Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-08 12:16:12 *** ስትጋልብ ፍረጥ! ***

በቀለ መኮነን(መልህቅ መጽሐፍ ርዕሱ የተቀየረ)
የሕህወት ጎዳና ገፁ ሲለወጥ፣
በጭነት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ፣
የእንቅፋት አፅሙ ቋጥኝ ሲገለጥ፣

ሸክም ዘንቦብህ ትቢያው ሲላቆጥ፣
ሲሆን ድጥ በድጥ፣
ሾህ ጭቃ ቅይጥ፣
ልብህ አይደንግጥ።
በምኞት ቅዠት በስጋት ርዶ፣
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ፣

ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ፣
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሽምጥጥ።
አያረጅ የለም አይለዋወጥ፣
ነገን ተማምነህ በመጓዝ ቁረጥ፤
እሩቅ አልመህ ቅርብ አትርመጥመጥ፤
ሰግተህ ከምትቆም ስትጋልብ ፍረጥ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
215 viewsTefera Muluneh, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 12:15:53
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
191 viewsTefera Muluneh, 09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 08:47:20 *** ማንነትህ የሚለካው በቆምክለት ዓላማ ነው! ***

ምናልባትም አሁን ያለህበት ደረጃ ከጋደኞችህ ያነሰ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን አሁን ያለህበት ሁኔታ የአንተን ማንነት አይለካም። የአንተ ማንነት የሚለካው አንተ ባለህ ዓላማ እና ለዓላማህ እያደረከው ባለው ነገር ነው።

“ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ” እንደሚባለው ዓላማህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
142 viewsTefera Muluneh, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 08:44:39
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
141 viewsTefera Muluneh, 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 08:46:56 *** አጥብቀህ ተጨነቅ ***

ማንም ያልተጨነቀ ዓለምን አይለውጥም። —Billie Jean King

ስንምንም ስለማንም ምንም የማታስብ ከሆነ ምንም አዲስ ነገር አትፈጥርም። አዲስ ነገርን የሚፈጥሩ ሰዎች ስለዚያ ጉዳይ አብዝተው የሚያሰላስሉ፣ የሚያስቡ እና አጥብቀው የሚጨነቁ ናቸው።

አናም ወዳጄ ሆይ ህይወትህን፣ በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን እና ዓለምን መለወጥ ትችላለህ። ሆኖም ግን ማሰብና መጨነቅ ይኖርብሃል።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
133 viewsTefera Muluneh, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 08:46:01
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
133 viewsTefera Muluneh, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 08:47:45 *** ሰው ስላንተ ምን እያለ ነው? ***

“የሞተን ውሻ ማንም አይደበድበውም!” ዴል ካርኒጌ።

ምንም ካልሰራህ ማንም ምንም አይልህም። መንቀሳቀስ ስትጀምር ግን የሚተቹህ፣ በነገር የሚጎነትሉህ፣ የሚሰድቡህ፣ የሚጠቋቆሙብህ … ይበዛል። ይህ ለአንተ የማደግህ ምልክት ነው። እየተንቀሳቀስክ ለመሆንህ ጠቋሚ ነው።ጥሩ እየሰራህ ነው ማለት ነው።

እናም ወዳጄ ሆይ ሰዎች ምን አሉኝ ብለህ እንቅስቃሴህን አትግታው። ይልቁንም ጠንክረህ ግፋበት።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
179 viewsTefera Muluneh, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 08:43:42
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
170 viewsTefera Muluneh, 05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 09:04:26 *** የማይተካ ሁን! ***

"የማይተካ ለመሆን አንድ ሰው ሁልጊዜ የተለየ መሆን አለበት." —Coco Chanel

ሁሉም ሰው የሚያደርገውን ነገር እያደረግህ ምንም የተለየ ነገር መፍጠርም ሆነ የተለየ ሆነህ በሌሎች ዘንድ መታየትና መታወስ አትችልም።

ይሁንና የተለየ ነገር የምታደርግ ከሆነ አንት በዚህ በምታደርገው የተለየ ነገር ከሌሎች በልጠህና ልቀህ ትታያለህ፤ በሌሎች ሰዎች ዘንድ በተለየ መንገድ ትታወሳለህ፤ በዚያ በምታደርገው ነገር ሁልጊዜም በሌላ በማንኛውን ሰው የማትተካ ትሆናለህ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
204 viewsTefera Muluneh, 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 09:03:10
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
182 viewsTefera Muluneh, 06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ