Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Silver
Platinum
Golden
Choleraupdate
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-04-15 12:55:37
#cloudbridge. #traininginstitute

ክላውድ በሪጂ ማሰልጠኛ ተቋም ፤ለስልጠና ፍላጊዎች በሙሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ እውቀት አቅም ግንባታ ነፃ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን በጉጉት  ይጠብቃል::

ስልጠና ሚሰጥባችው ዘረፎች መካከል፡
1, Digital marketing
2,Web development
3, Interior design
4, Graphic design

የስልጠና ቦታ
ሲቲ ሞል 6ኛ ፎቅ, መገናኛ ድልድይ,wow burger ያለበት፣Megenagna siti Mall 6th, Addis Ababa, Ethiopia

ለተጨማሪ መረጃ
094-228-0000
092-083-8483
ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸው ፈጥነው በአካል መተው ይመዝገቡ።
         ለአንድ ቀን ሚቆይ ነፃ ስልጠና!
Register online
https://cloudbridgeacademy.com/registration
22.1K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 16:36:25
ከበርካታ ባንኮች ከፍተኛ ብድር የሚወስዱ ተበዳሪዎችን የሚቆጣጠር ሕግ ሊወጣ ነው ተባለ።

ከበርካታ ባንኮች ብድር የሚወስዱ ተበዳሪዎችን መቆጣጠርና የብድር ክምችትን ማስተካከል የሚችል ሕግ፣ እየተሻሻለ ባለው የባንክ ሥራ አዋጅ ውስጥ ለማካተት እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል።

ብሔራዊ ባንክ ሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የፋይናንስ ስታቢሊቲ ሪፖርት (Financial Stability Report) የባንክ ብድሮች በጥቂት ተበዳሪዎች እጅ ተከማችተው እንደሚገኙ ይጠቅሳል።

በአገሪቱ ያሉት ሁሉም ባንኮች እስካለፈው ዓመት ሰኔ መጨረሻ ድረስ በሥራ ላይ ካዋሉት አጠቃላይ 1.9 ትሪሊዮን ብር ብድር ውስጥ 23.5 በመቶውን ያበደሩት ለአሥር ተበዳሪዎች እንደሆነ በሪፖርቱ ተካቷል።

ከፍተኞቹ አሥር ተበዳሪዎች ከአጠቃላይ የባንክ ብድር መጠን ውስጥ በ2014 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከነበረው 18.7 በመቶ ነው በ2015 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ወደ 23.5 ያደገ ነው ተብሏል።

እየተስተካከለ ያለው የባንክ ሥራ አዋጅ በብሔራዊ ባንክ ተጠናቆ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት አለመላኩን፣ ነገር ግን እንደ የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓይነት ተቋማት እያዩት አስተያየታቸውን እየሰጡበት መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ አረጋግጫለሁ ብሏል።

@TikvahethMagazine
32.1K viewsedited  13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 16:36:15
ከ7 እስከ 18 ለሆኑ ልጆች የኦንላይን  ኮዲንግ  ስልጠና

ስልጠና April 20 , 2024 ቅዳሜ ይጀምራል።

ከ7 እስከ 13 ለሆኑ ህጻናት የ6 ሳምንታት የscratch ስልጠና( ጌም እና አኒሜሽን እየሰሩ ነው ሚማሩት)።

ከ14 እስከ 18 ለሆኑት የ website ስልጠና ለ 2 ወር።

የምስክር ወረቀት ያገኛሉ

ክፍያ ለ6 ሳምንት ፕሮግራም 2500 ብር ነው።
ክፍያ ለ 2 ወር ፕሮግራም 3500 ብር ነው።

በቴሌግራም መረጃ ለማግኘት ያግኙን
@koderlabtrainingcenter ወይም በ 0940121072 ይደውሉ።

ይህንን ሊንክ በመጠቀም ሬጅስተር ያርጉ።
https://forms.gle/J3CeN5XE4vQW3MF49
28.4K views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 22:42:51
#Update : "በአደጋው ሁለት የአንድ ቤተሰብ ህጻናት ህይወታቸው አልፏል"- የዲላ ከተማ አስተዳደር

በዛሬው ዕለት (በ05/ 08/ 2016 ዓ/ም) 10 ሠዓት ገዳማ ንፋስ ቀላቅሎ በዘነበው ከባድ ዝናብ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዲላ ከተማ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በተፈጠረው ተፈጥሯዊ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ሁለት የአንድ ቤተሰብ ህጻናት መሆናቸውን አስተዳደሩ በመግለጫው ጠቅሷል።

በተጨማሪም በዚህ አደጋ በርካታ ዛፎች እና በርካታ የኤሌክትሪክ ፖሎች መውደቃቸውን ገልጾ፥ በዚህም ምክንያት ኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን አስታውቋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተካክሎ ወደ ቦታው እስኪመለስ ድረስ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግና ከተለያዩ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።

አስተዳደሩ በመግለጫው በአደጋው ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን የተመኘ ሲሆን በደረሰዉ አደጋ ንብረታቸውን ላጡ ወገኖች የዲላ ከተማ ነዋሪዎች የተለመደውን ቀና ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል።

@TikvahethMagazine
14.1K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 20:58:06
#Update

በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተደረገ በረራ 1 ሺህ 71 ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ዛሬ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ዘጠኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

መረጃው የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ነው።

@TikvahethMagazine
20.0K viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 19:29:04
#Update

በዛሬው ዕለት በጌዲዮ ዞን እና አካባቢው በጣለው ከባድ ዝናብ በሰው እና ንብረት ላይ ውድመት አድርሷል። በዲላ ዩኒቨርስቲ  እስካሁን በሰው ላይ ይህ ነው የተባለ ጉዳት አልደረሰም።

ሆኖም የግቢው ያሉ ዕፀዋት በፎቶ በምትመለከቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል። አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል።

@tikvahmagbot / TikvahFamily

@TikvahethMagazine
22.8K viewsedited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 18:17:23
በዲላ ከተማ አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በዲላ ከተማ አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ እስካሁን ባለው መረጃ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን በተወሰኑ ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ጉዳቱ የደረሰው ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ አካባቢ መሆኑን ያመለከተው የዲላ ከተማ ፖሊስ የተጎዱ ግለሰቦችን ወደ ሆስፒታል የመወሰድ እንዲሁም መንገድ ላይ የወደቁ ዛፎችንና የመብራት ፖሎችን ከመንገድ የማንሳት ተግባር እየተከናወነ ይገኛል ብሏል።

መረጃው የዲላ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ነው።

@TikvahethMagazine
23.1K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 18:01:57
የመንገድ ዳር የዶሮ ጥብስ በሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ የመንገድ ዳር የዶሮ ጥብስ ንግድ ማህበራት በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራ መጀመራቸው ተገልጿል። በዛሬው እለት በይፋ ስራቸውን የጀመሩት ካኖ እና ባማ የተሰኙት የመንገድ ዳር የዶሮ ጥብስ ንግድ ማህበራት ናቸው።

ማኅበራቱ ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጥላ ፕሮጀክት የገንዘብ እንዲሁም ከስራና ክህሎት ሚንስቴር፣ ከሲዳማ ክልል፣ ከሐዋሳ ከተማ ድጋፍ ማግኘታቸው ተገልጿል።

@TikvahethMagazine
22.1K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 17:57:10
#TikvahFamily: "ሰላም የቲክቫህ ቤተሰቦች አንድ ጉዳይ ተባበሩኝ ዛሬ በሐዋሳ ከተማ 5:00 ሰዓት አከባቢ ከአዲሱ ስታዲየም ወደ ወደ አሮጌ መናህሪያ ተሳፍሬ ስሄድ የትምህርት ዶክመንት ጥያለሁ እባካችሁ ያገኛችሁ አሳውቁኝ"

Via @tikvahmagbot

ስም፦ ጽዮን አዳነ / 0972782977

@TikvahethMagazine
19.3K viewsedited  14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 17:20:26
በኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ላይ ብልሹ አሰራር አለ ተባለ።

በአዲስ አበባ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ በሚሰጡ #ኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ላይ ብልሹ አሰራር እንዳለ የከተማው ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው የ9 ወራት አፈፃፀሙን በገመገመበት መድረክ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ የበክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የንግድ ፅ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ይህንን ጉዳይ አንስተዋል።

ኃላፊው፥ አዲስ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት ወይም ነባሩን ንግድ ፈቃድ ለማደስ የሚፈልግ ተገልጋይ አገልግሎቱን ወደየትኛውም ተቋም በአካል መምጣት ሳያስፈልገው በኦንላይን አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል አንስተዋል።

ሆኖም፥ ሆን ተብሎ አገልግሎቱን በማዘግየትና ወደ ቢሮ በአካል እንዲመጣ በማድረግ የመደራደር ዝንባሌዎች በክትትል መስተዋላቸውን ጠቅሰዋል።

ለዚህም ደግሞ አንዳንድ ባለሞያዎች በምክንያትነት የኢንተርኔት መቆራረጥ፣ የመብራት አለመኖርና መሰል ክፍተቶችን እንደሚያነሱ በመግለጽ ለአገልግሎቱ መዘግየት የሚቀርቡ ምክንያቶች እውነተኛነት ማረጋገጥ ከፅ/ቤት ኃላፊቹ የሚጠበቅ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከንግድ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚስተዋል ብልሹ አሰራርችን የዘርፉ አመራሮች ጠንካራ የክትትል እንዲያደርጉና ችግሩ በሚስተዋልባቸው ባለሙያዎች ላይም ጠንካራ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ኃላፊው ማሳሰባቸውን ከቢሮው ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ተመልክተናል።

@TikvahethMagazine
20.0K viewsedited  14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ