Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 57

2022-07-07 09:00:19
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
346 viewsTefera Muluneh, 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:50:22 *** የራስህን ታሪክ ራስህ ፃፈው! ***

የራስህን የህይወት ታሪክ ራስህ ፃፈው እንጂ ሌሎች እንዲጽፉልህ አትፍቀድ የምትለው ኦፕራ ዊንፍሬይ ነች።

ራስህ ልትኖረው የምትፈልገውን የህይወት ስክሪፕት መፃፍ ያለብህ አንተው ነህ። ግን ግን አንተ ልትጽፈው ካልወደድክ የግድ ሌሎች ሰዎች ይጽፉልሃል። ይሁንና ያ ሌሎች የፃፉልህ የህይወት ታሪክህ የሚያኮራህ ወይም የሚያስደስትህ ሊሆን አይችልም።

ወዳጄ ሆይ የራስህን የህይወት ታሪክ ራስህ ለመፃፍ ተነስ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
333 viewsTefera Muluneh, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:47:40
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
330 viewsTefera Muluneh, 04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:49:47 *** በተመሳሳይ መንገድ አትጓዝ! ***

እስካሁን በመጣህበት መንገድ እየተጓዝክ በህይወትህ ላይ ሌላ አዲስ ነገር እንዲከሰት አትጠብቅ።

ሁልጊዜ በምትጓዝበት መንገድ ስትመላለስ የምታገኘው ነገር ወይም የምትደርሰው ያው የምታውቀውና የለመድከው ቦታ ነው። የምትጓዝበትን መንገድ ስትቀይር ግን ሌላ አዲስ መዳረሻ ሌላ አዲስ ቦታ ላይ ትደርሳለህ።

አየህ ወዳጄ አስተሳሰባችን ለእኛ ልክ እንደዚህ ነው። እስካሁን የነበረን አስተሳሰብ አሁን ላለንበት ሁኔታ አድርሶናል። አሁን ያለንበትን ሁኔታ ካልወደድነውና መቀየር ከፈለግን አስተሳሰባችንን መቀየር የግድ ያስፈልገናል።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
351 viewsTefera Muluneh, 04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:46:57
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
412 viewsTefera Muluneh, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 07:07:46 *** ስኬትም ውድቀትም ! ***

ስኬት መጨረሻ አይደለም። ውድቀትም አበቃልን ማለት አይደለም። ይልቁንም እንደገና ለመቀጠል ድፍረት የሚሰጠን ነገር ነው ይለናል ዊንስተን ቸርችል።

አንዳንድ ሰዎች በትንንሽ ስኬቶች በመርካት ከትልቁ ህልማቸው ሲደናቀፉ እናያለን። ውድቀት መጥፎ የሚሆነውም ያን ጊዜ ብቻ ነው።

ካልሆነ ግን ውድቀት እንደገና በአዲስ ወኔ እና ብልሃት የመነሳት እድል ይሰጠናል እንጂ ወድቀን እንድንቀር አያደርገንም።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
367 viewsTefera Muluneh, edited  04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 07:06:11
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
975 viewsTefera Muluneh, 04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 09:25:47 *** የህይወትህ ዳመና! ***

ዳመና በህይወቴ እየተንሳፈፈ ይመጣል፣ የሚመጣው ዝናብ ለመሸከም ወይም ማዕበል ለማምጣት አይደለም፣ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ፀሐይ ስትጠልቅ የህይወቴን ሰማይ በቀለማት ለማድመቅ ነው። Rabindranath Tagore

በህይወታችን የሚመጣው ዳመና ሁሉ ወይም ጨለማ ሁሉ ለክፋት ወይም ለመጥፎ እድል አይደለም። በህይወታችን አንድ የሆነ ጣዕም ወይም ቀለም ለመጨመር ነው።

እናም መጥፎ ጊዜያትን በማማረር ሳይሆን በመልካም እድልነታቸው እንመልከታቸው። በእነዚያ ጊዜያት ውስጥ ምን መልካም ነገር አለ? ብለን እንጠይቅ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
369 viewsTefera Muluneh, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 09:21:06
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
350 viewsTefera Muluneh, 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 07:53:41 *** ተስፋ አትቁረጥ! ***

በዚህ ምድር ላይ ተስፋ እንደአለመቁረጥ ያለ ሃያል ነገር የለም። ምክንያቱም ተስፋ የማትቆርጥ ከሆነ ሙከራህን ትቀጥላለህ። ሙከራህን ከቀጠልህ ደግሞ ታሸንፋለህ። አየህ የማሸነፍ ምስጢሩ ተስፋ አለመቁረጥ ነው።

ተስፋ የሚቆርጡ ምንም አያገኙም። አንተ ግን ወዳጄ አሸናፊ ሆነህ ተፈጥረሃልና አሸናፊነትህን ለማረጋገጥ ተስፋ አትቁረጥ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
366 viewsTefera Muluneh, 04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ