የያዘውን ወረቀት ሰጣት። ወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ፅሁፍ ስታነብ አይኖቿ እንባ አቀረሩ። ለህጻኑ ቶማስ ኤዲሰንም መልዕክቱ «ልጅሽ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ነው፤ ስለሆነም የኛ ትምህርት ቤት ከርሱ አቅምና ብቃት አንጻር የሚመጥነው ባለመሆኑ በቤት ውስጥ አስተምሪው» ይላል በማለት አነበበችለት። እናት ልጇን በራሷ ስልት በቤት ውስጥ ማስተማር ጀመረች። ራሱም በራሱ እንዲማር አተጋችው፡፡ ጊዜዋን ሰውታ ከርሱ ጋር ሌት ከቀን በማሳለፍ አበረታችው፡፡

ዓመታት አለፉ። የቶማስ ኤዲሰን እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ህጻኑ ቶማስ ኤዲሴን የህይወት ፈተናዎችን ተጋፍጦ የወጣነት የዕድሜ እርከን ላይ ደረሰ። ለአገሩ አሜሪካና ብሎም ለዓለም ብዙ የፈጠራ ትሩፋቶችን አበረከተ። በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ አምፑል «ፈጣሪ» ሆነ። ዓለምን ከ«ጨለማ» ወደ «ብርሃን» አሸጋገረ። የሰው ልጅ ከኩራዝ ብርሃን ወደ ኤሌክትሪክ ብርሃን እንዲተዋወቅ መሸጋገሪያ ድልድይ ፈጠረ።

አንድ ቀን ቶማስ ኤዲሰን የእናቱን ሳጥን እየፈተሸ ሳለ አይኖቹ ከአንዲት ወረቀት ላይ ተተክለው ቀሩ። ወረቀቱን አንስቶ በውስጡ የያዘውን መልዕክት ሲያነብ ክው አለ። ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ «ልጅሽ ቂልና የማይገባው ዘገምተኛ ነው፤ ከነገ ጠዋት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ፈጽሞ አናስገባውም» የሚል ነበር። ቶማስ ኤዲሰን ለብዙ ሰዓታት በእንባ ጎርፍ ታጠበ። ይህች ወረቀት ቶማስ ኤዲሰን ህጻን እያለ ከመምህሩ ለእናቱ እንዲያደርስ የተሰጠው ወረቀት ናት። እናት የልጇን ስሜት ላለመስበር ጽሁፉን ያነበበችው በተቃራኒው ነበር ።.

ቶማስ ኤዲሰን ወረቀቷን ካነበበ በኋላ በማስታወሻው ላይ «ኤዲሰን ሞኝ እና የማይረባ ህጻን ነበር ፤ ግና ውድ በሆነች እናቱ እገዛ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ሊሆን ቻለ» በማለት አሰፈረ ።

በቅንነት ሼር አድርጉ
@the_secret_power
@the_secret_power