Get Mystery Box with random crypto!

የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ (pastor Alemayehu Abebe )

የቴሌግራም ቻናል አርማ alexkhc — የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ (pastor Alemayehu Abebe )
የቴሌግራም ቻናል አርማ alexkhc — የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ (pastor Alemayehu Abebe )
የሰርጥ አድራሻ: @alexkhc
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 184

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-07-01 05:14:17
232 views02:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 05:14:12 ስለዚህ በዕውቀታችን ለሐገር ለትውልድ የሚጠቅምን መልካም ነገር ሰርተን የምናልፍት መሳርያ ሊሆን ይገባል።
ብሔር በአንድ ተመሳሳይ ባህልና ስነልቦና ስር የተሰባሰቡ ህዝቦች መጠሪያ ነው።ብሔር የአንድ አካባቢ የህዝብ መኖሪያ ስፍራ መጠርያ ነው።ነገር ግን ያለ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል እውቀት ሰውኛ እሳቤ ብቻውን ባዶ ነው። ክርስትና ሕይወት ነው። በኑሮ የተገለጠ የብረሐን ሕይወት። የክርስቶስን ሕይወት ለመኖር ሳንወስን በስሙ ብቻ ለመመካት መሞከር ከንቱነት ነው። ስለዚህ ቋንቋና ብሔር ብቻቸውን በቅዱስ ቃሉ እውቀት ብርሃን ካልተመሩ ምግባራቸው እንሰሳዊ ይሆናል። ወደ ቅዱስ ቃሉ ዕውቀት እንመለስ ።

የሰው ልጅ ሁሉ ለፍጥረት በረከት ምክንያት እንዲሆን ተፈጥሮአል ። ከኛ የተነሳ ለሁሉ ሰላም እንዲሆን ደስታ ብረሃን እንዲሆን ተፈጥረናል። እንታደስ እንመለስ በይቅርታ በእርቅ እና በፍቅር እንኑር በራሳችን እንዲሆን የማንፈልገውን በሌላው ላይ እንዲሆን አናድርግ ።

ልዩ ጥሪ እና ምክር
1ኛ, በዘረኝነት እና በጽንፈኝነት በፖለቲካ ሽኩቻ በአገር ላይ እየመጣ ያለውን አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም በያለበት ለሰላም ሊቆም ይገባል።

2ኛ, ሁሉም የኃይማኖት መሪዎች ሕዝባቸውን ጠርተው ያስተምሩ ይምከሩ ይገስጹ !

3ኛ, የፖለቲካ አመራሮች በተለያየ ጎራ ተደራጅቶ ሕዝብ የሚያባሉ አክቴቪስቶችን አባሎቻችሁን አስተምሩ ምከሩ !

4ኛ, ሙሁራኖች መምህራኖችንና ተማሪዎቻችሁን ምከሩ አስተምሩ ገስጹ !

5ኛ, ሁሉም ሰው በየከተማው በየመንደሩ ለፍቅር ለእርቅ ለይቅርታ ችግሩን በውይይት በምክክር በመፍታት ለምድራችን ሰላም ምክንያት ይሁን ። ተባረኩልኝ !
58 views02:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 05:14:12 ሰው ሁሉ ከዘረኝነት ወጥቶ በአንድነት ለሰላም ይቁም !

እየተሰማ ፣አየታየ፣ እየተወራ እና እየሆነ ያለው ጆሮን ጭውው የሚያደርግ እጅግ ዘግናኝ አስፈሪ የሆነ ድርጊት ነው። ሰው ለሰው የበረከት የደስታ ምክንያት ሊሆን ይገባል እንጂ የሞቱ የውድቀቱ የሐዘኑ የለቅሶው ምክንያት መሆን የለበትም ። የሰው ልጅ ክቡር ፍጥረት ነው ። ዘረኝነት ባህል ቋንቋ የሰው ልጅ በምድር መኖር ከጀመረ በኃላ የተገኙ ነገሮች ናቸው። ስለዚህም እነዚህ ሁሉ ለሰው ልጅ ጥቅም የተፈጠሩ በመሆናቸው ከሰው በላይ ሊሆኑ አይችሉም።የሰው ልጅ ክቡር ፍጥረት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረ ፍጥረት ነው። በመሆኑም ሰው ከሰው ይበልጣል ያንሳል የሚል የተፈጥሮ ሕግ የለም። የሰው ልጅ ሁሉ እኩል ነው:: “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ...." ዘፍጥረት 1፥26

የሰውን ልጅ በዘረኝነት ለያይቶ ማጋደል የእግዚአብሔርን የተፈጥሮ ሕግና የክርስቶስን የማዳን ተልዕኮ መቃወም መርሁንም ማደናቀፍ ነው።ጌታ የሞተው ለሰው ሁሉ ነው። የማዳኑም ተልዕኮው ለሰው ልጆች ሁሉ ነው ።

ዘረኝነትን በብዙ ቃላት ማየት ይቻላል ዘረኝነት ጎሰኝነት ፣ ጠባብነት ፣ አላዋቂነት ፣ መንደርተኝነትና ራስ ወዳድነት ነው ። ዘረኝነት ከፋፋይነት ከመሆኑም በላይ የክርስቶስን አካል ቤተ ክርስቲያንን የሚያፈርስ የሰይጣን መሳርያ ነው ። ዘረኝነት ሐገርን የሚያፈርስ የሐገር ነቀርሳ ነው ። ሰው ለሰው የተፈጠረ ክቡር ፍጥረት በመሆኑ አንዱ ለአንዱ በረከት ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ የተፈጥሮ ሕግ ጋብቻ ፣ ማህበራዊ ሕይወት፣ የባህል ፣የኢኮኖሚ፣ የሐገር ፍቅር ያቆራኘው ያስተሳሰረው ሕዝብ ነው:: መችም አብሮነትን መቻቻልን እንደ አዲስ ማንም ሊያስተምረን አይችልም::ቤተክርስቲያን በአገራችን ላይ ያጠላውን ክፉ የዘረኝነት ድባብ ልታወግዝ ልትቃወመው ይገባል ::

ዘረኞች ለፖለቲካ ትርፋቸው ለሙስና ምሳቸው በትውልድ መካከል የጥላቻ ነጋሪት እየጎሰሙ ነው:: ዘረኞች በዘረኝነት ስለታወሩ ከራሳቸው ዓለም ውጪ ነገሮችን ማሰብ አይችሉም:: የሚገርመው ዘረኝነት ጓዙን ጉዝጓዙን ጠቅልሎ ወደ ቤተክርስቲያን መግባቱ ነው:: ክርስቶስ ኢየሱስ በሞቱ ያዳናቸው በደሙ አጥቦ የቀደሳቸው ቅዱሳንን እንጂ በዘር ልዩነት የገነባው ቤተ ክርስቲያን የለውም::

የዛሬ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዘረኝነት በሰፊው ተንሰራፍቷል::ወንድምን መጥላት ነፍሰ ገዳይነት ነው ።
"እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል።ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።" (1ኛ ዮሐንስ 3:-14-15)

መጥላት ብቻ ነፍሰ ገዳይነት ከሆነ ገዳይነት ምን ሊሆን ነው ? የእኛ ጥሪ የአስታራቂነት ጥሪ ነው ።ዛሬ ላይ በዘረኝነት አፍራሽ የሆነ ሰይጣናዊ አጀንዳ የታወሩ የተፈጠሩበትን በጎ እና መልካም ዓላማ የጣሉ ብዙዎች ናቸው ።

የዘር ፖለቲካን ማወጅና ማራገብ ወንጌልን ከማሰራጨት የበለጠ እንደሆነ አምነው የሚንቀሳቀሱ ክርስቲያን ነኝ ባዮች አሉ። ከጻድቁ ፍርድ አያመልጡም ።እየሆነ ያለው እየተሰማ ያለው በእጅጉ የሚያሳዝን የሚያስለቅስ ነው። የዘር ፓለቲካ እርስ በርስ ከማጫረስ ያለፈ ውጤት የለውም ። መታሰብ ያለበት ነፍሰ ገዳዩ ጥይት ተኳሹ ብቻ አይይደለም በሐሳብ የተባበረ ፣በገንዘብ የደገፈ፣ በምንም መልኩ ለወንድሙ መጥፋት መንገድ ያመቻቸ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው። ከእግዚአብሔር መንግስት እድል ፈንታ የለውም።

ለጊዜያዊ ክብር፣ ስልጣን ፣ ዝና ፣ ብልጽግና ወዘተርፈ ብሎ መተኪያ የሌለውን የሰውን ልጅ ህይወት ማጥፋት በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ከመሆኑም በላይ ከእግዚአብሔር መንግስ የሚያጎል ኃጢያት ነው ። ለጊዜያዊው ብሎ የዘላለም ህይወትን ማጣት ለሁለተኛው የዘላለም ሞት እራስን ማዘጋጀት ነው ።

ወገኖች ሆይ ዛሬ ላይ የምትጫረው የዘረኝነት እሳት ነገ ላይ ማንም ሊቆጣጠራት በማይችልባት ሆና ምንድርን በደም ጎርፍ መሙላቷን በጥቂቱ ከሩዋንዳ መማር ይቻላል :: የዘረኝነት የሰደድ እሳት ተመልሶ ጠንሳሹን ወገንን ላለማጥፋቱ ምንም ዋስትና የለም::

በዚህ ውስጥ ቤ/ክ ያላትን አስተዋጽዖ ማጥናት ይቻላል:: ቤ/ክ ማስተጋባት ያለባት ፍቅርን፣ እርቅን፣ ይቅርታን ፣ ፍትህን፣ የሚያድነውን ወንጌል …ወዘተ ነው:: በዘረኝነት ለተከሠተው ጥፋት ማዘን ብቻ በቂ አይደለም ዘረኝነት ፈጽሞ ለማጥፋት ተሰብስቦ መመካከር ይገባል ። አይደገምም ልንል ይገባል! ፍትህና የዜግነት መብት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊረጋገጥ ይገባል:: ሰይጣን ከመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ ነው ። ለዚህም የዘላለም ፍርድ፣ ጥፋት ፣ የገሃነም እሳት ተወስኖለታል። የሚከተለቱት እና የርሱ የሆኑ ሆሉ እድልፈንታቸው ይኸው ነው ።

ከሩዋንዳ እልቂት እንማር::አስተዋይ ከታሪክ ይማራል። ሰነፍ ግን ከራሱ ይማራል ነውና ነገሩ በሩዋንዳ ወደ አንድ ሚሊዬን የሩዋንዳ ዜጎች በዘር ግጭት ሳቢያ ለማመን እንኳ በሚከብድ ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። ይህ ዘረኝነት እና ቅስቀሳዎቹ ያስከተሉት ታላቅ እልቂት ነው:: በሁቱና በቱትሲ ሁለት ብሔሮች ብቻ ዘርን ማዕከል ተደርጎ ፅንፈኛ ሚዲያዎች በሰሩት የግደለው ! አጥፋው ! አውድመው ! የተሰኘ የቅስቀሳ ወላፈን በተነሳ የዘረኝነት የሰደድ እሳት የማይተካው የሰው ልጆች ህይወት ተቀጠፈ:: አሁን እኛ ጋር የምናየው የዘረኝነት እብደት ሩዋንዳውያንም ያኔ ሲጀማምራቸው የገጠማቸው ችግር ነው፡፡ ዛሬ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የምትለኮስ የጥላቻ ቃል ጥላቻውን በስሜት ለሚለኩሳት የጥፋት ሰውም የምትደረስ መርዝ ናት፡፡ስለዚህ እንመለስ የተፈጠርንበትን የተጠራንበትን የሰው ልጅን ከጥፋት የመታደግ በጎ ዓላማ እንያዝ።ከወዲሁ ልዩነትን መጠፋፋትን በሚፈጥሩ ሰይጣናዊ ዓላማዎችን እንንቃ።

ዘረኝነት በነገሰበት ቦታ እውቀት የለም ጥበብም እንዲሁ። ሰው ሰው ለመባል ማሰብ አለበት። ሰው ማሰብ በመቻሉ ልዩ ፀጋውን ተጠቅሞ አለምን ይሁን ተፈጥሮን መግራት እና አስተካክሎ ለጥቅሙ ማዎል ይችላል። እንሰሳት ግን ስለማያስቡ ተፈጥሮንም ሆነ አለምን በመግራት ለጥቅማቸው ማዋል አይችሉም። ይህ ፀጋ ያለው ሰው ብቻ ነው። ቋንቋ የሰው ልጆች እርስ በርስ የሚግባቡበት መሳሪያ እንጂ የመለያያ ምክንያት አይደለም:: ሰዎች በቋንቋቸው ትምክህት እና ኩራት ሊሰማቸው አይገባም:: የሰው ልጅ ከቋንቋ በላይ ነው :: ከባህሉ በላይ ነው። በአኗኗር ዘይቤ ከፈጠራቸው እሴቶች ሁሉ በላይ ነው።

ማንም ቤሔሩን ዘሩን አገሩን ቤተሰቡን ቋንቋውን መርጦ ወደዚህ ዓለም የመጣ የለም :: ይህ ትውልድ ለሚያደርገው ነገር ሁሉ መጠንቀቅ ይኖርበታል ::ቋንቋ ከመግባብያነት እና የእውቀት መሸጋገርያ ድልድይ ከመሆን ባለፈ ጥቅምት አይኖረውም። ሁሉም በሚያውቀውና በተረዳው መጠን የሚጠቅምን ነገር ስርቶ ማለፍ ይኖርበታል::የሰው ልጅ እውቀቱን ለመልካምም ሆነ ለክፉ ተግባር ሊጠቀምበት የሚያስችለው የማሰብ ኃይል እንዳለው አሳይቷል። እውቀት ከአድማስ ባሻገር የምናይበት አጉልቶ ማሳያ መነፅር ነው።አውቀት ለትውልድ የምናስተላልፈው የብዙ በረከት ምንጭ ነው።
52 views02:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 23:40:49
220 views20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 15:57:38 Channel photo updated
12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 06:37:20
214 views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 04:14:34 በፍቅሩ እንድንኖር ታዘናል !

ስለ ፍቅር ያልሰበከ ፣ያልጻፈ፣ ያልዘመረ፣ ያልዘፈነ ፣ያላስተማረ ማነው ? ሆኖም ግን የኖረው ፣በሕይወቱ የገለጠው፣ ለፍቅር ራሱን የሰጠ ፣ፍቅር የሚያስፍለውን መሰዋዕትነት ለመክፈል የቆረጠ ግን....

ከሞት የበረታ ከሲዖል ይልቅ የጨከነ አለ ጠቢቡ ሰለሞን :-
“እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።”
— መኃልየ. 8፥6

ነፍሱ የወደደችውን ለማግኘት ውቅያኖስ የማይሰነጥቅ፣ በረሃ የማያቋርጥ፡ ተራራ የማይቧጥጥ ቁልቁለትን የማይወርድ አሳትን የማያቋርጥ ማነው? በፍቅር ተጠርቶ እናትና አባቱን ትቶ የማይሄድ ማነው? ወይ ፍቅር ! አይጨበጥ አይዳሰስ አይዙት አያስሩት ድንገት የሚድፍ በመንገድ የሚያስቀር ሐያል ብርቱ ገናና የፍቅር አይነቱ ብዙ ነው ።

አንድ ሲባል የጾታ ፍቅር አለ። ወረት ሲያልቅ የሚያልቅ በወረት ሞተር ላይ ሆኖ የሚጋልብ ነዳጅ ሲያልቅ የሚያልቅ ጊዜያዊ ዘላቂ ያልሆነ ወይ ፍቅር :-
“ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞም ከወደዳት ውድ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፦ ተነሥተሽ ሂጂ አላት።”
— 2ኛ ሳሙኤል 13፥15
ፍቅርህ/ሽ በልቤ ይነዳል እሳት ጉልበቴ በፍቅርሽ ራደ ከፍቅርሽ የተነሳ ታምሜያለሁ ያለ ፣ ልቤን የሞላው የሚያፍነከንከኝ ምንድነው? ልረዳው ያልቻልኩት ስሜት ምንድነው? ከሳቅ ድምቀት የበለጠ ውብ ማዕዛ ያለው ፣ ከደስታ በላቀ የሚያስደስት ውበት የተባለ ፣ ለፍቅርሽ ወደር አጣሁለት የተባለ ሁሉ ላይዘልቅ ።
አንድ ቀን በወረት ሊሰናበት በውበት የመጣ ውበት ሲረግፍ የሚረግፍ የወረት ተጓዥ ፍቅር ቢባልም ሁኔታን አልፎ የሚሔድ ዘላለማዊ እውነተኛ ፍቅር ነውን በፍጹም ።

ሁለት ሲባል ደግሞ በስጦታ የሚገለጥ የፍቅር አይነት ነው ። የሥጦታው ፍቅር ይባላል። ሥጦታው ሲቀር የሚቀር ሥጦታው ሲያልቅ የሚያልቅ ይህስ ፍቅር ስሙ እንጂ ዘላቂ ነውን በፍጹም “--- ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል።”
— መኃልየ. 8፥7

ሲሰልስ ደግሞ የዝምድና ፍቅር የሚሉት የፍቅር አይነት አለ ። ሰው በሥጋና በደም ስለተቆራኘ የሚዋደደው ፍቅር ማለት ነው።
ይህም ጥል ፣ግጭት፣ አለመግባባት፣ መለያየት ሲፈጠር የሚቀር የፍቅር አይነት ነው ።“ቃየንም ወንድሙን አቤልን፦ ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።”
— ዘፍጥረት 4፥8

የዚህ ሁሉ መንደርደርያ ምክናቴ ቀጣዩን ዘላቂ ዘላለማዊ የማይሻር የፍቅሮች አውራ መሰረት እና ራስ የሆነ ፍቅር መግለጥ ነው ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ እስካለንበት ክፍለ ዘመን ደግሞም ለዘላለም የሆነ አንድ ሰው በንግግር በቃለት ብቻ ሳይሆን በተግባር የገለጠው የፍቅር አይነት ነው ። አጋፔ ፍቅር ይባላል። ፍቅርን ተግባር እንጂ የቋንቋና የቃላት ብዛት በቁልምጫ በማንቆለጳጰስ አይገልጠውም ።ለዚህ ነው ሐዋርያው ዮሐንስ “ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።” ያለው — 1ኛ ዮሐንስ 3፥18

የሰው ልጅ ሊረዳው መርምሮ ሊደርስበት ያልቻለ ሃያል በሰው አዕምሮ የማይገመት የማይመረመር ሐያላንን ነገሥታትን ምሁራንን የገዛ ያንበረከከ ሁንተናዬን የሚማርክ ልዩ እና ድንቅ ፍቅር አጋፔው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ። ይህንን ፍቅር በመስቀል ላይ የገለጠው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ።“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።"
— ዮሐንስ 15፥13

ይህም በአንድ ወቅት የሁሉም ነገር መነሻና ውጤት የነበረው ፍቅር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንድያ ልጁን ስለ ሰው ልጆች ለሞት አሳልፎ የሰጠ እግዚአብሔር አብ ፍቅር ነው ፣ነፍስን በመስቀል ላይ ስለ ሰው ልጆች አሳልፎ እስከመስጠት ፍቅር የገለጠ እግዚአብሔር ወልድ ፍቅር ነው፣ በመለኮት እሳት ፍቅሩን በልባችን ያፈሰሰ የነደደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፍቅር ነው ። “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።”
— ሮሜ 5፥5

የፍጥረት ሁሉ ምንጩ መነሻ አና ፍጻሜ እግዚአብሔር ፍቅር ነው። “እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥16

1ኛ,ፍቅር የሌለው እግዚአብሔር አይወድም ! “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። "
— ዮሐንስ 14፥15-16

2ኛ,በፍቅር የማይኖር እግዚአብሔር አያውቅም !
“ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥8

3ኛ,በፍቅር የማይኖር ትዕዛዙን አይጠብቅም ! “እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።”
— ዮሐንስ 15፥12

4ኛ,“አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።”
— ዮሐንስ 15፥9

“ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥20
164 viewsedited  01:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 04:39:41 #ክህደት #ምንድነው ?

ሰዎች ከያዙት እውነት ሲያፈነግጡ ሌላው ሰው ለምን ይደነግጣል ? ለሰውየው አዝኖ ወይስ እርሱም እምነቱን በጥርጣሬ ስለያዘ ? ክህደት እኛ እንደምናስበው ከአንድ ቤተ እምነት ወደ ሌላ ቤተ እምነት መሄድ ነውን ? ክህደት ማለትስ ምን ማለት ነው?

ባለንበት ዘመን ያለው የአምልኮም የእምነትም ነጻነት ሁሉ እንደልቡ እንዲፈነጭ በር ከፍቶለታል ። በእርግጥ ክህደት አዲስ ግኝት አይደለም፡፡ ሰው ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ የነበረ ያለ እስከፍጻሜ የሚኖር ነው ። ሙሁራኖች ስለ ሰው ልጅ ክህደት ሥነ-ልቦናዊ ትንታኔ ወይም አስተምህሮ ብዙ ገለጻዎች አሏቸው፡፡ ክህደት ዘርፈ ብዙ መገለጫዎች አሉት።

የተቀበሉትን የእውነት እምነት መጣል ፣ የታመኑበትን መክዳት ፣ እስከ ፍጻሜው ሊታመኑ የገቡትን ቃል ማፍረስ ወዘተርፈ ። ሰው በአንድ ጊዜ በውጫዊ ማንነቱ ሌላ ገጽታ በውስጣዊ ማንነቱ ሌላ ገጽታ ሊይዝ ይችላል። ንግግሩና ተግባሩ የሚለያይበት ክህደት አለ “እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።”
— ቲቶ 1፥16

ሰው ላዩን ላዩን በማስመሰል በውስጥ ማንነቱ የሚያደርገው ክህደት አለ :-“የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥5

ቅዱሱ ቃል በእምነታቸው ስለማይጸኑ ሰዎች ሲናገር “በዓለት ላይም ያሉት ሲሰሙ ቃሉን በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ እነርሱም ለጊዜው ብቻ ያምናሉ እንጂ በፈተና ጊዜ የሚክዱ ሥር የሌላቸው ናቸው።”
— ሉቃስ 8፥13

ከፍረሃት የሚመነጭ ክህደት አለ።እውነት መሰዋዕትነት የሚጠይቅ ነው። በመሆኑም ክህደት እውነት የምትጠይቀውን መከራ ላለመቀበል የሚደረግ ውሳኔ ነው ። ጴጥሮስ “እርሱ ግን፦ የምትዪውን አላውቅም አላስተውልምም ብሎ ካደ። ወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣ፤ ዶሮም ጮኸ።”
— ማርቆስ 14፥68

ጌታ ሰዎች ከእምነት ጽናት አንጻር ያሉበትን ደረጃ ያውቃል "በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፦ በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና፤”
— ማቴዎስ 26፥31

በድጋሜ ጴጥሮስ :-“እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን፦ የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ አሉት።እርሱ ግን፦ ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ ይረገምና ይምል ጀመር። ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ።”
— ማርቆስ 14፥70-71

በጌታ የተመረጠው ጥሪ በደረሰው ሰው በሐዋርያው ጴጥሮስ ላይ ይህ ከተከሰተ ከፍረሐት የመነጨ ክህደት ብዙዎችን ሊያገኝ ይችላል።

በተጨማሪም ይህ ውስጣችን የማይተማመን ስብዕናን ሊያመለክት ይችላል ። በውስጣችሁ ያለውን የእውነት ገጽታ በተቃራኒው መቀየር ክህደት ይባላል።

ክህደት ታማኝነትን ለማፍረስ ዋና ከሆኑት ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ክህደት በተቀበሉት እውነት ላይ እምነት ማጣት ነው። እግዚአብሔር ፣ ህብረተሰብ፣ አገር፣ ባልጀራ ፣ ልጅ ፣ ሚስት ወዘተርፈ ክህደት ሊፈጸምባቸው ይችላል ። ክህደት ማለት እውነትን መጣል ነው ።ከእውነት በተቃራኒ ያለውን መቀበል ነው ።

የክህደት ምንጩ ብዙ ነው ። ዓለምን መውደድ እንደ ዴማስ ፣ ጥቅም ፍለጋ እንደ ይሁዳ ፣ ፍረሃት እንደ ጴጥሮስ ፣ እውነት መሰዋዕትነት የሚያስከፍል ሆኖ ሲገኝ ወዘተርፈ የሚፈጸሙ ክህደቶች አሉ
ስለዚህም ክህደት በአንድ ነገር ላይ እምነት ሲጠፋ የሚደረግ ክህደትም አለ። በጥቅምን በመድራዊ ክብር እና ዝና ፍለጋ እውነትን መካድ አለ። ተቀባይነትን ለማግኘት እውነት ወዳለበት ሳይሆን ህዝብ ወደበዛበት ለመሄድ የሚደረግ ክህደት አለ ።

ጌታ ኢየሱስን ክርስቶስ እውነት ነው። ለዚህ ነው ቅዱሱ ቃል:-“ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥22

“ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ እንኳ የለውም፤ በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥23

" መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።" (ዕብራ 6 :-5-6) ይህ ከባዱ እና አስፈሪው መታደስም መመለስም የማይቻልበት ክህደት ነው ።

ስለዚህ አንድ ሰው ከእምነቱ ሲናወጥ ሲክድ እና የያዘውን እውነት ሲጥል ብዙዎች አብረው ይንቀሳቀሳሉ ይህ የሚያሳየው የሰዎቹ እምነት በእውነት ላይ ሳይሆን በከሃዲው ሰው ላይ የተተከለ መሆኑን ነው ።እኛ የተሰበከልን እውነት ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንጂ ሸንበቆ የሆነው የሰው ልጅ አይደለም ተጠንቀቁ ። “ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።”
— ኤርምያስ 17፥5

“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።”
— ገላትያ 1፥8

“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
— ዮሐንስ 14፥6

ስለኛ በሞተው በተቀበረው በሦስተኛውውም ቀን የሞትን ጣር አጥፍቶ በከሙታን በተነሳው በጌታችን በመድኃኒታችን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት አንጽና ከእውነት አንናወጥ ለዚህ እውነት እስከሞት እንጽና ። እኛን ሊያስደስተን የሚገባው ከብዙ ሰዎች ጋር፣ ከሐይማኖት ድርጅትች ጋር፣ ከታዋቂ እና ዝነኛ ሰዎች ጋር መሆን ሳይሆን እውነት ሕይወት መንገድ ከሆነ ጌታ ጋር መሆናችን እና በርሱ በማመናችን ሊሆን ይገባል ። ተባርካችኃል !
118 viewsedited  01:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 07:25:36 ትቀደሱ ዘንድ ፈልጉ !

"… ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።" ( ዕብራ 12:14)


በዘመኑ የምንኖረው ህይወት ፣ የምናመልከው አምልኮ፣ የምናገለግለው አገልግሎት ፣ የምንዘምረው ዝማሬ እና የምንፀልየው ፀሎት በእግዚአብሔር በቃሉም ያልተፈቀደልን ይሆን ?

በእውነት ይህንን ጥያቄ ሁሉም ክርስቲያን ራሱን ሊጠይቅ ይገባል ። ዘመነኛው ክርስቲያን በነዚህ አይነት ህይወት ፈታሽ ጥያቄ ራሱን መጨናነቅ አይወድም። ይሁን እንጂ እነዚህ ጥያቄዎች ወደ መንገዱ ወደ ቃሉ ወደ ፈቃዱ ወደ ቅድስና እንድናቀና የሚያደርጉን ናቸው ።

በመሆኑ ለቃሉ ሰይፍ ለመንፈሱ እሳት በመለኮት ብረሃን ፊት መገለጥ አስደሳች እና ሒሊናን ከሞት ሥራ የሚያጸዳ የከበረ እውነት ነው ። ከእግዚአብሔር ፊት የተሰወረ ምንም የለም ሁሉ በፊቱ የተገለጠ ነው ።

የተቀደሰ ፣በስነምግባር የታነፀ ፣ ከአመጻ የራቀ ፣ በጎ ተጽኖ የሚያመጣ ትውልድ የሚጠበቀው ከቤተክርስቲያን ነው። የክርስትና ሕይወት ግስጋሴ ወግቡ በክርስቶስ ሕይወት መቀረጽ፣ ወደ ሙላቱ ልክ መድረስ እና ክርስቶስን መምሰል ነው። “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።”
( ኤፌ 4፥12-13 )

መቀደስ በቃሉ መቀደስ በመንፈሱ የርሱ ቅዱስ ቤተመቅደስ መሆን ዋናው እንጂ አማራጭ አይደለም ቅዱስ ቃሉ"… ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።" ይላል ( ዕብራ 12:14) በሕይወታችን ትልቅ ግምት እና ስፍራ ልንሰጠው የሚገባው በቅድስና ሕይወት መመላለስን ነው ::

የመዳናችን ሚስጥር የተገለፀው በክርስቶስ ፍፁም ቅድስና ላይ ቢሆንም:: በክርስቶስ የዳነ ሕዝብ የተቀደሰ ህዝብ ነው። ምክንያቱም በደሙ ታጥቦአል ተቀድሶአል አግዚአብሔር በቅድስና የምንመላለስበትን ኃይልና ፀጋ ይሰጠናል:: “የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? ” ( ዕብራ 10፥29) በቅድስና የመመላለሱ ኃላፊነት የእኛ እንደሆነ ይነግረናል::

ነገር ግን ብዙዎች የራሳቸውን ኃላፊነት ከመወጣት በእግዚአብሔር ላይ መጣልን በድል ለመኖር በኛ ለመኖር ለሚሻው ጌታ ከመሰጠትና ከመታዘዝ ይልቅ ለንሰሐ መዘጋጀቱን ይመርጣሉ:: ማንኛውም ክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ቃል ማወቅ ያለበት እውነት በእግዚአብሔር ላይ መጣል የሚገባን ነገር እንዳለ ! ልንፀልይበት የሚገባ ነገር አለ ! እንዲሁ ደግሞ መታዘዝና እርምጃ ልንውስድበት የሚገባ ነገር አለ ::

በቅድስና ለመኖር የእግዚአብሔርንና የእኛን ኃላፊነት ለይተን ማወቅ ይኖርብናል ! ትቀደሱ ዘንድ ፈልጉ እንጂ ልፈልግላችሁ አይልም ::ፈልጉ የሚለው ቃል በእንግሊዘኛው (Pursue) "ተከታተሉ " የሚል ትርጉም አለው :: ይህ የትጋትና የጥረት አስፈላጊነትን ያመለክታል ! ለክርስቲያን የእግዚአብሔር እርዳታ አስፈላጊነት እንዳለ ሆኖ ቅድስናን መከተል ግን የኛ ኃላፊነት መሆኑን በሚገባ መረዳት ይኖርብናል ::

"እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ። ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።"(1ኛ የጴጥ 1:-14-17)
289 viewsedited  04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 05:29:53 ማንም በእርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል።
(ከዶ/ር ግርማ በቀለ ጽሁፍ ያነበብኩት)

ክርስትና ክርስቶስ በኛ የሚኖረው ከሆነ እኛስ በርሱ እንዴት እንኖራለን ስለሚገልጽልኝ ነው :-
በጥንት አበው ዘመን “አማኝ ነኝ” የሚል ሁሉ በርግጥ የመዳኑና የመለወጡ ምልክት የግል ፍተሻ (self-examination) እንዲያደርግ፣ የሽማግሌውና የተወዳጁን ሐዋርያ ዮሐንስን መልእክት ቱንቢ አድርገው ይጠቀሙበት እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያስረዳል። በዚያ ሚዛን የት ይሆን ያለነው - ማለት በሰው ፊት ሳይሆን በጌታ ፊት? የእግዚአብሔር መንግሥት መዝገብ ሳያውቀን፣ በቤተ ክርስቲያን መኖርና ማገልገልም ይቻላል። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነውና! በቤቱ ውስጥ እንክርዳድም አለ። መከር በሚታጨድበትና እውነተኛው ሰብል ከእንክርዳዱ በሚለይበት ዘመን እራሳችንን የት እናገኝ ይሆን? በዚህ ምድር በጌታ ቤት ዘመን ቆጥሮ፣ ምስባኩ ላይ ታይቶና ደምቆ፣ በላይ ግን፣ “ከቶ አላወቅኋችሁም”፣ መባልን ከመሰማት የምናመልጠው አሁን ቀን ሳለ በእግዚአብሔር ፊት በእውነት በመኖር ነው! እስቲ በሐዋርያው ዮሐንስ “የእግዚአብሔርና የዲያቢሎስ ልጆች" ልዪነት መለኪያዎች፣ በግርድፉ ለቅመን ባወጣናቸ 31 መስፍርት እራሳችንን እንይ። ልብ እንበል፣ ዮሐንስ የጻፈው ለአማኞች ነው። “እንግዲህ ልጆች ሆይ፤ እርሱ ሲገለጥ ድፍረት እንዲኖረን፣ በሚመጣበትም ጊዜ በፊቱ እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።” (1 ዮሐ. 2:28)።

1) እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም . . . በጨለማ እየተመላለስን ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል እንዋሻለን፤ እውነትንም አንኖረውም።(1ዮሐ. 1፡5-6)

2) ኀጢአት የለብንም ብንል [በዚህ ምድር በራስችን ፍጹም - perfectionism) ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም (1ዮሐ. 1:8)

3) “እርሱን ዐውቃለሁ” እያለ ትእዛዙን የማይፈጽም ግን ሐሰተኛ ነው፤ እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም (1ዮሐ. 2፡4)

4) ማንም በእርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል። (1ዮሐ. 2:6)

5) በብርሃን አለሁ የሚል፣ ወንድሙን ግን የሚጠላ አሁንም በጨለማ ውስጥ አለ። ነገር ግን ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው (1ዮሐ. 2:9-11)

6) ማንም ዓለምን ቢወድ፣ የአብ ፍቅር በእርሱ ዘንድ የለም፤ (1ዮሐ. 2:15)

7) ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድን የሚያምን ሁሉ አብም አለው። (1ዮሐ. 2:23)

8) ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ ታውቃላችሁ። - (1ዮሐ. 2:29)

9) ኀጢአት የሚያደርግ ሁሉ ዐመፅን ያደርጋል፤ ኀጢአትም ዐመፅ ነው . .በእርሱም የሚኖር ኀጢአትን አያደርግም (ሁን ብሎ ልቡ እያወቀ - perpetual, habitual and intentional sinning) ፤ ኀጢአት የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም። (1ዮሐ. 3:4-6)

10) ኀጢአትን የሚያደርግ (perpetual, habitual and intentional sinning) ከዲያብሎስ ነው:: ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ አንሥቶ [እስከ አሁን] ኀጢአትን የሚያደርግ ነው (1ዮሐ. 3:8)

11) ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን አያደርግም፤ የእርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም። (1ዮሐ. 3:9)

12) የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። (1ዮሐ. 3:10)

13) ፍቅር የሌለው ሁሉ በሞት ይኖራል።ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ። (1ዮሐ. 3:14-15)

14) እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።ማንም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በእርሱ ይኖራል? (1ዮሐ. 3: 16-17)

15) ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።እኛ የእውነት ወገን መሆናችንን በዚህ እናውቃለን (1ዮሐ. 3:18-19)

16) ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን፤ (1ዮሐ. 3:21)
17) ትእዛዞቹንም የሚጠብቁ ሁሉ በእርሱ ይኖራሉ፤ እርሱም በእነርሱ ይኖራል። በእኛ መኖሩን በዚህ ይኸውም እርሱ በሰጠን መንፈስ እናውቃለን። (1ዮሐ. 3:24)

18) የሚወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። የማይወድ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፤ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና (1ዮሐ. 4:7-8)

19) መንፈሱን ስለ ሰጠን፣ እኛ በእርሱ እንደምንኖር እርሱም በእኛ እንደሚኖር እናውቃለን። (1ዮሐ. 4:13)

20) ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምኖ በሚመሰክር ሁሉ፣ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል። (1ዮሐ. 4:15)

21) በዚህም ዓለም እርሱን እንመስላለንና። (1ዮሐ. 4:17)

22) ማንም፣ “እግዚአብሔርን እወደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና። (1ዮሐ. 4:20)

23) እግዚአብሔርን ስንወድና ትእዛዛቱን ስንፈጽም የእግዚአብሔርን ልጆች እንደ ምንወድ በዚህ እናውቃለን፤ (1ዮሐ. 5:2)

24) ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። (1ዮሐ. 5:4)

25) ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። (1ዮሐ. 5:12)

26) ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአት እንደማያደርግ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚጠብቀው፣ ክፉውም እንደማይነካው እናውቃለን። (1ዮሐ. 5:19)

27) እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ መላው ዓለምም በክፉው ሥር እንደሆነ እናውቃለን። (1ዮሐ. 5:19)

28) በክርስቶስ ትምህርት የማይኖርና ከትምህርቱ የሚወጣ ሁሉ አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት የሚኖር ግን አብም ወልድም አለው። (2ዮሐ. 1:9)

29) ልጆቼ በእውነት [እንደ ክርስቶስ] የሚመላለሱ መሆናቸውን ከመስማት የሚበልጥ ደስታ የለኝም። (3ዮሐ. 1:4)

30) ነገር ግን መሪ መሆን የሚወደው ዲዮጥራጢስ [leader in the spirit of anti-Christ) አይቀበለንም። ስለዚህ እኔ ከመጣሁ እርሱ በክፉ ቃላት ስማችንን ለማጥፋት የሚያደርገውን ሁሉ ይፋ አወጣለሁ፤ ይህም አልበቃ ብሎት ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሏቸው የሚፈልጉትን ይከለክላቸዋል፤ ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል። (3ዮሐ.1:9-10)

31) መልካም የሆነውን የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉ የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም (3ዮሐ. 1:11)
150 viewsedited  02:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ