Get Mystery Box with random crypto!

*** እድለኛ ነህ! *** ሰዎች ብዙ ጊዜ ሲሳካላቸው እገሌ እኮ እድለኛ ነው ይባላል። በጣም የሚ | Vision-power Page

*** እድለኛ ነህ! ***

ሰዎች ብዙ ጊዜ ሲሳካላቸው እገሌ እኮ እድለኛ ነው ይባላል። በጣም የሚገርመው ያሰው የተሳካለት በብዙ ድካምና ውጣውረድ መሆኑን ማንም አያስተውልም።

በእርግጥ ሰዎች እድለኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን እድልም ቢሆን መዘጋጀትን ይጠይቃል። እናቴ “በሬ በጭብጦ ተለወጠ/ተሸጠ ብትባል ያላቦካ ከየት ያመጣዋል?” የሚል አባባል አላት።

አየህ ወዳጄ ስኬት የሚገኘው በዕድል እንኳ ቢሆን ያንን እድል ለመጠቀም የተዘጋጀህ መሆን ይኖርብሃል። እድል የሚመጣው ለሚጥር እና በሚመጣለት እድል ሁሉ ለመጠቀም ለተዘጋጀ ብቻ ነው። እድል እንዲሁ ሳይዘጋጅ ለሚጠብቃት በፍፁም አትመጣም። ብትመጣም አይናችንን እያየ ታመልጠናለች።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!