Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 88.58K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2022-08-15 19:47:16 ፍራሽ አዳሽ

በተስፋሁን ከበደ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
10.7K viewsedited  16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 20:19:37 "ሰው ሁሉ የመናገር ነፃነቴን ተቀማሁ እያለ ይጮኻል፤ማንም የማይነካበትን የማሰብ ነፃነቱን ግን አይጠቀምበትም።"
ሶረን ኪይጋርድ

"አንድን ነገር መቼም ላላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ስታውቅ ደግሞ መቼም ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው!!"
ኮንፊሽየስ

ሁለት የሞኝነት መንገድ አለ ። አንደኛው እውነት ያልሆነውን ማመን ሲሆን ሌላኛው እውነት የሆነውን አለማመን ነው ።
ሶረን ኪድጋርድ


" ንግግር ከማድረግህ በፊት ንግግርህን በነዚህ ሶስት በሮች ፈትሸህ አሳልፈው...
ትክክል ነው ወይ?
አስፈላጊ ነው ወይ?
በጎ ነገር ነው ወይ? "
ሩሚ

"ሁሉም ሰው ሞትን ይቀምሳል ህይወትን የሚቀምሰው ግን በጣም ጥቂቱ ነው።"
ሩሚ

" ፍቅር ያልነካው እሱ በጨለማ ውስጥ እንደሚጓዝ ፍጡር ነው "
ፕሉቶ

"በአለም ላይ ከብዙ ሰው ጋር ትገናኛላችሁ ግን በጭራሽ ከራሳችሁ ጋር ተገናኝታችሁ አታውቁም።"
ኦሾ

"እንደ ወንድማማቾች መኖር ካለመድን እንደ ሞኞች አብረን እንጠፋለን።"
ማርቲን ሉተር ኪንግ

"በሰዎች በጥልቅ መወደድ ጥንካሬን ይሰጣችኋል። ሰዎችን በጥልቅ መውደድ ደግሞ በወኔና በድፍረት ይሞላችኋል።"
ላኦ ዙ

."ውለታ እንዲዋልላቸው ውለታ የሚውሉ ነጋዴዎች እንጂ የልብ ወዳጆች አይደሉም።"
ሀዲስ አለማየሁ

‹በህግ አንድ ሠው የሌላን ሠው መብት ከተጋፋ ወንጀለኛ ነው፡፡ በስነምግባር ግን አንድ ሠው ሌላ ሠው ላይ ክፉ ማሠቡ ብቻ ወንጀለኛ ያደርገዋል፡፡››
ኢማኑኤል ካንት


."ታላቁ ጦርነት ወይም ታላቁ ጅሃድ ራስን ማሸነፍ ነው፡፡"
ነብዩ መሀመድ


"ራሳችሁን ሆናችሁ ተፈጥራችሁ እስከመቼ የካርቦን ቅጂ ሆናችሁ ትኖራላችሁ። ማንም ከራሱ በስተቀር ሌሎችን መሆን የለበትም፡፡"
ኦሾ


@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
14.4K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 13:01:00
ለፍልስፍና አፍቃሪዎች በሙሉ እነሆ ምርጥ ቻናል

@Zephilosophy
ፍልስፍና ለነፃ አስተሳሰብ
https://t.me/joinchat/RVzIu0-BTYG_XaN8

በዚህ ቻናል ከተለያዪ የአለም ዳርቻዎች የተነሱ የታላላቅ ፈላስፋዎች አስተሳሰቦች እና ፍልስፍናዎች ይቀርባሉ።የአለምን የአስተሳሰብ ኮምፓስ የቀየሩ ፈላስፋዎች እና ሃሳቦቻቸው ከየመፅሀፉ እየተጨለፉ ለናንተ ይቀርባሉ።ከሶቅራጥስ እስከ ኒቼ ፤ ከቡድሃ እስከ ኦሾ ፤ ከማርክስ እስከ ሌኒን አለም ላይ የማይፋቅ አሻራዎቻቸውን ያሳረፋ ሰዎች ፤ ከክርስትና እስከ ቡዲሂዝም ፣ከእስልምና እስከ ሂንዲይዝም ፣ከሶሻሊስት እስከ ካፒታሊስት በዘመናት ውስጥ የተፈጠሩ ሀይማኖቶች ፣ስርዓቶች ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉ ይዳሰሳሉ። በዘመናት ውስጥ የተፈጠሩ ሀይማኖቶች ፣ስርዓቶች ርዕዮተ ዓለሞች ሁሉ ይዳሰሳሉ። ለዓለም ያስገኙት ሞራላዊና መንፈሳዊ ትሩፋቶች ይወዳሳሉ። ታሪካዊ ህፀፆቻው ደግሞ ያለምህረት ይተቻሉ!!

ማህበረሰቡ የሚሳሳላቸው ባህሎቹ እና እምነቶቹ በነፃነት ይጠየቃሉ ፣ይመረመራሉ ይፈተናሉ። እንደ ጣት ቁስል የተፈሩ እውነቶች መሀረባቸው ይገለጣል። እንደ ማህበረሰብ በጉያችን የጋረድናቸው እባጮች የግንባር ስጋ ይሆናሉ።ከግለሰብ እስከ ቡድን ፤ከሀይማኖት እስከ ርዕዮተ -ዓለም
፤ ከኋለቀር ባህሎች እስከ ዘመናዊ ስልጣኔዎች ያለምንም ፍርሃት በግላጭ ይሞገታሉ፣ ይመረመራሉ፣ይጠየቃሉ ውስጣቸው የተደበቀው እውነት እስኪገለጥ ድረስ በአውድማው ላይ መንሽ እየተፈለገ ፍሬው ከገለባ ይለያል።
መንሻችን የሰላ አምክንዮዊ አእምሮ፣ የሰከነ የሞራል ልዕልና እና ንፁህ ሰዋዊ ህሊና ናቸው።

Join

@Zephilosophy
@Zephilosophy
15.5K viewsedited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 06:16:26 ዛሬና መጪው ሳምንት የሰላም ውሎ እንዲሆንላችሁ ከፈለጋችሁ እነዚህን ሶስት ነገሮች ላቀብላችሁ . . .

1. ምንም ብታደርጉም ፈጽሞ ለውጥ የማታመጡትን ነገር ስታሰላስሉ አትዋሉ፡፡ መለወጥና ማስተካከል በማንችለው ነገር ላይ ጊዜያችንንና ስሜታችንን ካባከንን ሰላማችን ይናጋል፡፡

2. እጃችሁ ከገባና እናንተ ጋር ከደረሰ በኋላ የት እንደምትወስዱትና ምን ነገር ላይ እንደምታውሉት የማታውቁትን መረጃ ለመስማት ከመሞከር ተቆጠቡ፡፡ ከቀንደኛው የሰላም ጸሮች መካከል አንዱ፣ እጃችን ከገባ በኋላ ለምንም ነገር የማይጠቅም መረጃን የመስበስብ ልማድ ነው፡፡ ስራ ላይ የማናውለው መረጃ ውስጣችንን ታምቆ ሰላም ይነሳል፡፡

3. ማስታወስ በሚገባችሁና በመይገባችሁ ያለፉ ልምምዶች መካከል ለመለየት ሞክሩ፡፡ ጤና-ቢስ ልምምዶቻችሁን አንድ ጊዜ ትምህርታችሁን ካገኛችሁባቸውና ወደፊት ከተራመዳችሁ በኋላ እንደገና ላለማስታወስ ሞክሩ፡፡ ያለፉትን ጤና-ቢስ ልምምዶች ማሰላሰል ልምምዱን እንደገና እንደመኖር ያህል ነው፤ ውስጥም ያደክማል፤ ሰላም ይነሳል፡፡

የሰላም ቀን ይሁንላችሁ፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
16.2K viewsedited  03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 07:03:39 አንዴ ከሄዱ ብትለምኗቸው የማይመለሱ አራት ነገሮች!

ምንጩ ያልታወቀ አንድ ማስታወሻ፡-

በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯችሁ አራት ነገሮች፡-

“እድል” - አንዴ ካመለጣችሁ በኋላ!

“ቃል” - አንዴ ከአንደበታችሁ ከወጣ በኋላ!

“ጊዜ” - አንዴ ሳትጠቀሙበት ካለፈ በኋላ!

“አመኔታ” አንዴ ከጎደለ በኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡

1. “እድል” - በአጋጣሚም ሆነ ጠንክራችሁ በመስራታችሁ የመጣን እድል መለየት፣ ማክበርና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም፡፡

2. “ቃል” - ሁኔታዎች ሲገፋፏችሁም ሆነ እንዲሁ ስለለመደባችሁ በቀላሉ የምትናገሯቸውን ሰው ጎጂ ንግግሮች በሚገባ ማሰብና ራስን መግታት፡፡

3. “ጊዜ” - በሆነ ባልሆነ የምታባክኑትና አሁን ባላችሁ እድሜ ማድረግ የሚገባችሁን ነገር ባለማድረግ የምታባክኑትን ጊዜ በጥንቃቄ መያዝ

4. “አመኔታ” - ሰዎች ሲያምኗችሁና ራሳቸውንም ሆነ ነገሮቻቸው በእናንተ ላይ ሲጥሉ እምነት ከማጉደል መጠበቅ፡፡

በሉ እንግዲህ፣ ያለፈው አልፏል፣ የባከነው ባክኗል፡፡ የተራረፈውን እንሰባስበውና ሕይወትን እንደገና በአዲስ መልክ እንጀምር፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
22.6K views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 22:19:47
ከፍ ያለ ቦታ ላይ ስትሆን ኩራት (PRIDE) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ኩራት አንተ የደረስክበት የስኬት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ሰዎችን በንቀት እንድትመለከት ያደርግሃል፡፡

ታችኛው ክፍል ላይ ስትሆን ፣ ምሬት (BITTERNESS) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ምሬት ቅናት እንዲሰማህ እና አንተ ያልተሳካልህ በሌሎች ሰዎች ምክንያት እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል፡፡

ወደ ላይኛው መንገድ ስትጓዝ ስግብግብነት (GREED) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ስግብግብነት ትዕግሥት ያሳጣሃል እናም እንድትሰርቅ ወይም አቋራጮችን እንድትፈልግ ያደርግሃል።

ወደ ታች በምትወርድበት ጊዜ ፣ ተስፋ መቁረጥ (DESPAIR) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ፣ ሁሉም ነገር ተጠናቋል ብለህ እንድታስብ ሊያደርግህ ይችላል።

ኔልሰን ማንዴላ

@Human_Intelligence
21.7K viewsedited  19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 18:17:23
ድምጹ ይስተካከል!

ዛሬ . . . የስሜታችሁን ድምጽ ቀነስ፣ የአእምሮ ስሌታችሁን ድምጽ ጨመር . . . ሰዎች ስለእናንተ የሚያስተጋቡትን ድምጽ ቀነስ፣ እናንተው ስለራሳችሁ የምታውቁትን የእውነታ ድምጽ ጨመር . . . ያልሆነውንና ያልተሳካውን ነገር ድምጽ ቀነስ፣ የተሳካውንና መስመር የያዘውን ሁኔታ ድምጽ ጨመር . . . ግራ የገባችሁንና እርግጠኛ ያልሆናችሁበትን ሁኔታ ድምጽ ቀነስ፣ እርግጠኛ የሆናችሁበትን ሁኔታ ድምጽ ጨመር . . . የማይቀበሏችሁንና የማይወዷችሁን ሰዎች ድምጽ ቀነስ፣ የሚወዷችሁንና የሚናፍቋችሁን ሰዎች ድምጽ ጨመር . . . አድርጉ!

ብልህ ሁኑ! ለክፉው አትገኙ! አመዛዝኑ! የምታስቡትንና የምታምኑትን ለዩ!


ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
23.4K viewsedited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 16:25:44 መላውን ዓለም ከመጨበጥ ይልቅ ራስን መጨበጥ የተሻለ ነው

ምንጭ ፦ ህያውነት ፫ (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ ሀብታሙ ተስፋዬ
ተስፋሁን ምትኩ

ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው - እንደ አንድ እምቅ አቅም፡፡ ሲወለድ ልከኛ ሆኖ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ልዩ ነው - ምክንያቱም በመላው ህልውና ውስጥ ሰው ብቻ ነው አንድ አቅም ሆኖ የሚወለደው፤ ሌሎች እንስሳት ልከኛ ሆነው ነው የሚወለዱት፡፡

አንድ ውሻ ሲወለድ ውሻ ሆኖ ነውና መላ ህይወቱንም እንዲያ ሆኖ ይኖራል። አንድ አንበሳ ሲወለድ አንበሳ ሆኖ ነው፡፡ ሰው ሲወለድ ግን ሰው ሆኖ አይደለም፡፡ ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው። ሰው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ሰው የወደፊት ተስፋ አለው! ሌሎች እንስሳት ግን ተስፋ የላቸውም፡፡ ሁሉም እንስሳት ሲወለዱ በደመነፍስ ፍፁም ሆነው ነው፡፡ ሰው ብቸኛው ፍፁም ያልሆነ እንስሳ ነው። ስለዚህም በሰው ላይ እድገት፣ ዝግመተ - ለውጥ ይቻላል።

ትምህርት በእቅምና በልከኝነት መካከል ያለ ድልድይ ነው። ትምህርት በዘር መልክ ራሳችሁን እንድትሆኑ ያግዛችኋል፡፡ በተራ ትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት አይደለም። በእነዚህ ተቋማት የምታገኙት ትምህርት ጥሩ ስራ፣ ጥሩ ገንዘብ እንድታገኙ የሚያደርጋችሁ ብቻ ነው:: እውነተኛ ትምህርት አይደለም፤ ህይወትን አይሰጣችሁም። በቃ የኑሮዋችሁን ደረጃ ከፍ ቢያደርገው ነው፤ ነገር ግን የተሻለ ኑሮ የተሻለ ህይወት አይደለም፤ ሁለቱ አንድ አይደሉም።

በዓለም የሚሰጠው ትምህርት ተብዬ ነገር ዳቦ እንድታገኙ ብቻ የሚያዘጋጃችሁ ነው። ኢየሱስ እንዳለው «ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም::>> ዩኒቨርሲቲዎቻችሁ ደግሞ ይህን ነው እያደረጉ ያሉት - በተሻለ፣ በቀለለ፣ በተመቸ፣ ጥረት፣ ድካም በሌለበት መንገድ ዳቦ እንድታገኙ ያግዛችኋል። ስራቸው በሙሉ እናንተን ዳቦና ቅቤ እንድታገኙ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትምህርት በጣም፣ በጣም ኋላቀር ነው:: ለህይወት አያዘጋጃችሁም፡፡

ስለዚህም ብዙ ሮቦቶች ሲረማመዱ ታያላችሁ:: እንደ ተላላኪዎች፣ የጣቢያ ተቆጣጣሪዎች፣ ዋና ሰብሳቢዎች ብቃት አላቸው:: ፍፁማን ናቸው፣ ጥበበኞች ናቸው:: በጥልቀት ብትመለከቷቸው ግን ለማኞች እንጂ ሌላ ምንም እንዳልሆኑ ትረዳላችሁ፡፡ የህይወትን እንዲት ቅንጣት እንኳን አልቀመሱም፡፡ ህይወት ምን እንደሆነ፣ ፍቅር ምን እንደሆነ፣ ብርሃን ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ ስለ እግዚአብሄር ምንም አያውቁም፣ ህልውናን አልቀመሱም፣ እንዴት መዝፈን፣ መደነስ፣ መደሰት እንዳለባቸው አያውቁም:: የህይወትን ሰዋሰው የማያውቁ መሀይማን ናቸው። አዎ፣ ከሌሎች የበለጠ ያገኛሉ፤ ከሌሎች የበለጠ ብልጣ ብልጦች ናቸው፤ በስኬት መሰላል ከፍ ብለው ይወጣሉ - በውስጣቸው ግን ባዶ፣ ምስኪኖች ናቸው፡፡

ትምህርት ውስጣዊ ብልፅግናን ያጐናፅፋል፡፡ የበለጠ መረዳ መስጠት በጣም ኋላቀር የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ኋላ ቀር ነው ያልኩት በፍርሃት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው፤ ካልተማርኩ በህይወት መቆየት አልችልም፣ በሚለው አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ሗላቀር ነው ያልኩት በውስጡ ነውጥን ስላዘለ ነው፤ ውድድርን ያስተምራችሗል፣ ምኞታም ያደርጋችኋል። ሌላ ምንም ሳይሆን ሰዎች እርስ በርስ የሚጠላሉበት የውድድር ዓለም ለመፍጠር የሚደረግ ዝግጅት ነው።

ስለዚህም ዓለም የእብዶች መኖሪያ ሆናለች። በዚህ ሁኔታ ፍቅር ሊወጣ አልቻለም። አንዱ የሌላኛውን ጉሮሮ በሚበጥስበት በዚህ ነውጠኛ፣ ምኞታም የውድድር ዓለም ውስጥ እንዴት ፍቅር ሊታይ ይችላል? ሗላ ቀር ነው ያልኩት «በደንብ ካልተማርኩ፣ በቂ ከለላ ካላገኘው፣ ደህና መረጃ ካልያዝኩ በህይወት ፈተና ውስጥ አሸናፊ አልሆን ይሆናል>> በሚል ፍራቻ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ህይወትን እንደ ትግል ብቻ ነው የሚመለከታት፡፡

እኔ ትምህርትን የማየው ህይወትን እንደ ትግል ሳይሆን እንደ ደስታ ሲቀርፅ ነው፡፡ ህይወት ውድድር ብቻ መሆን የለባትም፣ ደስታ ጭምር እንጂ፡፡ ትምህርት በዓለም ላይ ከሚገኙ ዘፈን፣ ዳንስ፣ ቅኔ፣ ሙዚቃ፣ ስዕል፤ ዛፎች፣ አዕዋፋት፣ ሰማይ፤ ፀሃይ፣ ጨረቃ እና ሌሎች ነገሮች በሙሉ ሊያዋህዳችሁ ይገባል፡፡

ትምህርት ራሳችሁን እንድትሆኑ ሊያዘጋጃችሁ ይገባል። አሁን ግን አስመሳዮች እንድትሆኑ እያዘጋጃችሁ ነው፤ ሌሎችን እንዴት መምሰል እንዳለባችሁ እያስተማራችሁ ነው፡፡ ይህ ትምህርት ማሳት ነው፡፡ ትክክለኛ ትምህርት ራሳችሁን በእውነተኛ መንገድ እንዴት እንደምትሆኑ ያስተምራችኋል። እናንተ የተለያችሁ ናችሁ። እናተን የሚመስል ማንም የለም ፡ ወደፊትም አይኖርም። ይህ እግዚአብሄር ያጐናፀፋችሁ ታላቅ በረከት ነው። ይህ የእናንተ ክብር ነው! ልዩ መሆን ነው፡፡ አስመሳይ አትሁኑ፤ የካርቦን ቅጂዎች አትሁኑ።

እናንተ ትምህርት የምትሉት ነገር ግን ይህን እያደረገ ነው፡፡ የካርቦን ቅጂዎችን ይፈጥራል፤ እውነተኛ መልካችሁን ያጠፋል። <<ትምህርት>> የሚለው ቃል ሁለት ትርጉሞች አሉት፤ ሁለቱም ደግሞ ውብ ናቸው። አንደኛው ትርጉሙ ተግባር ላይ ባይውልም በደንብ ይታወቃል- አንድ ነገር ከውስጣችሁ ማውጣት። <<ትምህርት» ማለት በውስጥ ያለን ማውጣት፣ ውሀን ከጉድጓድ እንደ ማውጣት አቅምን በተግባር ማውጣት ነው።

ይህ ግን አልተተገበረም፡፡ ከዚህ ይልቅ ነገሮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ እንጂ እንዲወጡ አልተደረገም። ህብረተሰብ እና ታሪክ፣ ሳይንስ እና ሂሳብ ወደ ውስጣችሁ ያንቆረቁርላችኋል። እናም ፓሮቶች ትሆናላችሁ። ልክ እንደ ኮምፒዩተር ይጉሰጉሱባችኋል:: የእናንተ የትምህርት ተቋማት ነገሮች በጭንቅላቶቻችሁ ውስጥ የሚታጨቁባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡

እውነተኛ ትምህርት በውስጣችሁ የተደበቀውን (እግዚአብሔር በውስጣችሁ እንደ ሃብት ያስቀመጠውን) አውጥቶ፣ ገልጦ አንፀባራቂ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፡፡

ትምህርት ሌላም ትርጉም አለው:: ትምህርት (Education) የሚለው ቃል የመጣው Educare ከሚለው ቃል ነው:: ትርጉሙም ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት እንደማለት ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት በጣም አስፈላጊ ትርጉም አለው፡፡ ዮፓኒሻዶች እንዲህ ይላሉ «ጌታችን ሆይ፣ ከሃሰት ወደ እውነት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ፣ ከሞት ወደ ህይወት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ ከጨለማ ወደ ብርሃን ምራን፡፡» ይህ ነው «የትምህርት» ትክክለኛ ትርጉም፡- ከጨለማ ወደ ብርሃን።

ሰው ግን በጨለማ፣ ባለመንቃት ውስጥ እየኖረ ነው:: ሆኖም በብርሃን ምሉዕ መሆን ይቻላል፡፡ ነበልባሉ እዚያ አለ፡፡ ይሁንና መንበልበል፣ ወደ ውጭ መውጣት አለበት፡፡ ንቃት እዚያ አለ፤ ይሁን እንጂ መቀስቀስ አለበት:: ሁሉም ነገር ተሰጥቷችኋል! ስትወለዱ ይዛችሁት መጥታችኋል፡፡ ሰብአዊ አካል ስላለን ብቻ ሰው ነን ማለቱ ስህተት ነው፡፡ ለዘመናት ለብዙ መሳሳቶች መንስኤ የሆነው ይህ አስተሳሰብ ነው፡፡

ሰው ሲወለድ እንደ አንድ እድል፣ ሁኔታ ሆኖ ነው። ይህን የተጠቀሙበት ደግሞ እጅግ ጥቂቶች ብቻ ናቸው - ኢየሱስ፣ ቡድሀ፣ መሐመድ፣ ባሃውዲን። እውን ሰው የሆኑት እጅግ ጥቂቶች ናቸው- በብርሀን ሲመሉ የቀረ ጨለማ አይኖርም፣ በነፍስ ውስጥ የሚተርፍ አለመንቃት አይኖርም- ሁሉም ነገር ብርሃን ሲሆን፣ እናንተ ንቃትን ስትሆኑ...

ንቃት፣ ንቃት ብቻ፣ ንፁህ ንቃት... ይህ ያለው ብቻ ምሉዕ ይሆናል። ይሄን ጊዜ ህይወት ቡራኬ ትሆናለች።

ትምህርት ከጨለማ ወደ ብርሃን ይወስዳችኋል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
19.7K views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 21:02:11 አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣአልተፈቀደምና ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡

‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ላለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገር›› አሉት፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸው ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሐሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡

በመጨረሻም ለዋናው ኃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁን ድረስ ‹‹ለምን›› ብሎ የጠየቀኝ ባለመኖሩ ነበር፡፡ አንተ ‹‹ #ለምን ?›› ስላልከኝ አመሰግንናለሁ፡፡ በመሠረቱ ግን ሻንጣው የእኔ #አይደለም ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው፡፡

አብዛኞቻችን በሰዎች ላይ በደፈናው እንፈርዳለን፡፡ ነገር ግን ሁሌም በደፈናው ከመፍረዳችን በፊት "ለምን?" ብሎ መጠየቅም እውቀት ነው፡፡

@Human_Intelligence
18.9K viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 12:01:43 አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና "ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሃን ናቸው። ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም" አለ እግዚአብሔርም መለሰለት "ልጄ ሆይ! አዎ እጆችህ ንፁሃን ናቸው ግን ባዶዎች ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።

@Human_Intelligence
25.6K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ