Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-28 08:54:40 *** ቀጣይነት ያለው ተግባር ***

በአንዳንድ ቀናት ለውጥ እያመጣህ እንደሆነ ሊሰማህና ልትበረታታ ትችላለህ። በአንዳንድ ቀናት ደግሞ ምንም እንዳልሰራህ ሊሰማህ እና ምናልባትም በቀላሉ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ሊገጥምህ ይችላል። ግን አስታውስ ቀጣይነት ያለው ተግባር ምንም ካለማድረግ እጅጉን የተሻለ ነው።

የምታከናውነው ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም ተግባርህን እሰከቀጠልክ ድረስ ስኬትህን በየቀኑ እየገነባህ ነው። ወደ ፊት መጓዝህን ያቆምህ ዕለት ግን እስካሁን የገነባኸውን ሁሉ ከቆሻሻ ቅርጫት እንደጣልከው አስታውስ።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
177 viewsTefera Muluneh, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 08:54:40
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
164 viewsTefera Muluneh, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 08:31:13 *** የምትሰራው ስሜት ይሰጥሃልን? ***

የምትሰራው ነገር እያስጨነቀህ ከሆነ በትክክል እየሰራህ ነው። —Childish Gambino

የምትሰራው ሥራ ምንም ስሜት የማይሰጥህ ከሆነ ያንን ሥራ ወይ አልወደድከውም ወይም በትክክል ቢሰራም ባይሰራም በህይወትህ ላይ ብዙም ለውጥ የሚያመጣ አይደለም።

ብትሰራውም ባትሰራውም ለውጥ የማያመጣን ሥራ ባትሰራው ይሻላል። አየህ ወዳጄ ስሜት የማይሰጥህን ሥራ አትስራው ተወው! ምክንያቱም ለአንተም ሆነ ለሌሎች እሴት ካልጨመረልህ የመስራትህ ፋይዳ ምን ሊሆን ይችላል?

ስትሰራው የሚያስጨንቅህ፣ ትንሽ ሲዛነፍ የሚያበሳጭህ፣ ጥሩ እድርገህ ስታጠናቅቅ የሚያስደስትህ ከሆነ እየሰራኸው ያለው ሥራ ትክክለኛ ስራ ነው እና ግፋበት። ስሜት የሚሰጥህን ሥራ ስትሰራ ብቻ ስኬታማ ትሆናለህ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
195 viewsTefera Muluneh, 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 08:28:11
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
185 viewsTefera Muluneh, 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 08:26:37 *** በፍፁም እንዳታቆም***

“መብረር ካልቻልክ ሩጥ፣ መሮጥ ካቃተህ ተራመድ፣ መራመድ ካቃተህ ዳዴ በል፣ ዳዴ ማለት ቢያቅትህ ተንፏቀቅ … ግን ወደፊት መንቀሳቀስህን እንዳታቆም” ማርቲን ሉተር ኪንግ።

ዋናው ነገር አለማቆም ነው። እንቅስቀሴህ የቱንም ያህል ፈጣን ወይም ዘገምተኛ ይሁን እስካላቋረጥህ ድረስ የምትፈልግበት ትደርሳለህ። ካቋረጥህ ግን የትም አትደርስም። እናም ወዳጄ የቱንም ያህል ብትደክም፣ አቅም ቢያንስህ … ማቆም ግን የለብህም።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
217 viewsTefera Muluneh, 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 08:26:37
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
199 viewsTefera Muluneh, 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 09:14:47 *** አዲስ መንገድ ጥረግ! ***

"የምትሄድበትን መንገድ ካልወደድከው ሌላ አዲስ መንገድ መጥረግ ጀምር።" - ዶሊ ፓርተን

እየሄድክበት ያለው መንገድ አሰልቺ እና ምናልባትም የምትፈልገው ላይ ለመድረስ የማያስችልህ ሊሆን ይችላል።

የምትራመድበት ጎዳና የአንተ ትክክለኛ የህይወት መንገድ ላይሆን ይችላል። እናም በዚህ ጎዳና ስትጓዝ ህይወት አሰልቺ ልትሆንብህ ትችላለች።

ወዳጄ ሆይ ያለው መንገድ አንድ ብቻ አይደለም። ምናልባትም እየሄድክበት ያለው መንገድ ላንተ የተፈቀደ አይደለም። እናም የአንተን የህይወት መንገድ መጥረግ የአንተ ኃላፊነት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የራስህን መንገድ ራስህ መጥረግ ይኖርብሃል።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
215 viewsTefera Muluneh, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 09:10:22
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
193 viewsTefera Muluneh, 06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 08:55:25 *** ስጦታዎችህን ተጠቀምባቸው! ***

ራስህን በመስታወት ተመልከተው።

አካላዊ ማንነትህን ተመልከተው። በዓለም ላይ እንደ አንተ ያለ ማንም እንደሌለ ታውቃለህ? በዓለም ላይ ከ8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች አሉ። እናም እንደ አንተ ያለ ማንም የለም። አየህ አንተ ከሁሉም የተለየህ ሆነህ ተፈጥረሃል። እናም ህይንን ማንነትህን ከሌሎች የተለየ ነገር በማድረግ በተለየ መንገድ ተጠቀምበት።

አፈጣጠርህን ተመልከተው። አንት በጣም አስደናቂ ፍጡር ነህ! ሌሎች ሰዎች የሌላቸው ችሎታዎች አሉህ! በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገውንና መሆን የምትፈልገውን ለማድረግ የሚያስችል አቅም አለህ! እናም ይህንን አቅምህን በማውጣት አንተንና በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን ህይወት የሚለውጥ ቁምነገር በመስራት ተጠቀምበት።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
206 viewsTefera Muluneh, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 08:54:04
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision224
189 viewsTefera Muluneh, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ