Get Mystery Box with random crypto!

ፍላጎትና ችሎታ ሲራራቁ! አንድን ነገር በተዋጣለት መልኩ ለማከናወን የሚያስፈልጉን ዋና ዋና ነገሮ | የስብዕና ልህቀት

ፍላጎትና ችሎታ ሲራራቁ!

አንድን ነገር በተዋጣለት መልኩ ለማከናወን የሚያስፈልጉን ዋና ዋና ነገሮች ችሎታና ፍላጎት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱ ሲኖርና ሌላኛው ሲጎድል ስኬት የሕልም እንጀራ ነው፡፡

1. ችሎታና አቅም ኖሮ ፍላጎትና መነሳሳት ሲጠፋ

በአንድ ነገር ላይ ምንም ያህል ችሎታና አቅም ቢኖራችሁም፣ ያንን ነገር ለማድረግ ፍላጎትና መነሳሳት ከሌላችሁ ምንም ነገር ማከናወንም ሆነ የትም ደረጃ ልትደርሱ አትችሉም፡፡

ምናልባት ችሎታውና አቅሙ እያላችሁ ለመንቀሳቀስ ፍላጎትና መነሳሳት ያጣችሁት . . .

• ከጊዜያዊ የስሜት ቀውስ የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ፣ ለስሜት ቀውስ የዳረጋችሁን ሁኔታ ፈልጋችሁ በማግኘትና በመቅረፍ ራሳችሁን ለማነሳሳት ሞክሩ፡፡

• ያላችሁ ችሎታ መስራት ከምትፈልጉት ነገር ጋር የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ፣ ለጊዜው ራሳችሁን ገፍታችሁም ቢሆን እየተንቀሳቀሳችሁ ወደፊት በፍላጎታችሁ መስክ የምትሰማሩበትን መንገድ በሂደት ማስተካከል የግድ ነው፡፡

2. ፍላጎትና መነሳሳት ኖሮ ችሎታና አቅም ሲጠፋ
ከላይ ከተጠቀሰው በተቃራኒ፣ አንድ ነገር ለማከናወን ያላችሁ ፍላጎትና መነሳሳት ምንም ያህል ብርቱ ቢሆን ያንን ነገር ለማከናወን ችሎታውና አቅሙ ከሌላችሁ ብዙም አያራምዳችሁም፡፡
ምናልባት ፍላጎትና መነሳሳት እያላችሁ ለመስራት ችሎታንና አቅሙን ያጣችሁት . . .

• ከእውቀት ወይም ከክህሎት ጉድለት ከሆነ ያንን ለማስተካከል ማንበብ፣ መማር፣ መሰልጠንና ልምድ ማግኘት አስፋለጊ ነው፡፡

• ከገንዘብ ወይም ከቁሳቁስ እጥረት ከሆነ ያንን ለማስተካከል የገንዘብ አቅማችሁን ለመገንባት መጀመሪያ መስራት፣ ሊደግፋችሁ የሚችልን ሰው መጠየቅና የመሳሰሉትን ነገሮች ማድረግ የግድ ነው፡፡

በዚህ ሳምንት በዚህ ሃሳብ ላይ በሚገባ እንድታስቡበትና እንቅስቃሴ እንድትጀምሩ ላነሳሳችሁ፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence