Get Mystery Box with random crypto!

Vision-power Page

የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page V
የቴሌግራም ቻናል አርማ vision224 — Vision-power Page
የሰርጥ አድራሻ: @vision224
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 495

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-01 09:28:03 *** በሳቅ ህይወትህን ቀይር! ***

ስትስቅ ትለወጣለህ፤ ስትለወጥ በዙሪያህ ያለው ዓለም ሁሉ አስማታዊ በሆነ መንገድ ይለዋወጣል። -Charlie Chaplin

ሁላችንም ልክ እንደ አስማተኞች ነን፤ አንድን ሰው በፈገግታ ከተመለከተን ያለብንን ድካም፣ ህመም፣ … ረስተን ፈገግ በማለት ምላሽ እንሰጣለን።

ሳቅ ለሰዎች ራሳቸውን እና ዓለምን ሰላማዊ እና በአዎንታዊ መንገድ ለመለወጥ የሚያስፈልጉ ሁሉም ንጥረ ነገሮች ያሉት አዎንታዊ እና ኃይለኛ ስሜት ነው። ሳቅ መላውን ሰውነት ያዝናናል፤ በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል፤ …. እናም ሁልጊዜ ለመሳቅ ምክንያቶችን ፈልጉ።

ሳቅ በህይወታችን ላይ ዓመታትን ላይጨምር ይችላል፤ ነገር ግን በእርግጠኝነት ለዕድሜያችን ህይወትን ይጨምራል።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
208 viewsTefera Muluneh, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 09:28:03
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
188 viewsTefera Muluneh, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 10:23:53 *** እድለኛ ነህ! ***

ሰዎች ብዙ ጊዜ ሲሳካላቸው እገሌ እኮ እድለኛ ነው ይባላል። በጣም የሚገርመው ያሰው የተሳካለት በብዙ ድካምና ውጣውረድ መሆኑን ማንም አያስተውልም።

በእርግጥ ሰዎች እድለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን እድልም ቢሆን መዘጋጀትን ይጠይቃል። እናቴ “በሬ በጭብጦ ተለወጠ/ተሸጠ ብትባል ያላቦካ ከየት ያመጣዋል?” የሚል አባባል አላት።

አየህ ወዳጄ ስኬት የሚገኘው በዕድል እንኳ ቢሆን ያንን እድል ለመጠቀም የተዘጋጀህ መሆን ይኖርብሃል። እድል የሚመጣው ለሚጥር እና በሚመጣለት እድል ሁሉ ለመጠቀም ለተዘጋጀ ብቻ ነው። እድል እንዲሁ ሳይዘጋጅ ለሚጠብቃት በፍፁም አትመጣም። ብትመጣም አይናችንን እያየ ታመልጠናለች።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
217 viewsTefera Muluneh, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 10:18:02
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
228 viewsTefera Muluneh, 07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 08:08:17 *** ሁሉም ነገር እንዲኖርህ ትፈልጋለህ? ***

ሁሉም ነገር ሊኖርህ ይችላል፤ ይሁንና ሁሉም ነገር በአንድጊዜ ማግኘት አትችልም። -Oprah Winfrey

እያንዳንዱን የህይወትህን ክፍል ሙሉ ለሙሉ ለማስተካከል ሁሉንም እንደገና ለመጀመር አስበህ ታውቃለህ? ይህ ብዙዎቻችን ዘመን መለወጫ በመጣ ቁጥር የምናደርገው ነገር ነው።

አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ለማዳበር እና የተሻለ ሰው ለመሆን በርካታ ውሳኔዎችን እንወስናለን። ለምሳሌ አመጋገባችንን ማሻሻል፣ ጤናችንን መጠበቅ፣ ስፖርት መስራት፣ ገቢን ለማሳደግ የሚያስችሉ ዕቅዶችን መንደፍ፣ ቁጠባን መጀመር፣ ፍቅር መጀመር ወይም የነበረንን ይበልጥ ማጠንከር ወዘተ. ዕቅዶችን እናወጣለን።

ይሄ ሁሉ መልካም ነገር ነው። ይሁን እንጂ ይህንን ለውጥ በህይወታችን ዕውን ለማድረግ ጽናትን፣ ትዕግስት እና ከፍተኛ ጥንካሬን ይዞ ለረጅም ጊዜ መዝለቅን ይጠይቃል። የብዙዎቻችን ፈተናም የሚመጣው ለዚህ ነው። ፍላጎቶቻችን ሲበዙ ከየት እንደምንጀምር ግራ ይገባናል፤ ሁሉንም ይዞ መጓዝም ይከብደናል።

ወዳጄ ሆይ አንተ ግን ብልጥ መሆን አለብህ። የምትፈልገው ነገር ብዙ ቢሆንም!... እንደምታገኘው እርግጠኛ ብትሆንም!... ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማሳካት ሊከብድህ ስለሚችል ይበልጥ የምትፈልገው ላይ ትኩረትህን በማድረግ ደረጃ በደረጃ አንዱን እያሳካህ ወደሌላኛው ብትሄድ ነገሩ ሁሉ ቀላል ይሆንልሃል።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
58 viewsTefera Muluneh, 05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 08:03:56
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
56 viewsTefera Muluneh, 05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 08:26:32 *** ምርጡ ጊዜ! ***

የስኬትን መንገድ ለመጀመር ምርጡ ጊዜ መቼ ነው? ብዙዎቻችን ዛሬ ነገ እያልን የስኬታችንን ጊዜ እናረዝማለን። ሁልጊዜ እናቅዳለን፤ ግን ወደ ተግባር አንቀይረውም። ዕቅዳችንን ወደ ተግባር ለመቀየር እና የስኬትን መንገድ ለመጀመር ምርጥ የሚባል ጊዜ የለም። ካለም እሱ ዛሬ ነው። እናም የስኬት ጊዜህን ዛሬውኑ ጀምረው!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
133 viewsTefera Muluneh, 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 08:23:43
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
134 viewsTefera Muluneh, 05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 08:21:39 *** ሁለት ዜናዎች አሉኝ! ***

መጥፎው ዜና ጊዜ እየበረረ ነው፤ ጥሩ ዜና ደግሞ አብራሪው አንተ/ቺ ነህ/ሽ! -Michael Altshuler

ጊዜ ይከንፋል፤ ማንም ሊያቆመው አይችልም፤ ነገር ግን እኛ ማድረግ የምንችለው የህይወታችንን ትክክለኛ ሚዛን ለመጠበቅ ጊዜያችንን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም ነው።

ብዙዎቻችን የምንሰራው ትልቁ ስህተት በህይወታችን ያለን ጊዜ የተወሰነ መሆኑን አለማወቃችን ነው። ልብ በል! ጊዜ ሊፈጠር አይችልም፤ ነገር ግን ጥቅም ላይ ልናውለው እንችላለን።

የአንድ ሰው የጊዜ አጠቃቀም የዚያን ሰው ማንነት ይናገራል። ሁላችንም በተመሳሳይ በቀን ውስጥ እኩል 24 ሰዓታት አሉን። ልዩነት የሚያመጣው ይህንን ጊዜ በአግባቡ እና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም ወይም ባለመጠቀም ነው።

እናም ወዳጄ ሆይ ጊዜህን ተጠቀም!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!
25 viewsTefera Muluneh, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 08:15:24
መልካም አዲስ ቀን!
Tefera M.
— telegram: @Vision22
31 viewsTefera Muluneh, 05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ