Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-11 08:07:55 *** አዋዋልክን አሳምር ***

አንተ ማለት የምትውልበት ቦታ እና ሁኔታ ውጤት ነህ። ከቢዝነስ ሰዎች ጋር ከዋልክ አስተሳሰብህና ተግባርህ የቢዝነስ ሰው ዓይነት ይሆናል። ከአርቲስቶች ጋር ከዋልክም እንዲሁ አስተሳሰብህና ወሬህ ሁሉ የአርቲስት ይሆናል። ከሱሰኞች ወይም ከሌሎች ጋር ከዋልክም እንዲሁ።

“ከአህያ የዋለች ጊደር …” እንደሚባለው አንተም የውሎህ ውጤት ነህ። አዋዋልክን አሳምር ወዳጄ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
58 viewsTefera Muluneh, 05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 08:06:58
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
58 viewsTefera Muluneh, 05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 09:19:04 *** ሰው ባያደንቅህ አትገረም! ***

አንድ የሚያምር ነገር ብታደርግና ማንም ባይመለከተው አትከፋ። ለፀሐይ ሁልጊዜ ማለዳ ስትወጣ የሚያምር ትዕይንት አላት ነገር ግን አብዛኛው ተመልካች እንደተኛ ነው። ካነበብኩት

ፀሐይ ስትወጣ የሚኖራትን የሚያምር ገጽታ ሁሉም ሰው አይመለከተውም። ፀሐይም በዚህ ተቀይማ በየቀኑ መውጣቷን እና ያንን የሚያምር ገጽታዋን ማሳየቷን አትተውም።

አንተም የምታደርገው ነገር ሁሉ ሌሎች አይተው ቢያደንቁልህና ቢያበረታቱህ መልካም ነው። ነገር ግን ሰዎች ሁልጊዜ የአንተን ጥረትና ድካም ላይረዱ ወይም ከነጭራሹ ላይመለከቱህም ይችላሉ። አንተ ግን የምታከናውነው ለዓላማህ ነውና መስራትህን አታቋርጥ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
136 viewsTefera Muluneh, 06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 09:14:58
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
133 viewsTefera Muluneh, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 08:50:53 *** ልደትህ መቼ ነው? ***

የልደትህ ቀን ሲደርስ የሚሰማህ ምንድነው? ብዙዎቻችን የልደታችንን ቀን በጉጉት ነው የምንጠብቀው። እና በደስታና በፌሽታ እናሳልፈዋለን።

አንድ ጓደኛዬ “ሰው ለምንድነው ልደቱን በደስታና በፌሽታ የሚያሳልፈው? እንዲያውም ልደቱን ባከበረ ቁጥር በዚህ ምድር ከሚኖረው ቆይታ በአንድ አመት እየቀነሰ እና ወደ ህይወት ፍፃሜው እየተቃረበ በመሆኑ ሊያዝን ነው የሚገባው” ይላል።

እውነት ነው! በየቀኑ ከእድሜያችን ላይ በ24 ሰዓት እንቀንሳለን፤ በየወሩ በ30 ቀናት እንቀንሳለን፤ በየዓመቱ ደግሞ ከእድሜያችን ላይ አንድ ዓመት እንቀንሳለን። እንዲህ እንዲህ እያልን ወደ ፍፃሜያችን እንደርሳለን።

ዋናው ጉዳይ የህይወት ጊዜያችን ከመጠናቀቁ በፊት ምን ቁምነገር እየሰራን ነው? የሚለው ነው። በኋላ ጊዜ አልቆ ምንም ማድረግ በማንችልበት ሰዓት ይህንን ባደርግ ኖሮ የሚለው ሃሳብ ጥቅም የለውምና ወዳጆች ሆይ በጊዜ እንንቃ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
160 viewsTefera Muluneh, 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 08:47:28
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
153 viewsTefera Muluneh, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 08:29:45 *** ጠዋትህ ልክ እንደፈገገታህ! ***

ጠዋትህ ልክ እንደፈገግታህ ብሩህ እና የሚያምር ነው! ጠዋትህን በፈገግታ ካልጀመርክ ግን ቀንህ ልክ እንደፊትህ ጨፍጋጋ ይሆንብሃል። ቀንህ ያንተ ምርጫ ነው ማለት ነው።

ያማረ ውሎ እንዲኖርህ የምትፈልግ ከሆነ ጠዋትህን በፈገግታ እና በምስጋና ጀምር። ደስተኛ አመስጋኝ ሰው ተጨማሪ ደስታ እና የምስጋና በረከትን ያገኛል። እናም ቀንህን በፈገግታ ጀምር!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
169 viewsTefera Muluneh, 05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 08:28:00
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
162 viewsTefera Muluneh, 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 08:21:59 *** ስህተት የማደግ ዕድል ነው! ***

ብዙዎቻችን መሳሳትን እንፈራለን ወይም እንጠላለን። ይሁን እንጂ እኛ ሰዎች በመሆናችን መሳሳታችን የማይቀር ነገር ነው።

በሌላ በኩል ካየነው ደግሞ መሳሳት ሌላ ተጨማሪ መንገድ ለመማር እድል የሚሰጠን ነገር ነው። ካልሞከርን እና ካልተሳሳትን ትክክለኛውን መንገድ ልናውቅ አንችልም። እዚህ ላይ ዋናው ጉዳይ መሳሳት አይደለም። ስለተሳሳትን ሌላ መሳሳትን በመፍራት ወይም በመጨማቀቅ ከመሞከር እንቆማለን ወይስ ሙከራችንን እንቀጥላለን? የሚለው ነው።

ወዳጆች ሆይ ስኬት የሚመጣው በመሞከር፣ በመሳሳት እና እንደገና በመነሳት ነው።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
197 viewsTefera Muluneh, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 08:21:59
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
173 viewsTefera Muluneh, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ