Get Mystery Box with random crypto!

*** ልደትህ መቼ ነው? *** የልደትህ ቀን ሲደርስ የሚሰማህ ምንድነው? ብዙዎቻችን የልደታችንን | Vision-power Page

*** ልደትህ መቼ ነው? ***

የልደትህ ቀን ሲደርስ የሚሰማህ ምንድነው? ብዙዎቻችን የልደታችንን ቀን በጉጉት ነው የምንጠብቀው። እና በደስታና በፌሽታ እናሳልፈዋለን።

አንድ ጓደኛዬ “ሰው ለምንድነው ልደቱን በደስታና በፌሽታ የሚያሳልፈው? እንዲያውም ልደቱን ባከበረ ቁጥር በዚህ ምድር ከሚኖረው ቆይታ በአንድ አመት እየቀነሰ እና ወደ ህይወት ፍፃሜው እየተቃረበ በመሆኑ ሊያዝን ነው የሚገባው” ይላል።

እውነት ነው! በየቀኑ ከእድሜያችን ላይ በ24 ሰዓት እንቀንሳለን፤ በየወሩ በ30 ቀናት እንቀንሳለን፤ በየዓመቱ ደግሞ ከእድሜያችን ላይ አንድ ዓመት እንቀንሳለን። እንዲህ እንዲህ እያልን ወደ ፍፃሜያችን እንደርሳለን።

ዋናው ጉዳይ የህይወት ጊዜያችን ከመጠናቀቁ በፊት ምን ቁምነገር እየሰራን ነው? የሚለው ነው። በኋላ ጊዜ አልቆ ምንም ማድረግ በማንችልበት ሰዓት ይህንን ባደርግ ኖሮ የሚለው ሃሳብ ጥቅም የለውምና ወዳጆች ሆይ በጊዜ እንንቃ!

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!