2022-07-24 03:57:04
የመጽሐፍ ቅዱስን ስነ - አፈታትን መረዳት(ለጥያቄ የተሰጠ ምላሽ)።
*ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን በግሎ ያነባሉ? ???
*የግልዎ የፅሞና ጊዜ አለዎትን ???
*ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተቆራኘ ሕይወት እንዲኖሮት ይፈልጋሉ ???
*በቅዱሳን ሕብረት የቃሉ አገልጋይ መሆን ይፈልጋሉን ???
" የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ። በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።"(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፥16)
የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ - አፈታት / ስነ - ትርጓሜ / ዘዴ
1ኛ, መመልከት /Observation /
በዚህ ውስጥ
መቼ ተፃፈ? - የጊዜ አመልካች
ማን ፃፈው? - ጸሐፊውን አመልካች
ለማን ተፃፈ ?- ተደራሲያንን አመልካች
የት ተፃፈ ? - የቦታ አመልካች
እንዴት ተፃፈ? - ሁኔታን አመልካች
ለምን ተፃፈ? - ምክንያትን አመልካች
*ማን? ተናጋሪው ማነው? የሚነገርለትስ?
*ምን? ርዕሱ ምንድነው ቅደም ተከተሉስ?
*የት? ድርጊቱ እየተከናወነ ያለው የት ነው?
*መቼ? ድርጊቱ የተፈፀመው መቼ ነው?
* እንዴት? የተደረሲያን ምላሽ እንዴት ነበር?
2ኛ, መተርጎም / Interpretation /
*በምልከታው ያገኘነውን ሙሉ መረጃ መሠረት በማድረግ ወደ ትርጉም እንገባለን ። የመተርጎም ዓላማ በዘመኑ ለተጻፈላቸው ተደራሲያን ሊተላለፍ የተፈለገውን ትክክለኛ መልዕክት ማግኘት ነው። በመሆኑም በመተርጎም ሒደት የምንጠይቃቸው ቁልፍ ጥያቄዎች :-
* በምልከታው ቁልፍ ጥያቄዎች የተረዳሁት ምንድነው?
* ያነበብኩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለምንድነው የሚናገረው?
*በክፍሉ ትኩረት የተሰጠው ነገር ምንድነው?
*በዘመኑ የተጻፈላቸው ሰዎች ያሉበት ሁኔታ ምን ይመሥላል?
*የተላለፈላቸው መልዕክት እንዴት ተቀበሉት?
*ተደራሲያኑ ለመልዕክቱ የሰጡት ምላሽ ምን ነበር?
*በመታዘዛቸው ያገኛቸው በረከት ምንድነው?
* ባለመታዘዛቸውስ ምን አጋጠማቸው?
*ይህ ክፍል የተጻፈበት ዓላማ ወይም ምክንያት ምንድነው?
*በክፍሉ እግዚአብሔር ለተደራሲያኑ ሊናገር የፈለገው ዋና መልዕክት ምንድነው?
3ኛ,ማዛመድ /Application /
* በትርጉም ውስጥ ያገኘነውን መልዕክት በመያዝ በማዛመድ ሒደት ልንጠይቃቸው የሚገቡንን ቁልፍ ጥያቄዎች ።
*መልዕክቱ ከህይወቴ ጋር ምን ግኑኝነት አለው?
* መልዕክቱ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ያዘኛል?
* በመልዕክቱ የተሰጠኝ ተስፋ ምንድነው?
*መልዕክቱ አሁን ካለሁበት ሁኔታ አንጻር ለኔ ምን መልዕክት አለው?
* በክፍሉ ልርቀው ወይም ልከተለው የሚገባኝ ምሳሌ ምንድነው?
* በክፍሉ የተሰጠኝ የተስፋ ቃል የሚጠይቀው ቅድመ ሁኔታ አለ ወይ?
* በክፍሉ መታዘዝ/አለመታዘዝ/በሕይወቴ ሊያስከትለው የሚችለው ውጤት ምንድነው?
*መንፈስ ቅዱስ በተረዳሁት መልዕክት መሠረት የሚሰጠኝ አመራር ምንድነው?
*ያነበብኩት የመጽሐፍ ክፍል የተረዳሁት መልዕክ ከግል ህይወቴ ከቤተሠብ ከቤተ ክርስርስቲያን ከአገር አንጻር ምን የሚሰጠኝ መልዕክት አለ? እንዴትስ ሊዛመድ ይችላል?
በዘመኑ ካለው ስህት ለመጠበቅ አውዳዊ እና ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ይማሩ ያኔ አሳውን ሰው እያጠመደ ከሚያበላዎ ለራስዎ አጥምደው መብላት ይጀምራሉ !!!
16 views00:57