Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-25 08:14:17 *** ምርጡ ጊዜ ***

የስኬትን መንገድ ለመጀመር ምርጡ ጊዜ መቼ ነው? ብዙዎቻችን ዛሬ ነገ እያልን የስኬታችንን ጊዜ እናረዝማለን። ሁልጊዜ እናቅዳለን፤ ግን ወደ ተግባር አንቀይረውም።

ዕቅዳችንን ወደ ተግባር ለመቀየር እና የስኬትን መንገድ ለመጀመር ምርጥ የሚባል ጊዜ የለም። ካለም እሱ ዛሬ ነው። እናም የስኬት ጊዜህን ዛሬውኑ ጀምረው!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
142 viewsTefera Muluneh, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 08:13:27
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
141 viewsTefera Muluneh, 05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 08:13:29 *** ደስታ እና ሌሎችን ማገልገል ***

ተኛሁ እናም ህይወት ደስታ እንደሆነ ህልም አየሁ፤ ነቃሁ እናም ህይወት ሌሎችን ማገልገል እንደሆነ ተመለከትኩ፤ ወደ ተግባር ገባሁ እናም እነሆ ደስታ ሌሎችን ማገልገል ነበር። - Rabindranath Tagore

ደስታ በአጋጣሚ የምናገኘው ስጦታ አይደለም፤ ደስታን መሻትና እና ለማግኘት መጣር ያስፈልጋል። ዋናው ነገር ደስታን የት እንደምናገኘው ማወቁ ላይ ነው።

ደስታ በደረስንበት የዕውቀት፣ የስኬት፣ የሀብት … ደረጃ የሚለካም አይደለም። እውነተኛ ደስታ ያለችው ሌሎችን በመርዳት፣ በማገልገል እና ስለሌሎች በመኖር ውስጥ ነው።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
159 viewsTefera Muluneh, 05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 08:12:30
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
153 viewsTefera Muluneh, 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 07:33:47 *** በጣም ውድ መሆን ይኖርብሃል! ***

ሰዎች በፈለጉት ጊዜ የሚያገኙህና ወደ ፈለጉት የሚወስዱህ ርካሽ ልትሆን አይገባህም። አንተ ማለት የራስህ ማንነት ያለህ፤ ብዙ አቅምና ችሎታ ኖሮህ ብዙዎችን የምትጠቅም እና ይህንን ችሎታህን በማውጣት የተጠመድክ በጣም ውድ ሰው ነህ። እናም ሰዎች ወደፈለጉት አቅጣጫ እንደፈለጉ የሚያገኙህ ወይም የሚጎትቱህ አይደለህም።

በራስህ ዕቅድ ብቻ በመመራት እና ውጤታማ በመሆን አንተን ለማግኘት ለሚፈልጉ ሁሉ በጣም ውዱ ሰው ልትሆን ትችላለህ። እናም አሁን ሁሉም ነገር ተወዶ ሰው ብቻ ርካሽ በሆነበት አለም አንተ ለራስህ ውድ የሆነ ማንነትን በመገንባት ሁሉንም አስደምም!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
102 viewsTefera Muluneh, 04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 07:33:47
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
115 viewsTefera Muluneh, 04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 09:21:42 *** በህይወትህ ደስተኛ ነህን? ***

በህይወትህ ደስተኛ ሳትሆን በሥራህ እውነተኛ ደስታን ልታገኝ አትችልም። - Heather Schuck

ህይወትህ በደስታ የተሞላ ይሆን ዘንድ ሥራህ የህይወትህ አካል እንዲሆን አድርገው። ስራህ በህይወትህ የምትፈልገውን እና የደስታህ ምንጭ የሆነውን ጉዳይ ለማናወን እና ለማግኘት የሚያስችልህ ከሆነ ሥራህ የህይወትህ አካል ይሆናል።

ወዳጄ ሆይ በህይወትህ ልታሳካው የምትፈልገውን ለይተህ ሥራህ ይህንኑ የሚያሳካልህ መሳሪያህ እንዲሆን አድርገው። ያንጊዜ በሥራህ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
57 viewsTefera Muluneh, 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 09:21:42
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
58 viewsTefera Muluneh, 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 10:38:44
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
134 viewsTefera Muluneh, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 07:42:49 *** በጣም የሚያሳስብህ ምንድነው? ***

የራስህን መንገድ ፈልግ፣ በጣም የሚያሳስብህ ወይም የሚያበሳጭህ ጉዳይ ተረዳ፣ እናም ይህንን ስሜትህን ጠብቀው። የምትፈልገውን ሁሉ ማግኘት አትችልም። ነገር ግን ለአንተ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ልታገኝ ትችላለህ። እናም በዚህ መንገድ ማሰብ ለረጅም ጊዜ ጠንክሮ መስራት የሚያስችልህን ኃይል ይሰጥሃል። - Marissa Mayer

ሁሉንም ለማግኘት መፍጨርጨር ግን ሁለት ያባረረ አንድ አይይዝም የሚባለውን ይሆንብሃል። ወዳጄ ሆይ ይበልጥ ልታገኘው የምትፈልገው፣ ይበልጥ ስሜትህን የሚገዛው፣ ይበልጥ ራስህን ልትሰጠው የሚገባህ፣ ይበልጥ የአንተ መሆን የሚገባው ጉዳይህ ምንድነው?

ጊዜህን፣ ጉልበትህንና ዕውቀትህን ይበልጥ የምትፈልገው ጉዳይ ላይ አድርግ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
254 viewsTefera Muluneh, 04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ