Get Mystery Box with random crypto!

*** ስትጋልብ ፍረጥ! *** በቀለ መኮነን(መልህቅ መጽሐፍ ርዕሱ የተቀየረ) የሕህወት ጎዳና ገ | Vision-power Page

*** ስትጋልብ ፍረጥ! ***

በቀለ መኮነን(መልህቅ መጽሐፍ ርዕሱ የተቀየረ)
የሕህወት ጎዳና ገፁ ሲለወጥ፣
በጭነት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ፣
የእንቅፋት አፅሙ ቋጥኝ ሲገለጥ፣

ሸክም ዘንቦብህ ትቢያው ሲላቆጥ፣
ሲሆን ድጥ በድጥ፣
ሾህ ጭቃ ቅይጥ፣
ልብህ አይደንግጥ።
በምኞት ቅዠት በስጋት ርዶ፣
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ፣

ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ፣
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሽምጥጥ።
አያረጅ የለም አይለዋወጥ፣
ነገን ተማምነህ በመጓዝ ቁረጥ፤
እሩቅ አልመህ ቅርብ አትርመጥመጥ፤
ሰግተህ ከምትቆም ስትጋልብ ፍረጥ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!