Get Mystery Box with random crypto!

*** ስህተት የማደግ ዕድል ነው! *** ብዙዎቻችን መሳሳትን እንፈራለን ወይም እንጠላለን። ይሁን | Vision-power Page

*** ስህተት የማደግ ዕድል ነው! ***

ብዙዎቻችን መሳሳትን እንፈራለን ወይም እንጠላለን። ይሁን እንጂ እኛ ሰዎች በመሆናችን መሳሳታችን የማይቀር ነገር ነው።

በሌላ በኩል ካየነው ደግሞ መሳሳት ሌላ ተጨማሪ መንገድ ለመማር እድል የሚሰጠን ነገር ነው። ካልሞከርን እና ካልተሳሳትን ትክክለኛውን መንገድ ልናውቅ አንችልም። እዚህ ላይ ዋናው ጉዳይ መሳሳት አይደለም። ስለተሳሳትን ሌላ መሳሳትን በመፍራት ወይም በመጨማቀቅ ከመሞከር እንቆማለን ወይስ ሙከራችንን እንቀጥላለን? የሚለው ነው።

ወዳጆች ሆይ ስኬት የሚመጣው በመሞከር፣ በመሳሳት እና እንደገና በመነሳት ነው።

ስኬታማ እና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!