Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-06 09:54:35 *** ህይወትህን በየቀኑ መርምር! ***

ህይወት ያለ ዓላማ ደካማና ማረፊያ የለሽ ናት። በየቀኑ ለራሳችን ዛሬ አንድ አዲስ ነገር መጀመር አለብኝ እንበል፤ በየቀኑ የህይወት ዓላማችንን እንመርምር። – Thomas Kempis

በየቀኑ በህይወታችን አዲስ ነገር ማድረግን እንልመድ፤ አዲስ ነገርን በህይወታችን እንጨምር፤ … ይህ ሲሆን ህይወታችን ሙሉና ደስተኛ ይሆናል።

ወዳጄ ሆይ በህይወትህ ምን አዲስ ነገር እየፈጠርህ ነው? ምን አዲስ ነገርስ የህይወትህ አካል እንዲሆን እያደረግህ ነው?

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
69 viewsTefera Muluneh, 06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 09:54:14
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
71 viewsTefera Muluneh, 06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 08:55:38 *** የዕለቱ ጠቃሚ ጊዜያችን! ***

ሁልጊዜ ማለዳ የዕለቱ በጣም ጠቃሚ ጊዜያቸን ነው። ምክንያቱም ጠዋታችንን የምናሳልፍበት መንገድ ቀኑን ሙሉ ምን ዓይነት ጊዜ ሊኖረን እንደሚችል ስለሚነግረን ነው። -Lemony Snicket”

ቀኑን ሙሉ ውጤታማ ውሎ እንዲኖርህ ከፈለግህ ጠዋት ስትነሳ ጀምሮ ያለህን የማለዳ ጊዜ በትክክል ተጠቀምበት። ማለዳህን በትክክል የምትጠቀም ከሆነ ውሎህ ያማረ እንደሆነ መገመት ትችላለህ። ማለዳህን ካበላሸህ ግን ቀንህን ሙሉ ልትጠግነው የማትችለው ስብራት ይሆንብሃል።

ወዳጄ ሆይ ቀንህ ያማረ ይሆን ዘንድ ማለዳህን አሳምር!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
143 viewsTefera Muluneh, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 08:53:09
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
135 viewsTefera Muluneh, 05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 08:32:17 **** ህይወትህ ወዴት እያመራ ነው? ***

ሕይወትህን እንዴት ትገልጸዋለህ? የምትፈልገውን እያሳካህ ነው? ለአንተ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እያከናወንክ ነው? ራስህን እንደ ስኬታማ ትቆጥራለህ? የወደፊት ተስፋህንስ እንዴት እየተመለከትከው ነው?

ብትፈቅድልኝና ወደ ቤትህ መጥቼ አንድ ቀን ብቻ ለ24 ሰአታት ካንተ ጋር ብቆይ፣ ስኬታማ እንደምትሆን ወይም እንደማትሆን በሌላ አገላለጽ ህይወትህ ወደየትኛው አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ እነግርህ ነበር። ይልሃል እውቁ የአመራር ጥበብ አሰልጣኝ ጆን ማክስዌል

ይህ ማለት የቀን ውሎህ ወይም በየቀኑ የምታደርጋቸው ነገሮች የአንተን የወደፊት ስኬታማነት ይወስናሉ። ስለዚህ በየቀኑ የምናደርጋቸውን ነገሮች በማስተዋል እናድርጋቸው።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
170 viewsTefera Muluneh, 05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 08:31:04
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
160 viewsTefera Muluneh, 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 08:30:06 *** አትሽሽ! …ተጋፈጥ! ***

“ከሁሉ ነገር መሸሽ በጣም ቀላል ነው፤ መንቃት ግን ከባድ ነው። ከህይወትህ አትሸሽ፤ ከስራህ አትሸሽ፤ በዙሪያህ ካሉ ነገሮች ሁሉ አትሽሽ። ይልቁንም ንቃና ሁሉንም ልክ እንደፈተና ተጋፈጣቸው። ካነበብኩት

ወዳጄ ሆይ በመሸሽ የምታመልጠው ነገር የለም። ካሉብህ ፈተናዎች ሁሉ እፎይ ማለት የምትችለው ካሸነፍክ ብቻ ነው። እናም ፈተናaችህን በንቃት ተፋገጣቸው።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
183 viewsTefera Muluneh, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 08:28:00
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
171 viewsTefera Muluneh, 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 08:44:46 *** የወደፊት ዕጣህ የቱ ነው? ***

ጆን ማክስዌል “የወደፊት ዕጣህ የሚወሰነው ዛሬ በምትሠራው ነገር ላይ ነው።” ይላል። የእለት ተእለት ድርጊቶችህ ለበጎም ሆነ ለክፉ የወደፊትህን እየፈጠሩ ነው።

እርግጥ ነው፣ ግልጽ የሆነ ራዕይ እና ጠንካራ ስትራቴጂክ እቅድ መኖር አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። ነገር ግን፣ ምንም አይነት ራዕይ ወይም ስልታዊ እቅድ ያለ ውጤታማ የእለት ተእለት ተግባር ስኬታማ ሊሆን አይችልም።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
200 viewsTefera Muluneh, 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 08:43:58
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
182 viewsTefera Muluneh, 05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ