2022-05-15 06:13:41
ክርስትና ክርስቶስ በኛ የሚኖረው ሕይወት ነው !“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”
( ዕብራ 1፥3)
“እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።”
(2ኛ ቆሮ 3፥18)
ክርስትናን የኖረ ዛሬም መኖር የሚችል ወደፊትም መኖር የሚችል ክርስቶስ ብቻ ነው።ጌታ በኛ የሚኖር ከሆነ በኛ ለመገለጡ ምንም ጥርጥር የለም። ምክንያቱም በኛ የመኖሩ ሚስጥር እኛን በራሱ መልክ መግለጥ ነው።ክርስትና ጌታ በኛ የሚኖረው ሐይወት አንጂ እኛ የምንኖረው ሕይወት አይለም ።
ከኛ የሚጠበቀው እርሱን መቀበል፣በርሱ ማመን፣በደሙ ከኃጢያት መንጻታችንን አምኖ መቀበል ። እርሱ በኛ እንዲኖር መፍቀድ ፣ ለርሱ የተሰጠ ሁለንተናን መያዝ ነው ።
ክርስቶስ ሁሉን በመስቀል ላይ ጨርሶ ይህንን ሕይወት ባንተ እንድኖረው ፍቀድልኝ ብሎ ጀመረ ። እኛ በራሳችን ለመትከል የምንታገለው ጽድቅ የሚገልጠው እኛን እንጂ እርሱን አይደለም ። ደግሞስ ቃሉ ጽቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ይል የለ ።
የክርስትና ሕይወት ለውጥ የሚጀምረው ክርስቶስ ባንተ እንዲኖር ከመፍቀድ ነው።
“ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።”(ገላትያ 2፥20)
ክርስትና የምናወራው፣ የምንሰብከው፣ የምንዘምረው፣ የምንጸልየው ሕይወት ሳይሆን ክርስቶስ በኛ የሚኖረው የተገለጠ ሕይወት ነው ።
እውነቱ ብዙዎች ክርስትና አልገባቸውም ።ለዚህ ነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጌታ የፈጸመውን እና የጨረሰውን ሕግጋት እየለቀሙ የራሳቸውን ጽድቅ ለማቆም የሚታገሉበት ።ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለው አስርቱን ሕግጋት ጭኜበችኃለሁና እነርሱን ይዛችሁ ጽድቃችሁን ፈልጉ አላለንም ። የሰው ልጅ በመውደቁ ሕግጋቱን መፈጸም አልቻለምና ።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለው እንለዋወጥ ነው። ይኸውም ባንተ ልኑር አንተም በኔ ኑር ፣ ራስህን ስጠኝ ራሴን ልስጥህ ፣ ኩነኔህን ወስጄ ጽድቄን ልስጥህ ፣ የዕዳ ጽሕፈትህን ወስጄ ነጻነቴን ልስጥህ ፣ ፍርድህን ልቀበል በነጻነት ኑር.. ወዘተርፈ የሚል ነው ።ብዙዎች ክርስትናን በራሳቸው ሊኖሩት ስለሚታገሉ ስልችት ድክም የሚያደርግ መራራ የእስር ቤት ሕይወት ያደርጉትና እየቆዩ ሲሄዱ ፍቅራቸው ይቀዘቅዛል፣ እምነታቸው ይዝላል፣ ግለታቸው ይቀዘቅዛል፣ ሩጫቸው ወደ ፊት መሆኑ ቀርቶ የኃልዮሽ ይሆንባቸዋል ከዚያም የእምነታቸው ሞተር ይጠፋባቸዋል።
እውነቱ ግን በእነርሱ ያለው ክርስቶስ በነርሱ መኖር ስለደከመው አይደለም ።
ይቁንም ያልሆነ መረዳት የያዙ እነርሱ ናቸው ።
ከዚህም የተነሳ ብዙ ክርስቲያኖች ዱሮ ጠንካራ አገልጋይ ነበርኩ፣ እጅግ የምተጋ ጸሎተኛ ነበርኩ፣ በልዩ ስጦታ የተካንኩ ዘማሪ ነበርኩ፣ ግሩም ሰባኪ ነበርኩ፣ ነበርኩ ! ነበርኩ ! ነበርኩ ! እያሉ የነበሩበትን እንጂ አሁን ያሉበትን የማያወሩ ልባቸው እምነታቸው ሕይወታቸው ይደበዝዝባቸዋል ።
ዛሬስ ሕይወት እንዴት ነው ስትሏቸው ነበርኩን ማውራት ይጀምራሉ ። ቋንቋቸው ሁሉ ነበርኩ.....ነበርኩ ነው።
ከኃጢያት ወደ ኃጢያት ፣ ከእርኩሰት ወደ እርኩሰት ፣ ከበደል ወደ በደል እየሄዱ የሚያወሩት የሚሰብኩት የሚያውጁት ፣ የሚያስተምሩት፣ የሚዘምሩት ሰው በሂደት መቀደስ እንደሚችል ሆኖ ሳለ እነርሱ ከድካም ወደ ድካም የሚገሰግሱት ይሆናሉ ።
በመሰረቱ ቅድስና ሦስት ደረጃዎች አሉት
1ኛ, እንዳመኑ በክርስቶስ ቅድስና መቀደስ ! ( ኤፌ2:-8-9)
2ኛ, ሰው ካመነ በኃላ በሒደት በሕይወቱ የሚጀምረዊ ሒደታዊ የቅድስና ሕይወት ! “... ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።” (ዕብራ 12፥14)
3ኛ, አሁን ካለንበት ሥጋ ተለይተን ወደ ጌታ ሥንሔድ ! (1ጴጥ 1:-8-9)
እውነቱ ግን ክርስቶስ በኛ ሳለ በኛ እየኖረ ከክብር ወደ ክብር ፣ ከኃይል ወደ ኃይል ፣ ከከፍታ ወደ ከፍታ ፣ ከመገለጥ ወደ መገለጥ ፣ ከሞገስ ወደ ሞገስ ወዘተርፈ እንገሰግሳለን ።
“የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።”( 2ኛ ጴጥ 1፥2-3 )
ችግሩ ቤተክርስቲያን ሰይጣን አብያተ ክርስቲያትያናትን " በኒቆላዊያን" ትምህርት፣በኤልዛቤል ትምህርት፣ በተለያየ የሐሰት ትምህርት መጥለቅለቋ ነው። ሁሉም ትምህርቱን መፈተሽ ይኖርበታል ። እኛ አዲስ የተባለን አስተምሮ እንድንሰበስብ አልተጠራንም ቅዱሱ ቃል :-
“ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥16
ዛሬ ዛሬ ላይ ስለ ደህንነት፣ ስለ እግዚአብሔር ጽድቅ፣ ስለ ኢየሱስ የማዳን ሥራ ፣ ስለኃጢያት፣ ስለሞት፣ ስለትንሳዔ፣ ስለ ዳግም ምጸዓት ፣ስለደሙ መስማት እያቆመው ።አሁን ላይ ትምህርቶች ሁሉ ስለቁሳዊ በረከት ፣ ስለሥጋ ፈውስ ፣ስለተዓምራትና ስለገንዘብ ችግር...ወዘተርፈ ሆነዋል ። እነዚህ እይታቸው በምድር ላይ የተተከለ፣ ልባቸው እየደነደነ ፣ እኔ ያልኩት ካልሆነ በማለት የጌታ አካል የሆነችውን ቤ/ክ ለመበታተን ቆርጠው የተነሱት።
ስለዚህ የቤተክርስቲያናችንን አስተምህሮ መጠበቅ፣ የሕዝቡን የአኗኗር ዘይቤ ፣ የአውነተኛ ክርስቲያኖችን አቋም፣ የሕይወትና የአገልግሎታችንን ጥራት በቃሉ ብረሃን በመፈተሽ ልንጠብቅ ይገባል።
@alexkhc
@alexkhc
133 viewsedited 03:13