Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-02 09:23:43 *** ህይወት እያንኳኳች ነው ***

ህይወት ስታንኳኳ ሁለት ምርጫ አለህ። ተኝተህ መቆየት ወይም መነሳት። ቶም ክራስ

ህይወት እያንኳኳች ነው። ኑሮ ሲጨምር ራስህን እንድታሻሽል እየገፋፋችህ ነው። ትራስፖርት አጥተህ ስትቸገር ጠንክረህ በመስራት የራስህ መኪና እንዲኖርህ እየጎተጎተችህ ነው።
ሰዎች ዝቅ አድርገው ሲመለከቱህ ወይም ትኩረት ሲነፍጉህ ራስህን እንድትለውጥና ከፍ ብለህ እንድትገኝ እየነገሩህ ነው።

ህይወት ስታንኳኳ አቤት በላት! ፈጥነህ ተነስላት!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
210 viewsTefera Muluneh, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 09:23:43
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
202 viewsTefera Muluneh, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 09:47:44 *** ቀሪው ህይወትህን ምርጡ ህይወትህ አርድገው!***

"ቀሪው ሕይወቴን ከሕይወቴ የተሻለ ለማድረግ መርጫለሁ." - ሉዊዝ ሄይ

እስካሁን የመጣህበት መንገድ ምናልባትም ብዙ ጠመዝማዛና ውጣውረድ የበዛበት ሊሆን ይችላል። ምናልባትም እምቅ አቅምህን ተጠቅመህ የምትፈልገውን አይነት ህይወት መኖር ገና ያልጀመርክ ሊሆን ይችላል። ይሁንና ከዛሬ ጀምሮ ህይወትህን እንደና እንደ አዲስ መምራት ትችላለህ።

ቀሪው ህይወትህን ከእስካሁን የተሻለ ለማድረግ መወሰንና ውሳኔህን ማክበር ከቻልክ እውነትም ቀሪው ህይወትህ የህይወትህ ምርጡ ጊዜ ይሆናል።

ቀሪ ህይወትህን ምርጥ ለማድረግ ወስን ወዳጄ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
205 viewsTefera Muluneh, 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 09:42:17
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
190 viewsTefera Muluneh, 06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 08:52:55 *** ጽናት ያስፈለገህ ህልምህ ትልቅ ስለሆነ ነው! ***

ህልምህ ትልቅ ሲሆን የምትጓዘው ረጅም ነው ማለት ነው፤ ለመገለጥና ውጤቱም ለመታየት ጊዜ ይወስዳል ማለት ነው፤ ፈተናዎችና እንቅፋቶች ይበዛሉ ማለት ነው።

አየህ ፈተና እየበዛብህ ከሆነ ጉዞህ ረጅም መድረሻህም ትልቅ ነው ማለት ነው። እናም ፈተናዎችህን በሙሉ ለማለፍ ጽናት የሚባል የስኬት ጥበብ ሊኖርህ ይገባል።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
216 viewsTefera Muluneh, 05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 08:51:03
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
206 viewsTefera Muluneh, 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 08:59:48 *** ምን ዓይነት ልዩነት ማምጣት ትፈልጋለህ! ***

የምትሰራ ሥራ ልዩነትን ማምጣት ይችላል። እናም ምን ዓይነት ልዩነት መፍጠር እንደምትፈልግ መወሰን አለብህ።"—Jane Goodall

ማንኛውም ሰው በሚሰራው ሥራ ልዩነትን ማምጣት ይችላል። አንተም አንድ የተለየና ጠቃሚ ነገር በማድረግ የራስህን አሻራ ማሳረፍ ትችላለህ።

ይሁንና ምን ብታደርግ ነው የራስህን አሻራ ማሳረፍ የምትችለው? በተለየ መንገድ ካላከናወንከው በስተቀር ማንኛውን ሰው የሚያደርገውን ነገር በማከናወን ልዩነት ልትፈጥር አትችልም።

አየህ ወዳጄ አንተ አንደማንኛውም ሰው… ሰው ብትሆንም አንድ የተለየ ነገር በማድረግ የራስህን የተለየ ስጦታ ትገልጥ ዘንድ ብቃቱ እና አቅሙ ተሰጥቶሃል። እናም ያ አንተ ልታደርገው የምትችለው ነገር ምንድነው? … ይህንን ጥያቄ ስትመልስ በትክክል አሻራህን ማኖር ትጀምራለህ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
64 viewsTefera Muluneh, 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 08:57:54
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
67 viewsTefera Muluneh, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 08:27:04 *** በጽናት አንኳኳ ***

በጽናት የሚያንኳኳ የሚያቆመው በመግባት ነው። መሐመድ አሊ

ወዳጆች ሆይ የምትፈልጉትን በጥንቃቄ ምረጡ። ከመረጣችሁ ደግሞ በጽናት ለፍሬ አብቁት። ዋናው ነገር ማለም ወይም ማቀድ አይደለም፤ በጽናት መንገዱን መጓዝ እንጂ።

ጽናት ካለህ በስኬት ጎዳና ያሉ እንቅፋቶች አያደናቅፉህም፤ ፈተናዎች አያስቆሙህም፤ እናም የምታቆመው ጎዳናው በድል ሲጠናቀቅ ብቻ ነው!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
146 viewsTefera Muluneh, 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 08:22:47
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
150 viewsTefera Muluneh, 05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ