Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 88.58K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-10-14 22:03:09 ​ ለአንድ ማህበረሰብ እድገት ግልፅነት ወሳኝ ነው። የማህበረሰብ ግልፅነት ደግሞ ከእያንዳንዱ ግልሰብ ግልፅነት ይመነጫል።

የግለሰብ ግልፅነት ደገሞ እረስን ማፋጠጥ ይጠይቃል። እኛ እንኳን ለሌላው ለራሳችንም ግልፅ አይደለንም። ውስጣችንን በሁለት ጎራ ከፍለን እናፋጃለን። ይህም ሌላው ሰው ካሳደረብን ጫና ይልቅ በራሳችን ላይ ትልቅ ሸክም ጭነን እንዞራለን።

ውስጣችን የሚሄድ ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሚንቀሳቀስ ነገር አለ። ይህ ነገር በግልፅ ልንጋፈጠው ይገባል።

ምንም ሊሆን ይችላል። ከተራ ሀሳብነት እስከ መርዛማ አመለካከት ድረስ ሊደርስ ይችላል። ግን ምንም ይሁን ምን ውስጣችንን ለሁለት ከፍሎ ማፋጀቱ አይቀርም። ግልፅነት ይጎለናል። ምናስበውን እንዳንሆን ወይም ደግሞ ማናስበው እንድንሆን ያረጋናል። ምናስበውን እንዳናወራ ወይም ያላሰብነውን እንድናወራ ያደርገናል። ያሰብነውን በተቃራኒው እንድንሄድ ይገፋፋናል።

ከአስተሳሰባችን ፍፁም ተቃራኒ የምንሄድበትም ምክንያት ይሄ ነው። ምናልባት የተቀደሰ ሀሳብ ይዘን ተነስተን ይሆናል። ነገር ግን ይህን በግልፅ ውስጣችን ማስረፅ ካልቻልን ወደ ፍጅት ውስጥ እንገባለን። ተግባርና ሀሳብ ሌላ ይሆናል። የተቀደሰው ሀሳባችን በትግባር ግን እርኩሰትን ይፈጥራል። በግልፅነት አልታጀበማ። ተግባሩ እርኩሰት ነው ብለን እንኳን ለማውገዝ አሁንም ግልፅነት ያስፈልጋል።

ስለሚሰሙን ስሜቶች ስለምናስበው ሀሳብ በተግባርም ሲለወጥ ስለሚያመጣው ውጤት በግልፅ ከራሳችን ጋር ቁጭ ብለን መገምገም ይኖርብናል። አደባብሶ ማለፍ የሚፈልግ ሁሌ ልክ ነኝ የሚል አስተሳሰብ ውስጣችን ይከሰታል። ነገር ግን ችላ ብለነው በግልፅነት ልናወራበት ይገባል።

እውነታን መቃወም (Resisting Reality) የሚባል ነገር አለ። ይህን ነገሮችን እንደሆኑት እና እንደ አፈጣጠራቸው ከመቀበል ይልቅ እራሳችን እንዲሆንና ቢሆን በሚል ፍላጎት ብቻ እንተረጉማለን። የሀሳባችን ውጤት መጥፎ ሆኖ ሳለ እውነታን በመቃወም ጥሩ ለማረግ እንሞክራለን። እውነታው ግን ህሊና ከእውነት ጋር እንጂ እኛ እንደምናስበው አይሄድምና ግልፅነት እንደጎደለን ከመናገር ወደሁአላ አይልም። ለዛም ነው ለራስ እውነታ ግልፅ አለመሆን ሸክም የሚሆነው።

ስለ ግንኙነታችን ፤ ስለህይወታችን ፤ ስለትዳራችን ፤ ስለ አስተሳሰባችን ፤ ስለ ህይወት መርሀችን ግልፅ የሆነ እውነታ መያዝ አለብን። ያኔ የጎበጠውን ለማቅናት ፥ የተንሻፈፈውንም ለማስተካከል እውቀት ይኖረናል።

በሽታን ለማከም ግልፅ የሆነ የበሽታው መኖር መረጋገጥ አለበት። በሽታው እንዳለን ካላመንን ግን መቼም መዳን አንችልም። የመፈወስ የመጀመርያው እርምጃ ህመሙ መኖሩን ማመን ነው። ከዛ የሚደረገው ነገር ይደረጋል። ሁሉም ለራሱ ግልፅ መሆን ሲጀምርና እውነታን መቃወም ሲያቆም ያኔ ድምር ውጤቱ የማህበረሰብ ግልፅነትን ይፈጥራል።

ለራሴ ምን አየዋሸው ነው? አሁን በዚህ ቅፅበት ለራሴ ግልፅ ያልሆንኩት ምንድነው? አስተሳሰቤና ድርጊቴ ተስማምተዋል ወይስ እየተቃረኑ ነው? ብቻዬን ስሆና ከሰው ጋር ስሆን ያለኝ አመለካከት አንድ ነው? ሰው ጋር ስሆን ጥሩ እሱ ሲሄድ በውስጤ እያማሁት ይሆን? የማሳየው ፈገግታ ከውስጤ ነው ወይስ የይስሙላ ነው? ወዘተ. . .

ከራስ ጋር የአስተሳሰብና የድርጊት አፈፃፀም ግምገማ በየቀኑ ሊደረግ ይገባል። ጠዋት ስንነሳ ያለንን አስተሳሰብ በሱ ውለን ማታ ከዛው አስተሳሰብ ጋር መገኝት አለመገኝታችንን መገምገም ይገባል። ከራስ ጋር የሚደረግ ስብስባ ደግሞ ማንም የሚያየው የለምና ነጩን ነጭ ጥቁሩን ጥቁር ማለት አለበት። ይህም የህይወትናና አእምሮን እረፍትና ቅለት ይሰጠዋል ።


@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
15.3K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 19:04:42 የጎረቤት ሳር ሁሌ የበለጠ ለምልሞ ይታያል”

 ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ድንጋይ ቀጥቃጭ ይኖር ነበር። በህይወቱ እምብዛም ደስተኛ አልነበረም።

አንድ ቀን በአንድ ሃብታም ቤት በኩል ሲያልፍ የግቢዉ በር ወለል ብሎ ተከፍቶ ስለነበር ወደውስጥ ሲመለከት የግቢዉን ማማር፣ እንዲሁም የባለቤቶቹን ግርማ ሞገስ አይቶ “የዚህ ቤት ባለቤት እንዴት የታደለ ነዉ! መቼ ይሆን እኔስ እንደዚህ የምሆነዉ?” አለ።
ገና ያን ከማለቱ የልቡ ምኞት ሞላለትና ሃብታሙን ሰውዬ ሆነ። ከሩቅ ሆኖ በቅናትና ስስት ሲያየው የነበረዉ ሃብትና ንብረት የሱ ሆኖ እሱም በተራዉ ሌሎች ይቀኑበት ጀመር። ይህ ከሆነ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንድ ትልቅ ባለስልጣን በሱ ቤት በኩል በደማቅ አጀብ ያልፍ ነበር። የአካባቢዉ ሰዉ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከወገቡ ጎንበስ እያለ አክብሮቱን ይገልጽለትም ነበር።

“እንዴት ሃይለኛ ባለስልጣን ቢሆን ነው? አይ እሱን ቢያረገኝ!” አለ ድንጋይ ቀጥቃጩ።
አሁንም እንደቅድሙ ከመቅጽበት ባለስልጣኑን ሆነ። ቅድም አይቶ የተደነቀበት አጀብና ክብርም የሱ ሆነ። ሰዎች ትከሻ ላይ ሆኖ የሰዉን አክብሮትና ትኩረት እየተዟዟረ ያጣጥም ጀመር። በመሃል በጣም ሙቅት አስቸገረዉና ቀና ብሎ ወደ ጸሃይ ተመለከተ። ከሰማይ ሆና በኩራት ብርሃኗን ስትረጭ አይቶ “ይቺ ጸሃይ እንዴት ሃይለኛ ናት? ጸሃይ መሆን ተመኘሁ!” አለ።

ጸሃይ ሆነና በስፋት ብርሃኑን እየረጨ፣ ሜዳዉን በሙቀት እያነደደ እያለ ትልቅ ዳመና መጣና ከለለዉ። ምኞት አያልቅምና “አረ አሁንስ ዳመና በሆንኩ!” አለ።

ዳመና ሆኖ ዝናብ እያዘነበ ምድርን ውሃ ሲያጠጣ ትንሽ እንደቆየ የሆነ ነገር ሲገፋዉ ተሰማዉ። ምን እንደሆነ ዞር ብሎ ሲመለከት ንፋስ እንደሆነ አየ። “ዋው! እንዴት ጠንካራ ነዉ ይሄ ንፋስ ‘ባካችሁ? አይ ንፋስ ቢያረገኝ?” ብሎ ተመኘ።

ንፋስ ሆኖ ከቤት ላይ ጣራዎችን ሲነቅል፣ ዛፎችን ከስራቸዉ መንግሎ ሲጥል ትንሽ ቆይቶ አንድ ከቶም ሊገፋዉ ያልቻለ ነገር ገጠመዉ። ቢል፣ ቢሞክር እምቢ አለዉ። እንዲህ ያስቸገረዉ ነገር እጅግ ትልቅ የሆነ አለት ነበር። “ይሄ አለት እንዴት ሃይለኛ ነዉ?” ብሎ ተደነቀ። “አይ አለት ቢያረገኝ!” ብሎ ተመኘ።

ወዲያዉም ትልቁን አለት ሆነ። እንደዚያ እንዳለ ድንጋይ ሲቀጠቀጥ የሚሰማ ድምጽ ተሰማዉ፤ ራሱም እየተለወጠ ሲመጣ ታወቀው።
“እንዴ – ከዚህ አለት የበለጠ ምን ጠንካራ ነገር አለ?” ብሎ ዝቅ ብሎ ሲመለከት አንድ ድንጋይ ቀጥቃጭ አየ።


የሰዉ ልጅ ምኞት መቼም አያልቅም! ለዉጥን መሻት፣ የተሻለን ነገር መፈለግ በራሱ ምንም ችግር የለዉም። ሆኖም እነዚህን ልብ ልንል ይገባል፡

“የጎረቤት ሳር ሁሌ የበለጠ ለምልሞ ይታያል” የሚል አባባል አለ። ከያዝነዉ ይልቅ ይልደረስንበት የበለጠ ይስበናል። አሁን ያለንበት ቦታ ያለዉን በጎ ነገር ችላ እንዳንል ግን መጠንቀቅ አለብን። እነዚያን መልካም ነገሮች በተገቢዉ መጠን ማጣጣም ይገባናል።

አለበለዚያ “ደስታን የምናገኘዉ” የሩቅ ህልሜ ሲሳካ ብቻ ነዉ ካልን ከላይ እንዳየነዉ የሆነ ደረጃ ስንደርስ ሌላ መሻት ይመጣና ሁሌም የሌለንን ለማግኘት ስንባዝን ህይወታችን መቼም የማይሞላ ማሰሮ ይሆናል። ሌላ አባባል እንጨምር “ደስታ ማለት የሌለንን ማግኘት ሳይሆን የያዝነዉ/ያለንን በደንብ መዉደድ ነዉ”

ከላይ የቀረበዉ ታሪክ እንዲየው ለማሳያ እንጂ በህይወታችን እዉነተኛ ለዉጥ ለማምጣት ከምኞት ባለፈ ጠንካራ ስራ፣ ትእግስትና በራስ መተማመን ያስፈልጋል። ያዝ ለቀቅ ሳይሆን የምንፈልገዉን በግልጽ አስቀምጠን ቀን ከሌት መትጋት ይኖርብናል።

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
5.0K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 20:36:17 ብስጭትን ማረቅ

በልጃቸው ብስጩነት አሳብ የገባቸው አባት ኮረጆ ሙሉ ምስማር ለልጃቸው እያስያዙት በተናደድክ ቁጥርና ብስጩነት ሲሰማህ ከዚህ ኮረጆ ውስጥ አንድ ምስማር በማውጣት ከአጥሩ እየወሰድክ ምታው ሲሉ አዘዙት፡፡

በመጀመሪያው ቀን ልጁ ብስጭቱን ለማረቅ ባደረገው ሙከራ ሰላሳ ሰባት ምስማሮችን አጥሩ ላይ አሳረፈ፡፡

ብስጭቱን ለመቆጣጠር አባቱ በሰጡት ምክር መሰረት ለቀጣዮቹ ሳምንታት ይኸንን ድርጊት በመደጋገም ለመቆጣጠር ሙከራ አደረገ፡፡

በየቀኑ አጥሩ ላይ የሚመታቸው የምስማር ቁጥርም እየቀነሰ መጣ፡፡

በዚህም የተረዳው ነገር ቢኖር ምስማሮቹን ከአጥሩ ላይ ከመምታት ይልቅ ብስጭቱን መቆጣጠር የቀለለው መሆኑን ነበር፡፡

በጨረሻም ልጁ ሳይበሳጭ የሚውልበት ቀን መፈጠሩን ለአባቱ በነገራቸው ጊዜ አባት ተከታዩን ሥራ እንዲሰራ መከሩት፡፡

ምንም አይነት ብስጭት ሳይሰማው በዋለ ቀን አንድ ምስማር ከአጥሩ ላይ እንዲነቅል፡፡

ይኸንንም ሲያድርገ ሰንብቶ ሁሉንም ምስማሮች ነቅሎ እንደ ጨረሰ ላባቱ አሳወቀ፡፡

አባትም የልጃቸውን እጅ ይዘው ወደ አጥሩ እየሳቡት “ልጄ! አሁን ያደረከው ጥሩ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ተመልከት አጥሩ ላይ ያሳረፍከውን ቀዳዳዎች፡፡

አጥሩ ከዚህ በፊት እንደነበረው መሆን አይችልም፡፡

ነገሮችን በብስጭት ሁነህ በተናገርክ ጊዜ ሊሽር የማይችል፤ ሊቀበሉት የሚቀፍ ምልክት እያኖርክ መሆንክን አትዘንጋ፡፡

በቀጠይ ጊዜ በተናገርከው ከመጸጸትህ በፊት ብስጭትህን ለመቆጣጠር እንደምትችል እርግጠኛ ሁን፡፡

በባልጆሮችህ ላይ ጉዳት ብታደርስ ባቀረብክላቸው ተደጋጋሚ ይቅርታ ልባቸው ቢሽርም አካላዊ ምልክቱ ግን ሊወገድ አይችልም፡፡

ስለዚህ ከባልጀሮችህ ጋር ያለህን ግንኙነት በሰከነ ስሜት ተቀበለው፡፡

የበጎነት ውሃም አጠጣው አብሮነታችሁ ሲለመልም ታየዋለህ ሲሉ አባት ምክራቸውን ለገሱት፡፡

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
3.2K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 20:25:07 ማይክል ጃክሰን ለ150 አመት ያህል መኖር ይፈልግ ነበር ፡፡

በዚህም ምክንያት 12 ሀኪሞችን በቤቱ በየቀኑ ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ይመረምሩት ነበር ፡፡ የሚመገበዉም ምግብ ከመመገቡ በፊት በላብራቶሪ ገብቶ ይመረመር ነበር ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 15 ሰዋች ደግሞ መስራት ስላለበት የሰውነት እንቅስቃሴ ይቆጣጠሩ ነበር ፡፡ የሚተኛበትም አልጋ ትልቅ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመኝታ ቤቱን ኦክስጂን መጠኑን ያስተካክል ነበር ፡፡ በውጭም እንዳጋጣሚ ከሰውነት አንዱ ከተጎዳበት የሰውነት አካል የሚሰጡ ሰዋች ዘወትር በተጠንቀቅ ነበሩ ፡፡

ይህ ሁላ ሲሆን ማይክል ጃክሰን 150 አመት የመኖር ህልም ነበረዉ ፡፡  ነገር ግን ሊሳካለት አልቻለም ፡፡ ሁሉም በነበር አለፈ ፡፡

በሰኔ 25 ፣ 2009 G.C በ 50 አመቱ ልቡ መስራት አቆመ ፡፡ የነዛ 12 ሀኪሞች ርብርብ ምንም ሊሰራ አልቻለም ፡፡ ከዚህ በላይ የ ሉሳንጀለስና የካሊፎርኒያ ሀኪሞች ጥምረት ያመጣው ለውጥ አልነበረም ፡፡ የእድሜዉን አጋማሽ በሀኪሞች ክትትል የሚጓዘዉ 150 አመት የመኖር ህልሙን ሊያሳካ አልቻለም ፡፡

የማይክልን የመጨረሻ የምር ቆይታ በአለም 2.5 ሚሊዮን ህዝብ በቀጥታ ተከታትሎታል በታሪክም በብዙ ሰዉ የታየ የቀጥታ ስርጭት ሁኗል ፡፡ በሞተበትም ቀን የአለማችን ትልልቅ Internet መፈለጊያዎች እነ Wikipedia , Twitter , AOL'S ተጨናንቀዉ መስራት አቁመዉ ነበር ፡፡

ማይክል ሞትን መፈተን አስቦ ነበር ሞት ግን ቀድሞ ፈተነዉ ፡፡ በዚህ ቁሳዊ አለም ምንም የማይዘዉ ሞት የሚፈትኑትን አብዝቶ ይፈትናል ፡፡ 


አሁን ይህን ልብ ብለን እናስብ !

❖ለምን ቁሳዊ ህይወትን አብልጠን እንወዳለን?
❖በዚህ አለም ትልቅ የምንሮጥለት ነገር ምንድን ነዉ?
❖ለምን በመንጋ አስበን በመንጋ ኑረን በመንጋ እንሞታለን ?
❖ሕይወታችን የሚነዳዉ ሀሳባችንን በመለወጥ ነዉ ወይስ ልብስና መልካችንን በመለወጥ ?

በሕይወት ትልቁ ነገር ደስታ ፣ ሰላም እና ባለን ነገር እርካታ ነዉ ፡፡ ስለዚህ ገንዘብ ማካበት ደስታ አያመጣም ባለን ነገር መርካት ግን ደስታን ያመጣል ፡፡ ሰላም በወሬና በምኞት አይመጣም ነገር ግን ባለን ነገር ተረጋግተን ማሰብ ስንጀምር ይመጣል፡፡ ሞት አይቀርምና ባለን እድሜ ጥሩ ነገር ሰርተን እንለፍ ።

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
2.9K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 20:21:44 ችግር ብቻ

አንድ ቀን በመንገድ ላይ እየሄድኩ ጓደኛዬ ጆርጅ በመንገዱ እየመጣ አየሁት። ፊቱ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ያሳብቃል፡፡ ጆርጅ እጅግ በመከፋት ውስጥ ነበር፡፡ እንደተለመደው “እንዴት ነህ ጆርጅ?” ብዬ
ጠየቅኩት:: የጠየቅኩት የተለመደ የሰላምታ ልውውጥ ቢሆንም ጆርጅ ግን ጥያቄውን በቁምነገር ወስዶት ለ15 ደቂቃ ያህል እንዴት መጥፎ ስሜት ውስጥ እንደሆነ ነገረኝ:: ብዙ በተነጋገርን ቁጥር፣ መጥፎ ስሜቱ እየተጋባብኝ መጣ፡፡

በመጨረሻ “ይኸውልህ ጆርጅ በእንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆንህ አዝናለሁ:: እንዴት እዚህ ውስጥ ገባህ?” ስል ጠየቅኩት::
ድንገት ተበሳጨ፡፡

“ችግሮቼ ናቸዋ!” አለ፡፡ “ችግር ብቻ... ሌላ ነገር የለም... ችግር ብቻ:: ችግሮች ሰልችተውኛል። ችግሮቼን ልታስወግድልኝ ከቻለ ለምትመርጠው የእርዳታ ድርጅት 5,000 ዶላር እለግሳለሁ::” አለኝ

አሁን ለእንደዚህ አይነት ችሮታ ጉጉ ስለሆንኩኝ ፣ አንድ በጣም ጥሩ ነው ብዬ ያሰብኩትን ሀሳብ አመጣሁ::

ከዚያ “ትናንትና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩበት ቦታ ሄጄ ነበር:: እንዳረጋገጥኩት አንዳቸውም እንኳ ምንም አይነት ችግር የለባቸውም እዚያ መሄድ ትፈልጋለህ?” አልኩት። “መቼ መሄድ እንችላለን? የምፈልገው ቦታ ያንን ይመስለኛል::” ሲል ጆርጅ መለሰ።

ከዛም በሚቀጥለው ቀን ወደ አንድ የመቃብር ስፍራ ወሰድኩት ከዛም "ምንም አይነት ችግር የሌለባቸው የማውቃቸው ብቸኛ ሰዎች እነዚህ ናቸው" አልኩት።

                   ኬን ብላንቻርድ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
3.1K viewsedited  17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 07:52:09 ጊዜ ያላችሁ አይምሰላችሁ!!!

አንድ እድሜውን ሁሉ ሰዎችን በሕይወት ክህሎት ዙሪያ በማስተማር ያሳለፈ የእድሜ ባለጠጋ፣ “ወጣቶች ሊሰሩት ከሚችሉት ስህተት እጅግ የከፋው የትኛው ነው?” ተብሎ ሲጠየቅ፣ ከልምዱ በመነሳት እንዲህ ሲል መለሰ ይባላል፣ “ብዙ ጊዜ እንዳላቸው ማሰብ”፡፡

ልጆች ተጫውተው ለማለፍ ያላቸው ዓመታት አስቡት! እጅግ ውስን ነው!

ወጣቶች ለትምህርትና ማሕበራዊ ግንኙነትን በማዳበር ለመብሰል ያላቸው ዓመታት አሰላስሉት! ጥቂት ናቸው!

ጎልማሶች በስራው ዓለም ባላቸው ስምሪት ለአሁኑ ቤተሰባቸው ፍላጎትና ለወደፊት የሽምግልና እድሜያቸው ለማስቀመጥ ያላቸውን የእድል መስኮት አስቡት! ብዙም አይደለም!

እነዚህ ጊዜያቸውን ጠብቀው የሚመጡ ሂደቶች በትክክለኛ የጊዜ አጠቃቀም ብልሃት ካልተያዙ በብርሃን ፍጥነት ያልፋሉ፡፡ አንዴ ካለፉ ደግሞ አይመለሱም፡፡

“የአፍሪካ ጊዜ”

እንደ አፍሪካዊ፣ ከዚያም ጠበብ ሲል እንደ ኢትዮጵያዊ፣ የጊዜ አጠቃቀም ሁኔታችን ምን ያህል የተበላሸ እንደሆነ ለማወቅ ምንም አይነት ጥናታዊ አቅርቦቶችን ለማግኘት መጣጣር የለብንም የራሳችንንና በአካባቢአችን ያለውን የጊዜ አጠቃቀም ሁኔታና ዝንባሌ ማጤኑ ከበቂ በላይ ነው፡፡ ለአንድ ስብሰባ ስንጠራ በሰዓቱ ብንደርስ የሚገጥመንን ቁጭ ብሎ ያልመጡትን የመጠበቅ ሁኔታ ወይም ደግሞ በሰዓቱ መድረስ የሚሰጠንን “የመዋረድና የመናቅ” መንፈስ ስለምንፈራው ዘግይቶ መድረስ እንመርጣለን፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የማይቋረጥን ዑደት ፈጥሮብናል፡፡ የሰርጎቻችንን ሁኔታ እናስባቸው፡፡አንድ ሰው የሰርግ ጥሪውን አክብሮ በሰዓቱ ቢገኝ ከአንድና ከሁለት ሰዓታት በላይ ቁጭ ብሎ ሰርጉ እስኪጀመር መጠበቅ የተለመደ ነው፡፡

አንድ የጋና ተወላጅ እንዲህ ሲል ተናግሯል፣ “ክፍለ ዓለማችን ሳታድግ የመቀጠሏ ዋነኛ ምክንያት በጊዜ ላይ ያለን ግድ የለሽ ዝንባሌና ማሻሻል ያለብን የጊዜ አባካኝነት ዝንባሌ ነው፡፡ ሰዓትን ያለማክበር ችግራችን ከልክ ያለፈ ከመሆኑ የተነሳ ቀጠሮን አለማክበርና በሰዓት አለመገኘት የአፍሪካ ጊዜ በመባል ተቀባይነት አግኝቷል”::

እንደሚታወቀው ሁሉ ሁላችንም እንደማንኛውም በቀደሙት ዘመናት ኖረው እዳለፉ ሰዎች በቀን ውስጥ 24 ሰዓታት አሉን፡፡ ነገር ግን በዚህ በምንኖርበት ክፍለ- ዘመን ያለው የኑሮ ጫናና ሩጫ እነዚህን ቢሰራባቸውም ሆነ ባይሰራባቸው ከማለፍ ፍንክች የማይሉ ሰዓታት አጭር ያደርጋቸዋል፡፡ የየቀኑ ሩጫና መጨናነቅ ቀኑ እንደ አንድ ደቂቃ ታጥፎ የሄደ እስኪመስል ድረስ ያዋክበናል፡፡ ያለን ምርጫ አንድ ነው፣ ሰዓትን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር!

ይህንን አስበህ ታውቃለህ? ሰዓትህን በአግባብ በመጠቀም ሁኔታዎችን ካልመራሃቸው ሁኔታዎች ራሳቸው አንተን ይመሩሃል፡፡ በሰዎችም በቀላሉ የምትመራና የምትነዳ ሰው ትሆናለህ፡፡ ውጤቱም የምርታማነትና የስኬታማነት መቀነስ ነው፡፡

ጊዜህን በአግባብ የመጠቀም ብቃት እንደጎደለህ ለማወቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እራስህን መጠየቅ ትችላለህ፡-
•  አንድን የጊዜ ገደብ ያለውን ስራ ለመጨረስ ዘወትር በመጨረሻው ሰዓት የመሯሯጥ ባህሪ አለህ?
•  አብዛኛውን ጊዜ ለቀጠሮም ሆነ ለሌላ የጊዜ ገደብ የመዘግየት ዝንባሌ አለህ?
•  በተመሳሳይ ጊዜ ከአንድ በላይ ቀጠሮ ወይም ፕሮግራም በመያዝ ግራ የመጋባት ባህሪይ ያጠቃሃል?

ለእነዚህና ለመሰል ጥያቄዎች ያሏችሁ መልሶች “አዎን” ከሆነ፣ ስለጊዜ አጠቃቀማችሁ በሚገባ አስቡበት

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
548 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 19:58:37 ሕይወት እና መጥረቢያ!

ሁለት እንጨት ፈላጮች ሥራ ይቀጠራሉ…
ሥራው የግንድ ቁራጮችን መፍለጥ ነው፡፡ ሥራቸውን
የሚጀምሩት እኩል ሰዓት ነው፤ የሚያርፉትም እንዲሁ፡፡ ነገር ግን… አንደኛው ፈላጭ ከሌላኛው በተሻለ ብዙ ግንዶችን
በመፍለጥ፣ ፍላጮቹን ከምሮ ሌላኛውን ያሳጣዋል(ሳ- ጠበቅ)።

ሁለት፣ ሶስት ቀናት… ተቆጠረ… ይሄ ትንሽ ግንዶችን ብቻ
የሚፈልጠው ፈላጭ በባልደረባው በጣም በመቅናቱ የተነሳ ከሱ
እኩል ብዙ ፍልጦችን ለመከመር ባለ በሌለ አቅሙ በፍጥነት
ቢፈልጥም በመጨረሻ እጁ ይዝልና ቀኑ ሲገባደድና ክምራቸው
ሲታይ አሁንም እንደተሸነፈ ነው፡፡
ታዲያ… በባልደረባው የቀናው ይሄ ፈላጭ ለዕረፍት ሲቀመጡ፣
እንዲህ ሲል ጠየቀው…
"መጥረቢያችን አንድ አይነት ነው፣ የሚሰጠን የግንድ አይነት አንድ ነው፣ የምንጀምረው፣ የምናርፈው እኩል ነው… እንዴት
ነው ያንተ ፍላጮች ሊበዙ የቻሉት?"
ሌላኛው ፈላጭ እንዲህ ሲል መለሰለት…
"ትክክል ነህ ወዳጄ! ሁሉ ነገር ላይ እኩል ነን! ነገር ግን የምንበላለጠው ስናርፍ ብቻ ነው!

አንተ በዕረፍት ሰዓታችን መጥረቢያህን ወርውረህ ቁጭ ትላለህ፤ እኔ ግን የእረፍት
ሰዓቴን መጥረቢያዬን በመሳል/በመሞረድ ነው የማሳልፈው! ልዩነታችንን የፈጠረውም እሱ ነው፡፡"

እስኪ ምሳሌዋን እናስፋት…
አየህ! የሁላችንም ልዩነት የሚፈጠረው እዚህ ጋር ነው!
በእረፍት ሰዓትህ ምንድን ነው የምታደርገው?
መጥረቢያህን ትሞርዳለህ ወይስ ዝም ብለህ ነፍዘህ ትቀመጣለህ?
በስራህ ወይም በሞያህ መንገድ እራስህን ትሞርዳለህ ወይስ
በማይረባ ነገር በመሞዳሞድ ጊዜህን ታባክናለህ?
በዶለዶመ እውቀትና ልምድ ህይወትህን ትገዘግዛለህ ወይስ በሰላ መጥረቢያ ክርትፍትህ እያደረግህ መንገድህን ታቀናለህ?

እንጃ!
እኔ ግን ሁሌ እንደምልህ ልበልህ…
በየትኛውም መስክ ብትሆን ሥራህ የተቃና እንዲሁን ሁሌም መጥረቢያህን ሳል።

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
2.8K viewsedited  16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 18:59:47 ገሎች

ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ፣ ማን ነው ብሎ ያለ?
ታዲያ አሁን ታዲያ አሁን፣ ምን ነክቶት ዝም አለ?
ምንቼቶችም አልቀው፣ ገሎች ቀርተው ሳለ!!


ዛፍነት

መሆን ከተመኘህ፣ ዛፍነትን ምረጥ፡
ቆርጠውህ ሲሄዱ፣ ሺ ሆነህ አቆጥቁጥ!


ማህበረ አማሳይ

ይህን ወጥ እንግዲህ፣ ሁሉም ካማሰለው ፣
እጅ እጅ ማለት እንጂ፣ መጣፈጫም የለው።



አራሚ

ነቃይና አራሚ፣ ድሮም ዛሬም አሉ፡
ከሐበሻ ምድር መቼ ይጠፋሉ።
አሉ! አሉ! አሉ!
ጥንትም ዛሬም አሉ።
ባረም አመኻኝተው ሰብል የሚነቅሉ።


ወዴት ነህ

ወዴት ነህ ይለኛል
ሊያሳፍረኝ ታክሲ
ሊጭነኝ ወያላ፤
እኔና ሀገሬ እንሄድበት መንገድ
ግብ እንዳለን ሁላ፡፡

ይስማዕከ ወርቁ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
2.9K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 12:58:50 የሜቭላና ሰባቱ ጥበቦች

(በሚስጥረ አደራው)

In generosity and helping others, be like a river
In compassion and grace, be like the sun
In concealing other’s faults, be like the night
In anger and fury, be as if you have died
In modesty and humility, be like the earth
In tolerance, be like the sea
And either appear as you are, or be as you appear”

እንሂን ሰባት የሜቭላና ጥበቦችን እኔ እንደሚከተለው ተረድቻቸዋለው። ዘርዘር አድርጌ ከሌሎችም ነገሮች ጋር እያጣቀስኩኝ አቅርቤያቸዋለው፦

ለሰዎች ደግ ስትሆን እንደወንዝ ሁን– ወንዝ ሰው መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ምናልባትም ደግነታችሁ እንደወንዝ ይሁን ያለው፤ ሳትመርጡ፣ ለለመናችሁ እጃችሁን ዘርጉ ለማለት ይመስለኛል። ሌላው ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ወደኋላ የማይመለስ ሲሆን ቀጣይነቱን ይመሰክራል፤ የኛም ደግነት እንዲህ እንዲሆን ሲመኝልን ይሆን? ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማያበቃ፤ እንደወንዝ የሚፈስ መልካምነት ድንቅ ነው። ሌላው የወንዝ ውበቱ ዝቅ ብሎ ሳይጮህ መፍሰሱ ነው። ዝቅ ብሎ ሌሎችን ከፍ እንደማድረግ ምን ውብ ነገር አለ? ይህንን አደረግኩኝ፤ እንዲህ ደግ ሰራው እያሉ መጮህ የደግነትን ክብር ይነካል፤ እንደወንዝ በዝምታ፤ ለሌሎች መልካም መሆን ነው እውነተኛው ደግነት።

ስትራሩ እና ለሰው ስታዝን እንደጸሃይ ሁን– እዚህ ላይ ሌላኛው የፐርሺያ ገጣሚ ያለው ትውስ አለኝ። “ከዚህን ያህል ጊዜ በኋላም እንኳን ጸሀይ ለምድር ውለታ አለብሽ አላለቻትም፤ ከውለታ የጸዳ ፍቅር እንደጸሃይ ያበራል” ሲል ገጥሟል። ለዚህም ነው ስታዝኑ እና ለሰው ስታስቡ እንደጸሀይ ሁኑ ያለው። ውለታ እንደዋልን ሳይሰማን የምንሰጠው ደግነት ጸዳል ያለው ስለሆነ። ጸሀይ ለምድር ብርሃን እንደሆነች ሁሉ፤ ከውለታ የጸዳው ምግባራችን ለኑሮዋችን ብርሃን ነው።

የሰውን ጥፋት ስትሸፍን እንደ ምሽት ሁን– ሰው በምሽት ብዙ ነገሮች የሚያደርገው የሌላውን ሰው አይን ሸሽት ነው። ጨለማ ጉድ ደባቂ ነው። ብዙ ሰዎች ከስህተቶቻቸው በላይ ይቀጣሉ ብዬ አምናለው (በግሌ)። አንዷ ስህተታቸው በአደባባይ እየበዛችባቸው፤ ብዙዎችን ከትናንት ስህተታቸው ጋር ተጣብቀው እንዲቆዩ አድርገናቸዋል። እንደጨለማ የሰው ስህተትን እንሸፍን ሲባል፤ መወቀስ ያለበት አይወቀስም፤ ስህተት የሰራ ሁሉ እየተሸፋፈነለት ይኑር ማለት አይመስለኝም። ይልቁንም የሌሎችን ስህተት ለኛ መመጻደቂያ አናድርገው ለማለት ነው። እንደሰው ሁላችንም ስህትትን እንሰራል፤ ነገር ግን ትናንት በሰራነው ስህተት ዛሬንም ነገንም ማጣት የለብንም። ለሌሎችም እንዲሁ፤ ለንጋታቸው እድል እንስጣቸው (ሁለተኛ እድል)።

በንዴትህ ወቅት እንደ ሞተ ሁን- ሞት የእንቅልፍ ታላቅ ወንድም ነው ይሉታል። ከጸጥታ ሁሉ በላይ የከበደ ጸጥታ ሞት ነው። በንዴት ውስጥ እንደሞተ ሰው ጸጥ ማለት፤ ከጥበቦች ሁሉ በላይ የገዘፈ ጥበብ ይመስለኛል። እንደሞት ሁሉን የሚያሳልፍ ትዕግስት ይኑራችሁ ሲለን ነው።”ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ነገር አትስራ” ይላሉ። ንዴታችንን ለቅጸበት በጸጥታ ብናሳልፈው፤ ምን ያህል ከጸጸት እራሳችንን እናድን ነበር።

ሌላውን ስታከብርና እራስህን ዝቅ ስታደርድ እንደ ምድር ሁን– “ይህ ሰው መሬት ነው ጸባዩ” ሲሉ እሰማ ነበር። መሬት ሁሉን ቻይ ናት፤ ለሁሉም እድል የምትሰጥ ዝቅ ብላ ሌሎችን በላይዋ የምታኖር ናት። ሰው እንደምድር ይሁን ሲባል፤ ሁሉም እየተነሳ ይርገጠው ማለት ሳይሆን፤ የሰውን እኩልነት አምኖ፤ በፍቅር ይኑር ለማለት እንጂ። ሌላው ማንሳት ያለብን የምድር ጸጋ ሀብቷ ነው።ምድር ሀብታም ባለጸጋ ናት፤ ለሰው የማትነፍገው ብዙ ሀብት አላት። ሰውም እንደምድር የብዙ ጸጋዎች ባለቤት ነው። መልካም ነገር ዘርተውበት ክፉ ፍሬ የሚያበቅል መሬት የለም። ሰውም በላዩ መልካም ምግባሮችን ሲዘራ፤ መልካም የህይወትን ፍሬ ሊለቅም የተፈጥሮ ህግ ይፈቅድለታል።

የመቻቻል አመልህ እንደ ውቂያኖስ ይሁን– ሰፊ የመቻል ልብን ሲያመላከተን ነው እንግዲህ። በተለይ ለዚህ ለእኛ ዘመን ሰዎች እንደውቂያኖስ ከሰፋ መቻቻል በላይ ምን የሚያስፈልገን ነገር አለ? መቻቻል ከንትሹ ቤተሰብ፤ ጀምሮ እስከትልቂቱ አለም ደረስ እየጠበበ የመጣ፤ ከውቂያኖስነት አልፎ ልትደርቅ እንደተቃረበች የውሃ ሽንቁር መስሏልና።


ሌላው የመጨረሻው የገጣሚው እረድፍ እንዲህ ይላል “ወይ የሆንከውን ምሰል፤ አልያም የመሰልከውን ሁን”። አብዛኛውን ጊዜ የምንናገረውን አይደለንምና። የምንመስለው እና እውነተኛው ማንነታችን ክፍተት አለበት። ይህ ክፍተት የሌለበት አንድም ባይኖርም፤ እራስን እየፈተሹ መጓዙ ግን ክፍተቱን እያጠበበው ይሄዳል። ሰው ለፍጹምነት መጓዝ የለበትም፤ ፍጹም ንጹህ መሆን ለሰው የተሰጠ አይደለምና፤ በቆሸሹ ቁጥር መንጻት ግን ባህሪያችን ሊሆን ይገባዋል። የሆንነውን ለመምሰል፤ አልያም የመሰልነውን ለመሆን ሁሌም ወደውስጣችን ልናይ ይገባናል።

እንግዲህ ከወንዝ፤ ከጸሀይ፤ ከምሽት፤ ከምድር፤ ከውቂያኖስ፤ እንዲሁም ከሞት የተቀመመን ባህሪ አስቡት፤ እኔ እንደሚመስለኝ፤ የኑሮዋችን መምህራን፤ ከመጽሀፍት እና ከተለምደው እውቀት በላይ ተፈጥሮ እና አካባቢያችን ይመስሉኛል። ይህንን ለማይት ግን ሶስተኛ አይንና ስድስተኛ የስሜት ህዋስን ይጠይቃል።
       

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
470 views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 19:32:28 የጠቢቡ ሰሎሞን ፍርድ

ሦስት ነጋዴዎች ድንገት አንድ ቀን በንጉሥ ሰሎሞን የዘውድ ችሎት ተገኙ፡፡ ሦስቱም ለብዙ ዘመን አብረው ለመነገድ ተማምለው፣ ግመል ጭነው፣ ገንዘብ ቋጥረው፣ ስንቅ አንጠልጥለው፣ ሀገር ጥለው የሄዱ ናቸው፡፡
‹ንጉሥ ሆይ› አለ አንዱ በዙፋኑ ፊት እጅ ነሥቶ፡፡ ‹እኛ አብረን ለመነገድ ተስማምተን መንገድ የጀመርን ጓደኛሞች ነን› አለ፡፡
ሁለተኛውም ነጋዴ ተቀብሎ ‹ቃላችንንም አክብረን ለንግድ ሩቅ ሀገር ስንጓዝ ድንገት የሰንበት በዓል ደረሰብን› ሲል ቀጠለ፡፡
ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ሰንበትን አክብረን ለመዋል ስለፈለግንም ድንኳን ከተከልንበት ቦታ ራቅ አድርገን ጉድጓድ ቆፍረን ገንዘባችንን በከረጢት ቀበርነው፡፡ ከመካከላችን ማናችንም ገንዘቡን ተደብቀን ላንወስድ መሐላ ፈጽመን ነበር፡፡ በማግሥቱ ግን ወደ ጉደጓዱ ሄደን ስንቆፍረው ገንዘባችንን አጣነው› አለና አስረዳ፡፡ የመጀመሪያው ነጋዴም አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ‹ንጉሥ ሆይ ጉድጓዱን ስንቆፍርም ሆነ ገንዘቡን ስንደብቅ ሌላ ሰው ያየን የለም፡፡ ከሰረቅነው እኛው ነን፡፡ ነገር ግን ማናችን እንደሰረቅን ልንተማመን አልቻልንም› አለ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን በልቡ ‹መስረቅ የቻለ ሰው መዋሸትና መሐላን ማፍረስ አያቅተውም› ብሎ አሰበና ነገሩን ቀለል አድርጎ ‹ነገ ተመልሳችሁ ስትመጡ ማን እንደሰቀረው እነግራችኋለሁ› ሲል አሰናበታቸው፡፡
በማግሥቱ ሦስቱ ጓደኛሞች መጡ፡፡ ችሎቱም ተጀመረ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን ‹የእናንተን ጉዳይ ከመመልከቴ በፊት ሦስታችሁም ጠቢባን መሆናችሁን ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ በመሆኑም በሚከተለው ታሪክ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡ እፈልጋለሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብረው እየተማሩና እየተጫወቱ አደጉ፡፡ ወደፊት ትልቅ ሰው ሲሆኑ ተጋብተው አብረው ለመኖር ቃል ተግባቡ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የኑሮ መሥመር አለያያቸውና በተለያዩ ቦታዎች መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ በዚህ መካከልም ሴቷ ቃል ኪዳንዋን ረሳችውና ሌላ ባል አገባች፡፡ ጋብቻው በተፈጸመበት ቀን ማታ የገባቺው ቃል ኪዳን ትዝ አላት፡፡ ደነገጠች፡፡ ነገሩን ለባልዋ ነገረቺው፡፡ ባልዋም ለቃል ኪዳን ትልቅ ቦታ የነበረው ሰው ነበርና ‹በይ ተነሺ ቃል የገባሺለትን ሰው እንፈልገው፤ ስናገኘውም ቃል ኪዳኑን ማፍረሳችንን ነግረነው፣ የገንዘብ ካሣም ከፍለነው ይቅርታ ያድርግልን፡፡ ያለበለዚያ ትዳራችን ይበላሻል› አላት፡፡
ሁለቱ አዲስ ተጋቢዎች ልጁ ይገኝበታል ወደሚባለው ቦታ ሩቅ መንገድ ተጉዘው አገኙት፡፡ የሆኑትንም ነገር ሁሉ ገለጡለት፡፡ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው፣ ገንዘቡን እንዲቀበላቸው ለመኑት፡፡ ልጁ ቀና ሰው ስለነበር ይቅርታ አደረገላቸው፡፡ ‹ያልሠራሁበትን ገንዘብ አልቀበልም› ብሎ ገንዘቡን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ እነርሱም አመስግነውት ተመለሱ፡፡ ሲመለሱ በመንገድ ላይ አንድ ዘራፊ አጋጠማቸውና የያዙትን ገንዘብ ነጠቃቸው፡፡ ልጂቱም ገንዘቡ በምን ምክንያት እንደተያዘ ታሪኩን እያለቀሰች ለዘራፊው ነገረቺውና እንዲመልስላቸው ለመነቺው፡፡ ዘራፊውም በታሪኩ ተደንቆ የወሰደውን ገንዘብ መለሰላቸው፡፡
ንጉሥ ሰሎሞን ይህን ታሪክ ከተረከ በኋላ ‹ከባልየው፣ ከሚስቱ፣ ከቀድሞ ወዳጇና ከዘራፊው የትኛው ሰው የበለጠ ምስጋና ይገባዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?› ሲል ጠየቃቸው፡፡
የመጀመሪያው ነጋዴም ‹ለእኔ የበለጠ ምስጋና የሚገባት ሴቲቱ ናት፡፡ ቃል ኪዳንዋን አስታውሳ ይቅርታ ለመጠየቅ መነሣቷ ያስመሰግናታል› ሲል ሐሳቡን ሰጠ፡፡
ሁለተኛው ነጋዴም ‹ለእኔ ግን የበለጠ ምስጋና የሚገባው ባልዋ ነው፡፡ ምክንያቱም ሚስቱ ቃል ኪዳንዋን ማፍረሷን ስትነግረው ቃልዋን ተቀብሎ፣ ቤት ንብረቱን ትቶ፣ ገንዘቡን ይዞ ወደ እጮኛዋ ዘንድ መሄዱና ይቅርታ መጠየቁ ያስመሰግነዋል› ሲል አስተያየቱን ሰጠ፡፡
ሦስተኛውም ነጋዴ ‹ባልና ሚስቱ ያደረጉት ነገር የሚገርምና የሚያስመሰግን ነው፤ ነገር ግን የቀድሞ እጮኛዋ ሞኝ ሰው ነው፤ ገንዘቡን መቀበል ነበረበት› ሲል ሐሳቡን ለገሰ፡፡
ንጉሥ ሰሎሞንም ሐሳባቸውን ከሰማ በኋላ ሦስተኛውን ነጋዴ ‹ገንዘቡን የሰረቅከው አንተ ነህ› አለው፡፡ ሰውዬውም ደነገጠና ወደ ንጉሡ ተመለከተ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም ‹ያልደከመበትን ገንዘብ የሚመኝ አእምሮ ባይኖርህ ኖሮ ያንን ልጅ ሞኝ አትለውም ነበር፡፡ አስተሳሰቡ ከሌለ ድርጊቱ አይመጣም፡፡ አንተ ውስጥ ተጣምሞ የበቀለ ነገር አለ፡፡ ሁለቱ ጓደኞችህ ታማኝነትን ዋጋ ሰጥተውታል፤ አንተ ግን ለታማኝነት ዋጋ አልሰጠኸውም፡፡ ስለዚህ ካንተ በቀር ይህን ሊያደርግ የሚችል ሰው የለም፡፡
የአንተን አእምሮ ሳየው የተሠራበትን ነገር አየሁት፡፡ አእምሮ ሲሰጠን ተሠርቶ አልተሰጠንም፡፡ እንዲሠራ ተሰጠን እንጂ፡፡ ሰው በርስቱ ላይ እንዴት ያለ ቤት እንደሚሠራ መወሰንና ቤቱን መገንባት የእርሱ ድርሻ ነው፡፡ የሚጠቀመው ዕቃ የሚገነባበትም መንገድ የቤቱን ጥንካሬ ይወስነዋል፡፡ አእምሮም እንዲሁ ነው፡፡ በሕግ፣ በምግባር፣ በትምህርት፣ በጥበብ፣ የተገነባ አእምሮ ያንተን ዓይነት አስተሳሰብ አይኖረውም፡፡ አሁን የሰጠኽው ሐሳብ ያሳለፍከውን ሕይወት፣ የተዘራብህን ዘርና የተሠራህበትን ነገር አሳይቶኛል፡፡ ወላጆችህን አየኋቸው፤ ጓደኞችህን አየኋቸው፣ መምህሮችህን አየኋቸው፡፡ እነዚህ ሁሉም ወይም ከእነዚህ አንዱ የዘራብህ ዘር ትክክል አይደለም፡፡ ምናልባትም ይህ ዘር ባንተ ላይ መዘራቱን አታውቀው ይሆናል፡፡ ግን ተዘርቶብሃል፡፡
‹አንድ ታሪክ ልንገራችሁ› አላቸው ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡ እንዲቀመጡ ተፈቀደላቸው፡፡ ሁሉም ሌባውን ያወቀበት መንገድ አስደንቋቸዋል፡፡ ምንጣፍ ላይ ቁጭ አሉ፡፡
አንድ ቀን አንድ ልጅ እኔ ዘንድ ለፍርድ ቀረበ፡፡ የመጣው አባቱን ገድሎ ነው፡፡ ታዳሚዎች ሁሉም ‹አባቱን የገደለ ፈጽሞ ይሙት ይላልና ይገደል› ብለው ወሰኑበት፡፡ እኔ ግን ይህንን ነገር ያደረገበትን ምክንያት ለመረዳት ስለፈለግኩ ጠየቅኩት፡፡ ነገሩም እንዲህ ነበር፡፡ አንድ አባት ልጁን ሁል ጊዜ አንድ ነገር ያስተምረዋል፡፡ ጓደኞቼ መቱኝ ሲለው ‹በላቸው› ይለዋል፡፡ ፍየሉ ወጋኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ ዕንቅፋት መታኝ ሲለው ‹በለው› ይለዋል፡፡ የአባቱ መፍትሔ ሁልጊዜ ‹በለው› ብቻ ነበር፡፡ ልጁ በዚህ ትምህርት ነበር ያደገው፡፡ አደገ፡፡ ጎለመሰ፡፡ ፈረጠመ፡፡ ያገኘውን ሁሉ እየደበደበ፡፡
አንድ ቀን የአባቱን በጎች ወስዶ አባቱ ሳይፈቅድለት ሸጠና መጣ፡፡ አባቱ ለምን እንደሸጠ ሲጠይቀው ‹ገንዘብ ያስፈልገኛል› አለው፡፡ አባቱ ተናደደና በበጎች መጠበቂያ ጅራፍ መታው፡፡ ያን ጊዜ ልጁ ድንጋይ አንሥቶ እንደ ቃየል አባቱን አናቱን መትቶ ገደለው፡፡ ልጁን ለምን አባቱን እንደገደለ ስጠይቀው ‹አባቴ ያስቸገረኝን ሰው ሁሉ እንድመታ አስተምሮኛል፡፡ አባቴም ስላስቸገረኝ መታሁት፡፡ ለመሆኑ ከመምታት በቀር ምን ማድረግ እችል ነበር?› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ይህ ልጅ ሌላ ነገር አልተማረምና ያደረገው የተማረውን ነው፡፡ ሰው የትምህርቱ ውጤት ነውና› አለው፡፡ ሰውዬውም በነገሩ ተገርሞ ገንዘቡን መለሰ ይለናል ሚድራሽ የተባለው የአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ፡፡
ይህንን ታሪክ ሳነብ ዛሬ በልጆቻችን ኅሊና እየገነባን ያለነው የዘረኛነትና የጠባብነት፣ የጽንፈኛነትና የአምባገነንነት ጡብ ይታወሰኛል፡፡ እያንዳንዳችን ለሌላው ብለን የምናስታጥቃቸው ነገር አፈሙዙ ወደራሳችን ሊዞረን እንደሚችል ያሰብንበት አልመሰለኝም፡፡ የተጣመመ ሐሳብ እያሰጠን፣ የተጣመመ ትውልድ አፍርተን የተስተካከለች ሀገር አንደመመኘታችን ያለ ሞኝነት ከወዴት ይገኛል?
ዳንኤል ክብረት


@Human_Intelligence
487 viewsedited  16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ