Get Mystery Box with random crypto!

በኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ላይ ብልሹ አሰራር አለ ተባለ። በአዲስ አበባ በክፍ | TIKVAH-MAGAZINE

በኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ላይ ብልሹ አሰራር አለ ተባለ።

በአዲስ አበባ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ በሚሰጡ #ኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ላይ ብልሹ አሰራር እንዳለ የከተማው ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው የ9 ወራት አፈፃፀሙን በገመገመበት መድረክ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ የበክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የንግድ ፅ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ይህንን ጉዳይ አንስተዋል።

ኃላፊው፥ አዲስ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት ወይም ነባሩን ንግድ ፈቃድ ለማደስ የሚፈልግ ተገልጋይ አገልግሎቱን ወደየትኛውም ተቋም በአካል መምጣት ሳያስፈልገው በኦንላይን አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል አንስተዋል።

ሆኖም፥ ሆን ተብሎ አገልግሎቱን በማዘግየትና ወደ ቢሮ በአካል እንዲመጣ በማድረግ የመደራደር ዝንባሌዎች በክትትል መስተዋላቸውን ጠቅሰዋል።

ለዚህም ደግሞ አንዳንድ ባለሞያዎች በምክንያትነት የኢንተርኔት መቆራረጥ፣ የመብራት አለመኖርና መሰል ክፍተቶችን እንደሚያነሱ በመግለጽ ለአገልግሎቱ መዘግየት የሚቀርቡ ምክንያቶች እውነተኛነት ማረጋገጥ ከፅ/ቤት ኃላፊቹ የሚጠበቅ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከንግድ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚስተዋል ብልሹ አሰራርችን የዘርፉ አመራሮች ጠንካራ የክትትል እንዲያደርጉና ችግሩ በሚስተዋልባቸው ባለሙያዎች ላይም ጠንካራ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ኃላፊው ማሳሰባቸውን ከቢሮው ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ተመልክተናል።

@TikvahethMagazine