Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 51

2022-08-07 07:59:14 *** አንዳንድ ጊዜ … ***

ስኬታማ ለመሆን አንዳንድ ጊዜ መከራን መጋፈጥ ሊኖርብህ ይችላል። ዚግ ዚግላር።

ወደ ስኬት የምታደርገው ጉዞ ሁልጊዜ የተመቻቸ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ስኬታማ ለመሆን ብዙ መናወጥ እና የማያቋርጥ ፈተና፤ በውስጥም ሆነ በውጭ ፈጣን የሆኑ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች፤ እርግጠኛ ልትሆንባቸው የምትችላቸው ነገሮች በሙሉ ማጣት፤ በሰዎች ዘንድ መገለል፤ … ሌላም ሌላም ሊያጋጥም ይችላል።

እናም ያ የምትፈልገው ስኬት እነዚህን ሁሉ ማለፍ ስትችል የሚሰጥህ ሽልማትም ሊሆን ይችላል። አየህ የምትፈልገውን ለማግኘት ይህን ሁሉ ማለፍህ ግድ ይሆናል። የእነዚህ ነገሮች መከሰት የአንተን የዓላማ ጽናት የሚፈታተን ወይም ጥርጣሬ እንዲገባህ የሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ እንድትገባ የሚያደርግ ቢሆንም በማስተዋል ልትሐሻገራቸው ከቻልክ … በቃ ስኬት የአንተ ነች!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
326 viewsTefera Muluneh, 04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 07:55:52
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
221 viewsTefera Muluneh, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 07:35:51 *** ትልቅ ሆኖ የተፈጠረ የለም! ***

ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም፤ ነገር ግን ታላቅ ለመሆን ግን መጀመር አለብህ። ዚግ ዚግላር።

ማንም ወደ ዚህች ምድር የመጣ ሁሉ ትልቅ ሆኖ አልተወለደም። ነገር ግን ትልቅ ለመሆን በማለሙና በመስራቱ ምክንያት ትልቅ የሆኑ ሰዎች አሉ።

አንተም አሁን ያለህበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምንም የተፈጠርከው ትልቅ የመሆን ሙሉ አቅምን ይዘህ ነውና አሁኑኑ ትልቅ የመሆን ጉዞህን መጀመር ትችላለህ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
344 viewsTefera Muluneh, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 07:28:44
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
252 viewsTefera Muluneh, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 08:41:13 *** ስኬትህን ፍጠረው! ****

በአዕምሮየ ሊፀነስ ከቻለ፤ ልቤ ሊያምነው ከቻለ፤ ማሳካት እችላለሁ። መሐመድ አሊ።

ስኬትህን በአዕምሮህ ፍጠረው! በልብህም እንደሚሳካልህ እምነት ይኑርህ! ከዚያ እንዳይሳካ እንቅፋት የሚሆንብህ አንዳች ነገር እንደሌለ ታያለህ!

ወዳጄ ሆይ ስኬትህን አሁኑ ፍጠረው! … የምትፈልገውን አልም … እዚያ እንዴት ልትደርስ እንደምትችል እቅድ አዘጋጅለት! … እንደምታሳከው ከልብህ እመንና ሥራህን ጀምር! … በቃ ስኬትህ ያለው ከውስጥህ ነው! … ከውስጥህ አውጣውና እውን አድርገው!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
31 viewsTefera Muluneh, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 08:39:03
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
37 viewsTefera Muluneh, 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 08:30:15 *** የሽንፈት ልብስ እና የስኬት መሰላል ***

የሽንፈትን ልብስ ለብሰህ የስኬትን መሰላል መውጣት አትችልም። ዚግ ዚግላር።

በመሰላል ሽቅብ ወደላይ እየወጣህ ስለመውደቅ የምታስብ ከሆነ ምንም ያህል መሰላሉ አስተማማኝ ቢሆንም ተንሸራተህም ይሁን በሌላ መንገድ መውደቅህ አይቀርም።

አየህ ስለ መውደቅ እያሰብህ እና በመውደቅ አስተሳሰብ ውስጥ ሆነህ፣ እንደሚሳካልህ በውስጥህ እምነት ሳይኖርህ የስኬትን መሰላል መውጣት በጣም አስቸጋሪ ነው። እናም ወዳጆች ሆይ የስኬትን መሰላል እየወጣችሁ ስለመውደቅ በፍፁም ማሰብ የለባችሁም። ምክንያቱም ስኬታችሁ የሃሳባችሁ ውጤት ነውና!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
26 viewsTefera Muluneh, edited  05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 08:19:28
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
38 viewsTefera Muluneh, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 07:20:48 *** በደረስክበት አመስግን! ***

መጓዝ የምትፈልገው ረጅም ቢሆንም፤ እንዲኖርህ የምትፈልገው ብዙ ቢሆንም፤ መሆን የምትፈልገው ትልቅ ቢሆንም አሁን በደረስክበት እና አሁን ባለህበት ሁኔታ ማመስገን አለብህ።

የምታልመው ቦታ ወይም የስኬት ደረጃ ላይ የምትደርሰው አሁን ባለህና በደረስክበት አመስጋኝ ስትሆን ነው። ስታመሰግን ሌላ እንድታመሰግን የሚያደርግህን ለውጥና እድገት ታገኛለህ። እናም በደረስክበት እና ባለህ አመስጋኝ ሁን!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
215 viewsTefera Muluneh, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 07:15:14
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
234 viewsTefera Muluneh, 04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ