Get Mystery Box with random crypto!

#Update : 'በአደጋው ሁለት የአንድ ቤተሰብ ህጻናት ህይወታቸው አልፏል'- የዲላ ከተማ አስተዳ | TIKVAH-MAGAZINE

#Update : "በአደጋው ሁለት የአንድ ቤተሰብ ህጻናት ህይወታቸው አልፏል"- የዲላ ከተማ አስተዳደር

በዛሬው ዕለት (በ05/ 08/ 2016 ዓ/ም) 10 ሠዓት ገዳማ ንፋስ ቀላቅሎ በዘነበው ከባድ ዝናብ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዲላ ከተማ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በተፈጠረው ተፈጥሯዊ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ሁለት የአንድ ቤተሰብ ህጻናት መሆናቸውን አስተዳደሩ በመግለጫው ጠቅሷል።

በተጨማሪም በዚህ አደጋ በርካታ ዛፎች እና በርካታ የኤሌክትሪክ ፖሎች መውደቃቸውን ገልጾ፥ በዚህም ምክንያት ኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን አስታውቋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተካክሎ ወደ ቦታው እስኪመለስ ድረስ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግና ከተለያዩ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።

አስተዳደሩ በመግለጫው በአደጋው ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን የተመኘ ሲሆን በደረሰዉ አደጋ ንብረታቸውን ላጡ ወገኖች የዲላ ከተማ ነዋሪዎች የተለመደውን ቀና ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል።

@TikvahethMagazine