Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 89.04K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2022-05-21 21:21:28 አምስት ስድስት ሰባት
ደራሲ-ስብሀት ገብረ እግዚአብሔር
ተራኪ - አበበ ባልቻ

@Human_Intelligence
2.1K viewsedited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 21:15:51 መስተአድርት
ደራሲ -ጃርሶ ሞት ባይኖር
ተራኪ- አበበ ባልቻ

@Human_Intelligence
2.3K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 07:15:41 ፍላጎትና ችሎታ ሲራራቁ!

አንድን ነገር በተዋጣለት መልኩ ለማከናወን የሚያስፈልጉን ዋና ዋና ነገሮች ችሎታና ፍላጎት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱ ሲኖርና ሌላኛው ሲጎድል ስኬት የሕልም እንጀራ ነው፡፡

1. ችሎታና አቅም ኖሮ ፍላጎትና መነሳሳት ሲጠፋ

በአንድ ነገር ላይ ምንም ያህል ችሎታና አቅም ቢኖራችሁም፣ ያንን ነገር ለማድረግ ፍላጎትና መነሳሳት ከሌላችሁ ምንም ነገር ማከናወንም ሆነ የትም ደረጃ ልትደርሱ አትችሉም፡፡

ምናልባት ችሎታውና አቅሙ እያላችሁ ለመንቀሳቀስ ፍላጎትና መነሳሳት ያጣችሁት . . .

• ከጊዜያዊ የስሜት ቀውስ የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ፣ ለስሜት ቀውስ የዳረጋችሁን ሁኔታ ፈልጋችሁ በማግኘትና በመቅረፍ ራሳችሁን ለማነሳሳት ሞክሩ፡፡

• ያላችሁ ችሎታ መስራት ከምትፈልጉት ነገር ጋር የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ፣ ለጊዜው ራሳችሁን ገፍታችሁም ቢሆን እየተንቀሳቀሳችሁ ወደፊት በፍላጎታችሁ መስክ የምትሰማሩበትን መንገድ በሂደት ማስተካከል የግድ ነው፡፡

2. ፍላጎትና መነሳሳት ኖሮ ችሎታና አቅም ሲጠፋ
ከላይ ከተጠቀሰው በተቃራኒ፣ አንድ ነገር ለማከናወን ያላችሁ ፍላጎትና መነሳሳት ምንም ያህል ብርቱ ቢሆን ያንን ነገር ለማከናወን ችሎታውና አቅሙ ከሌላችሁ ብዙም አያራምዳችሁም፡፡
ምናልባት ፍላጎትና መነሳሳት እያላችሁ ለመስራት ችሎታንና አቅሙን ያጣችሁት . . .

• ከእውቀት ወይም ከክህሎት ጉድለት ከሆነ ያንን ለማስተካከል ማንበብ፣ መማር፣ መሰልጠንና ልምድ ማግኘት አስፋለጊ ነው፡፡

• ከገንዘብ ወይም ከቁሳቁስ እጥረት ከሆነ ያንን ለማስተካከል የገንዘብ አቅማችሁን ለመገንባት መጀመሪያ መስራት፣ ሊደግፋችሁ የሚችልን ሰው መጠየቅና የመሳሰሉትን ነገሮች ማድረግ የግድ ነው፡፡

በዚህ ሳምንት በዚህ ሃሳብ ላይ በሚገባ እንድታስቡበትና እንቅስቃሴ እንድትጀምሩ ላነሳሳችሁ፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
3.8K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 18:41:00 ራስህን ጠብቅ! ፓስወርድህን አጥብቅ!
(World Password Day!)
(እ.ብ.ይ.)

ዲጂታል ጦርነቱ ተጧጡፏል፡፡ የዓለም ሐያልነት ፉክክር በቴክኖሎጂ ስልጣኔ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ሐገራት ቴክኖሎጂ ያልነካውና ያልደረሰበት የለም፡፡ ንብረቶቻችን፣ ጥሪቶቻችንና ገንዘቦቻችን እንደጥንቱ ጊዜ ዘመድ ወይም ወዳጅ ጋር በታማኝነት በአደራ የምናስቀምጥበት፣ ከመሬት በታች ቆፍረን የምንደብቅበት፣ በቤታችን ሳጥን ውስጥ ቆልፈን የምንሸሽግበት ጊዜ እያበቃ ነው፡፡ ዛሬ ቁልፉ ዘምኗል፣ ማስቀመጫውም ረቅቋል፡፡ ግዢዎቻችንንም ሆነ ሽያጮቻችንን የምናቀላጥፈው፣ የዕለት ተዕለት የሕይወታችንን መስተጋብር የምናስኬድበት፣ ገንዘባችንን ወደፈለግነው ቦታ የምናዘዋውረው መረጃ ቴክኖሎጂው በቀደደልን አዲስ መንገድ ሆኗል፡፡ ሁሉ ነገር በእጃችን መዳፍ ቁጥጥር ውስጥ እየሆነ ነው፡፡ የምንፈልገውን ማዘዝ፣ የምንሻውን ማንበብ፣ ማዳመጥና ማየት የምንፈልገውን ሁሉ የምናደርገው በገዛ የእጃችን ስልክ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ በዘመናዊው ዓለም አሰራር ስራ ለመቀጠር፣ ትምህርት ለመማር፣ የፍርድ ቤት ክርክሮችን ቀጠሮ ለማስያዝ፣ ለአየር በረራ፣ የሆቴል አልጋ ለመከራየት፣ ወዘተ ስራዎቻችንን ለማቀላጠፍ እንዲረዳን ደግሞ የመጠቀሚያ ስምና የይለፍ ቃል (Username amnd Password) የግድ ያስፈልገናል፡፡ ግላዊ ሃሳቦቻችንን የምናንፀባርቅባቸው፣ ከሌላው ጋር የምንከራከርባቸው፣ የምንማማርባቸው፣ የምንደዋወልባቸው፣ የምንዝናናባቸው፣ ያሻነውን የምናደርጋባቸው እነፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩቱብ፣ ሚሴንጀር፣ ወዘተ ሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎች ያለ ጠንካራ የይለፍ ቃል አደጋ ላይ ይጥሉናል፤ ደህንነታቸውም ካልተጠበቀ ከጥቅማቸው በላይ ጉዳታቸው ያመዝናል፡፡

በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮምፕዩተርን የይለፍ ቃል እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ ያስተዋወቀው ታዋቂው አሜሪካዊ የኮምፕዩተር ሳይንቲስት ፈርናንዶ ኮርባቶ (Fernando Corbato) ሲሆን ዓላማውም በጊዜው የነበሩ ተመራማሪዎች ግላዊ የምርምር ፋይሎችን እንዲጠቀሙ ለመፍቀድ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. “Perfect Passwords” በሚል ርዕስ መፅሐፍ በማሳተም ለመጀመሪያ ጊዜ ፓስወርድ ቀን ሊሰየምበት እንደሚገባ ሃሳብ ያነሳው ሰው ደግሞ ማርክ ብሩኔት (Mark Brunett) የተባለ ፀሐፊ ነበር፡፡ ከስምንት ዓመታት በኋላ ሃሳቡ ተቀባይነት አግኝቶ የሳይበር ደህንነት ባለሞያዎች እ.ኤ.አ. በ2013 ዓ.ም አድርገውት በነበረው ዓመታዊ ስብሰባ የፈረንጆቹ የግንቦት (May) ወር በገባ በመጀመሪያው ሐሙስ የዓለም የፓስወርድ ቀን መታሰቢያ እንዲሆን ተስማምተው ቀኑን አፅድቀውታል፡፡ ይሄ እንዲሆን ዋናውን ሚና የተጫወተው ታዋቂው የኮምፕዩተር ዕቃዎች አምራች የሆነው ታላቁ የአይቲ ኩባንያ ኢንቴል (Intel) ድርሻ ከፍተኛ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የዛሬው ሐሙስ ግንቦት 5 ቀን 2022 ዓ.ም የዓለም የፓስወርድ ቀን ለአስራአንደኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የዓለም የፓስወርድ ቀን ለምን አስፈለገ ለሚለው ጥያቄ ባለሞያዎቹ ሲመልሱ የሕይወት መስተጋብራችን ድሮ ከነበረው እየተለወጠ በመምጣቱና ሁለመናችን ወደዲጂታል ዓለሙ እየተቀየረ በመሆኑ ምክንያት የቴክኖሎጂው አጠቃቀማችን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆንና ጥብቅ የይለፍ ቃል እንደሚያስፈልገን ለማስገንዘብ ነው፡፡ ጥንቃቄው አንደኛ የመጠቀሚያ ስማችንንና የማለፊያ ቃላችን አለመዘንጋት ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ጉዳይ ግን የይለፍ ቃላችን (Password) በቀላሉ አየር በአየር በሚዘርፉ የመረጃ መንታፊዎች (ዘመናዊ ሌቦች) በቀላሉ እንዳይዘረፍ ቁልፋችንን ማዘመን እንደሚጠበቅብን ለማሳሰብ ነው፡፡

ዘመኑ የወለዳቸው፣ ለዓለም ስጋት እየሆኑ የመጡት የመረጃ መንታፊዎች አይደለም ግለሰብን ቀርቶ ትላልቅ ግዙፍ ተቋማትን እየተገዳደሩ ይገኛሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በያንዳንዷ ሰከንድ 921 የይለፍ ቃሎች (Passwords) ጥቃት ይከፈትባቸዋል፡፡ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ደግሞ ይሄ ቁጥር እጥፍ ሆኖ አድጓል፡፡

ዋናው ቁምነገር እንዴት ነው የይለፍ ቃላችንን በቀላሉ የማይደፈርና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የምናደርገው የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ የዘርፉ ባለሞያዎቹ እንደሚመክሩት ተጨማሪ መግቢያዎችን (Logins) መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ አንደኛው Two-factor authentication የሚባል ሲሆን ከመጠቀሚያ ስምና ከይለፍ ቃል በተጨማሪ ማንም ሌላ ሰው ሊያውቀውና ሊደርስበት የማይችለውን የሚስጥር ጥያቄዎችን በመሙላትና እሱን በመመለስ ወደመረጃ መረቡ የምንገባበት ዘዴ ነው (ለምሳሌ የመጀመሪያ ፍቅረኛ ስም፣ የእናት ስም፣ ወይም የትውልድ ቀንና ቦታ፣ ወዘተ)፡፡ ሁለተኛው የፊት አሻራን (Face Recognition) መጠቀም ነው (ምናልባት ይሄኛው ዘዴ በቅርቡ ሶስትና አራት አመታት ውስጥ በተመረቱ ዘመናዊ ስልኮች ውስጥ የሚገኝ መላ ነው)፡፡ ሶስተኛው ዘዴ ደግሞ Single-Use code የሚባል ሲሆን ወደመረጃ መረቡ ለመግባት የፈለገው ሰው ማን እንደሆነ ለማረጋገጥ መግቢያችንን ከኤሜላችን ጋር በማስተሳሰር ወደኢሜላችን ኮድ ወይም የሚስጥር ቁጥሮች እንዲላክን በማድረግ እኛ ራሳችን ስለመሆናችን የምናረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ.. ዘመኑ ረቅቋል፤ ዘመናዊ ሌባውም የዛኑ ያህል ተመንጥቋል፡፡ ስለዚህ ለአፍህም ለይለፍ ቃልህም ዘብ ቁም፡፡ አዕምሮህን ከክፉ ሃሳብ፣ አፍህን ክፉ ከመናገር፤ የማለፊያቃልህን ከመረጃ መንታፊዎች አድን፡፡ ራስህን ጠብቅ! ፓስወርድህን አጥብቅ!

ቸር ጊዜ!

____
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
ሐሙስ ሚያዚያ ፳፯ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም.

@Zephilosophy
@Zephilosophy
3.1K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 21:15:23
ለፍልስፍና አፍቃሪዎች በሙሉ እነሆ ምርጥ ቻናል ተከፍቶላችዋል

@Zephilosophy
ፍልስፍና ለነፃ አስተሳሰብ
https://t.me/joinchat/RVzIu0-BTYG_XaN8

በዚህ ቻናል ከተለያዪ የአለም ዳርቻዎች የተነሱ የታላላቅ ፈላስፋዎች አስተሳሰቦች እና ፍልስፍናዎች ይቀርባሉ።ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ፤ ከሰሜን እሰከ ደቡብ የአለምን የአስተሳሰብ ኮምፓስ የቀየሩ ፈላስፋዎች እና ሃሳቦቻቸው ከየመፅሀፉ እየተጨለፉ ለናንተ ይቀርባሉ። ከሶቅራጥስ እስከ ኒቼ ፤ ከቡድሃ እስከ ኦሾ ፤ ከማርክስ እስከ ሌኒን አለም ላይ የማይፋቅ አሻራዎቻቸውን ያሳረፋ ሰዎች ፤ ከክርስትና እስከ ቡዲሂዝም ፣ከእስልምና እስከ ሂንዲይዝም ፣ከሶሻሊስት እስከ ካፒታሊስት በዘመናት ውስጥ የተፈጠሩ ሀይማኖቶች ፣ስርዓቶች ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉ ይዳሰሳሉ። ለዓለም ያስገኙት ሞራላዊና መንፈሳዊ ትሩፋቶች ይወዳሳሉ። ታሪካዊ ህፀፆቻው ደግሞ ያለምህረት ይተቻሉ ፣ይወቀሳሉ።

ፍልስፍናን ከተደበቀችበት ጓዳ አውጥተን በአደባባይ እናሰጣታለን። ማህበረሰቡ የሚሳሳላቸው ባህሎቹ እና እምነቶቹ በነፃነት ይጠየቃሉ ፣ይመረመራሉ ይፈተናሉ። እንደ ጣት ቁስል የተፈሩ እውነቶች መሀረባቸው ይገለጣል። እንደ ማህበረሰብ በጉያችን የጋረድናቸው እባጮች የግንባር ስጋ ይሆናሉ።ከግለሰብ እስከ ቡድን ፤ከሀይማኖት እስከ ርዕዮተ -ዓለም
፤ ከኋለቀር ባህሎች እስከ ዘመናዊ ስልጣኔዎች ያለምንም ፍርሃት በግላጭ ይሞገታሉ፣ ይመረመራሉ፣ይጠየቃሉ ውስጣቸው የተደበቀው እውነት እስኪገለጥ ድረስ በአውድማው ላይ መንሽ እየተፈለገ ፍሬው ከገለባ ይለያል።
መንሻችን የሰላ አምክንዮዊ አእምሮ፣ የሰከነ የሞራል ልዕልና እና ንፁህ ሰዋዊ ህሊና ናቸው።

Join

@Zephilosophy
@Zephilosophy
5.4K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 23:36:18 አንድ ንጉስ አስር ተናካሽ ውሾች (Wild dogs) ነበሩት ፤ እነዚህን ውሾችም አገልጋዮቹን ‹አሽከሮቹን› ሲያጠፉ ለማሰቃየትና ለማስበላት ይጠቀምባቸዋል፡፡

ከእለታት አንድ ቀን አንደኛው አሽከሩ ትክክል ያልሆነ ሃሳብ ንጉሱን ተናገረው ፤ በዚህም ምክንያት ንጉሱ እጅግ ተቆጣበት ፤ ወዲውኑም ወደ ውሾቹ እንዲወረወር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

አሽከሩም በሀዘን "አስር አመታት አገለገልኩህ ፤ ተገዛውልህ ያልከኝን ሁሉ አደረኩልህ ፤ አሁን ግን ይህንን አደረክብኝ ፤ እባክህ ወደ ውሾች ውስጥ ከመወርወሬ በፊት አስር ቀን ስጠኝ" ብሎ ተማጸነው ንጉስም ተስማማ ‹ፈቀደለት› ፡፡

ይወረወር ዘንድ የተፈረደበት አሽከር ውሾቹን ወደሚንከባከበው ሌላኛው አሽከር ሔደና ‹እባክህ እነኝህን ውሾች ለአስር ቀን ልንከባከባቸው › ብሎ ጠየቀው፡፡ የውሾቹ ጠባቂም ግራ በመጋባት ሁኔታ ፈቀደለት ፡፡

የተፈቀደለት አሽከርም ውሾቹን መንከባከብ ጀመረ ፤ ቆሻሻቸውን ማጸዳዳት ፤ ምግባቸውን በሰአቱ ማቅረብ ፤ ማጠብና አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ አደረገላቸው ፤ አስር ቀኑም አለቀ፡፡

ከዚያም በኋላ ከንጉስ ጋር በተነጋገሩት መሰረት …አሽከሩ ተጠርቶ ወደ ተናካሽ ውሾቹ ዘንድ ይወረወር ዘንድ አዘዘ ፤ ወረወሩትም ፡፡ ወርዋሪዎቹም ይህ አሽከር እንዴት በውሾቹ ሊበላ እንደሚችል እየዘገነናቸው መመልከት እንደጀመሩ ያላሰቡትን ሁኔታ በአይናቸው አዬ ፤ ንጉሱም በሚመለከተው ሁኔታ ግራ ተጋባና «በእነዚህ ተናካሽ ውሾቼ ላይ ምን ደረሰ ? ምንስ ገጠማቸው?» ማለት እንደጀመረ… የተወረወረው አገልጋይ በውሾቹ መሃል እየተሻሼ በኩራት እየተራመደ እንዲህ አለ "እነዚህን ውሾች ለአስር ቀናቶች ብቻ መገብኳቸው ተንከባከብኳቸው እነርሱም ያደረኩላቸውን በፍጹም አልዘነጉም ፤ አንተን ግን አስር አመት ሙሉ ተገዛሁልህ አገለገልኩህ ነገር ግን በአንዲት ጥፋት ምክንያት ሁሉንም ረሳህና ለሞት አሳልፈህ ሰጠኸኝ" አለው ፡፡

ንጉሱም ሁኔታውን ሁሉ በማስተዋልና ፤ ከውሾች እንዳነሰም በመገንዘብ አገልጋዬ ነጻ እንዲሆን አዘዘ ፤ ነጻም ሆነ፡፡

#ይህ_መልእክት ሰው በጣም ብዙ ውለታ ውሎላቸው ነገር ግን በአንድ ጥፋት ምክንያት የተደረገላቸውን ሁሉ እየረሱ በክፋት ለሚነሳሱ ሁሉ ይሁን፡፡ በመልካም ነገር የተሞላ ታሪክን ፤ በአንድ ስህተት ምክንያት ከንቱ አናድርግ፡፡

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
11.0K viewsedited  20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 22:48:13 ....

የአብዛኛዎቻችን ወላጆች ልጅ አዋቂ እንዲሆን ከበላ ፣ትምህርት ቤት ከተላከ፣ የሚያድርበት ማደሪያ ካለው፣ ካልታረዘ በቃ የተቀረው አድጎ አዋቂ፣ ሀላፊነት ተቀባይ ለመሆን የልጁ የራሱ ሀላፊነት እንደሆነ ያስባሉ።

አባትሽ ትምህርት ቤት ሲጠራ «አንቺ መቼም ሰው አትሆኚም! ሁሌም እንዳዋረድሽኝ» የሚልሽ ተደጋጋሚ ወቀሳ ሰው እንዳትሆኚ ወደታች እንደሚጎትትሽ አያስተውልም።

አጎትሽ ድንገት ከአምስት ዓመት አንዴ መጥቶ «ውይ እቴቴ በዝህችኛዋስ አላደለሽም! ትልልቆቹን ይባርክልሽ እንጂ እቺ መቼም ሰው አትሆንም!» ብሎ ለእናትሽ ባዘነ ሙድ ሲነግራት አንቺ ይዘሽው የምታድጊው ከንቱነት እያቀበለሽ እንደሆነ አይገነዘቡልሽም።

አፏ የማያርፍ አክስትሽ «እቴትዬ ይህቺኛዋስ ደህና አማች ታመጣልሽ እንደው እንጂ ትምህርቱስ አልሆናትም!» ስትልሽ እናትሽ አብራ ትስቃለች እንጂ በማንም ፊት የማትረቢ እንደሆንሽ እያመንሽ ራስሽን እንደምትቀጪ አትገነዘብም!

ወላጆች ልጆቻቸውን በዱላ ሲቀጡ የሚታያቸው ዱላው ደም አለማፍሰሱ ነው። ወይም አጥንት አለመስበሩ፣ እዛ ደረጃ ካልደረሰ ልጁ እየተቀጣ እንጂ እየተጎዳ አይደለም። ትምህርት እየሰጡት ነው።

ዱላው ሰውነቱ ላይ ሊያርፍ በተዘረጋ ቁጥር ከሰውነቱ መሸማቀቅ ጋር በዘመኑ ሁሉ አብሮት የሚጓዝ በራስ ያለመተማመን እያሳጨዱት እንደሆነ አያውቁም። ሰውነቱ ላይ ባረፈው ዱላ ልክ ፈሪ እና ሸምቃቃ ልጅ እያፈሩ እንደሆነ አያውቁም! ሲቀጠቅጡት ያሳደጉትን ልጅ አድጎ በሰዎች ፊት መብቱን አንገቱን ሳይደፋ የሚጠይቅ ኩሩ ባለመሆኑ ይወቅሱታል። ከነዛ የዱላ ሰንበሮች ጋር በራስ መተማመኑ መክሰሙን አያስተውሉም። የዱላው ቁስል አይደለም ከልጁ ጋር አብሮ የሚኖረው ስሜቱ ነው። ፍርሃቱ፣ አንገት መድፋቱ፣ እንዳያስረዳ እንኳን <ዝም ጭጭ!> ተብሎ የዋጠው የመጠየቅ እና የመናገር መብቱ፣ ሰቀቀኑ ………… ያ ነው አብሮት የሚያድገው።

ሜሪ ፈለቀ


@Human_Intelligence
12.9K viewsedited  19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 09:45:35 በመላው አለም ለምትኖሩ የእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ1443ኛው የዒደል አድሃ በአል በሰላም አደረሳችሁ!!

ኢድ ሙባረክ!!
11.6K views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 22:17:23 “የመገፋት ስስነት”
(“የመገፋት ህመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በስነ-ልቦናው ቋንቋ “የመገፋት ስስነት” (Rejection Sensitivity) የተሰኘው ሃሳብ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው የሚያጋጥማቸውን ጥቃቅን የሰዎች ሁኔታ ከመገፋትና ከመገለል ጋር የማዛመድ ስስነትንና ዝንባሌን የሚያሳይ ጽንሰ-ሃሳባ ያመለክታል፡፡

አንዳንድ ሰዎች በመገፋት ዙሪያ እጅግ ስስ ከመሆናቸው የተነሳ እንደተገፉ የመሰላቸው ማንኛውም አይነት ሁኔታ ሲመለከቱ የመደናገጥና የመዋረድ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ሰዎች ሲያስጠብቋቸው፣ ስልካቸውን ካልመለሱላቸውና እንደዚህ የመሳሰሉ “አናሳ” የሆኑ ክስተቶች የዝቅተኝትን፣ የመናቅንና የመገለልን ስሜት ያመጣባቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ዝንባሌን አስመልክቶ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፣ የዚህ ተጽእኖ ሰለባዎች፣ ሰዎች በፊት ገጽታቸው የሚያሳዩት ሁኔታ እነሱን ያለመቀበልና የመግፋት ምልክት እንዳለው ሲሰማቸው የአንጎል እንቅስቃሴያቸው (Brain Activity) በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ጥናቶቹ ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም፣ እነሱን የመግፋት ወይም የማግለል ገጽታ ሊኖረው የሚችልን ማንኛንም እንቀስቃሴም ሆነ ንግግር በንቃትና ሁኔታዎችን በማዛመድ የመመልከትና የመጠባበቅ ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡

የዚህ ዝንባሌ አንዱ ጫና፣ አድልዎ-ተኮር ምላሽ (Attention Bias) ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ለአስር ሰዎች የፍቅር ጥያቄ አቅርበው ዘጠኙ ተቀብለዋቸው አንዱ ብቻ ፍላጎት እንደሌለው ቢገልጽላቸው፣ እነሱ የሚያተኩሩትና ስሜታቸውን የሚነካው የዘጠኙ እሺታ ሳይሆን የአንዱ እምቢታ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትኩረትን ከመገፋት አንጻር ብቻ የመቃኘት አድሎአዊ አመለካከት የሚያስከትልባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ በግል ሕይወታቸውም ሆነ በማሕበራዊ ግንኙነታቸው ላይ የሚስከትለው መዘዝ ቀላል አይደለም (ምንጭ፡- verywellmind.com)፡፡

ሁኔታውን ስንጨምቀው፣ በመገፋት ስቃይ ውስጥ ያለፈ ሰው የሰዎችን፣ በተለይም በእነሱ ሕይወት ስፍራ እንዳላቸው የሚሰማቸውን ሰዎች እያንዳንዱን ተግባር በመገመት በመላ-ምት የመኖር ዝንባሌ ያጠቃቸዋል፡፡ ይህ አሉታዊ-ገማችነት ገደብ የሌለው ሃሳብ-ወለድ አለም ውስጥ እንዲዋዥቁና የሌለንና ያልተፈጠረን ነገር በውስጣቸው እንዲያሰላስሉ ያደርጋቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች አንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት አለም ውስጥ ከገቡ በኋላ ሲያሰላስሉት ውለው ያደሩት ነገር በእነሱ ውስጥ “የሌለ እውነታ” ሆኖ ይኖራል፡፡ የዚህ ስሜት ውጤት ሰዎች የሚያደርጓቸውንም ሆነ የማያደርጓቸውን ነገሮች እየለቀሙና እየቆጠሩ ካለባቸው “የመገፋት ስስነት” ጋር የማዛመዝ ሁኔታ ነው፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች የሚሰማቸው ስሜት በእርግጥም ከእውነተኛ የመገፋት ልምምድ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ለመገፋት ስሜት ስስ እንዲሆኑ ከዳረጋቸው ከእውነታ የራቀ እይታም ሊነሳ ይችላል፡፡ መነሻው ያም ሆነ ይህ፣ ሰዎች በዚህ የስሜት ተጽእኖ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላለባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ትክክለኛውን መፍትሄ እንዲፈልጉ ይመከራሉ፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
12.1K viewsedited  19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 21:24:58 ባንዲት ነጭ ፀጉር ላይ

ከአሌክስ አብራሀም

@Human_Intelligence
9.7K viewsedited  18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ