Get Mystery Box with random crypto!

Free Education Ethiopia ✔️︎

የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎
የሰርጥ አድራሻ: @free_education_ethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 38.83K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Student’s Center
Our groups different grades
@EthioGrade6
@EthioGrade7
@EthioGrade8
@EthioGrade9
@EthioGrade10
@EthioGrade11
@EthioGrade12
Online school bot
@Education_Ethiopia_Bot
📮For paid promotion @Free_Education_Ethiopia_Bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2022-05-03 20:24:08
#መግቢያ_ቀናት

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ።

እስካሁን ባለው የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ያሳወቁ ተቋማት እና የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ/ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2015 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

@Free_Education_Ethiopia 
Stay Safe!

For campus info join @fee_university
5.2K viewsRBST, edited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 20:19:26
#HarmayaUniversity

በ2014 ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በግንቦት 12፣ 13 እና 14 /2014 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

ምንጭ ፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ፅ/ቤት

@Free_Education_Ethiopia 
Stay Safe!

For campus info join @fee_university
4.1K viewsRBST, edited  17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 20:19:26
#ኦዳቡልቱም_ዩኒቨርሲቲ

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 10 እና 11 ይሆናል ተብሏል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-
1. የ8ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ኦርጅናልና ኮፒ ፣ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጅናልና ኮፒ
2. ከ9-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪብት ኦርጅናልና ኮፒ
3. አራት ፓስፖርት ሳይዝ ጉርድ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም
4. አንሶላ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የትራስ ጨርቅ እና ብርድ ልብስ በመያዝ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ በሚገኘዉ ዋናዉ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ።

ምንጭ፦ የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

@Free_Education_Ethiopia 
Stay Safe!

For campus info join @fee_university
3.7K viewsRBST, edited  17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 20:18:54
#DebreTaborUniversity

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና
ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.dtu.edu.et ይመልከቱ።

የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር የቴሌግራም ቻናል ላይ ማለትም t.me/dturegistrar በመግባት የተመደባችሁበትን መኝታ ክፍል (ዶርም) ማየት እንደምትችሉ ተገልጿል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@Free_Education_Ethiopia 
Stay Safe!

For campus info join @fee_university
3.4K viewsRBST, edited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 20:18:33
#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች
ዋናውና ኮፒው
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.bhu.edu.et ይመልከቱ።

ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ብቻ ምዝገባ እንዲያደርጉ ያሳሰበው ዩኒቨርሲቲው፤ ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia 
Stay Safe!

For campus info join @fee_university
3.4K viewsRBST, edited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 20:17:28
#MaddaWalabuUniversity

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ብቻ ምዝገባ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የትምህርት ማስረጃዎች
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ
• የኮቪድ-19 መከላከያዎች

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia 
Stay Safe!

For campus info join @fee_university
4.2K viewsRBST, edited  17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 20:10:30
#HawassaUniversity ጥሪ

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ #በኦንላይን ከግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎች በተቋሙ ድረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑ ተገልጿል፡፡


ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የ12ኛ እና የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት
ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• የሌሊት አልባሳት
• የስፖርት ትጥቅ

ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
6.6K viewsπ, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 14:48:39
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አዲስ በከፈተው CMC ካምፖስ ምዝገባ ጀምሯል።

ለ2014 ዓ.ም ዕውቅና ያገኘባቸው የትምህርት መስኮች፦

- አካውንቲንግ እና ፋይናንስ
- ማኔጅመንት
- ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- ኮምፒውተር ሳይንስ

አድራሻ፦ ከሰሚት አደባባይ ወደ CMC ሚካኤል በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 500 ሜትር አለፍ ብሎ

ለበለጠ መረጃ፦

0116298163/54/55

#Unity_University
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
6.4K viewsπ, 11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 22:01:52
የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.3K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 13:02:17
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ወላጆች እና ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ !

ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 በወረቀት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በቂ የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ወላጆች እና ማህበረሰቡ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡

በጋምቤላ ክልል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናውን በመደበኛ፣ በግል እና በማታ 3653 ያህል ተማሪዎች ይወስዳሉ።

ለፈተናው 17 የፈተና ጣቢያዎች ዝግጁ መሆናቸውን ተገልጿል።

ፈተናውን ለመስጠት ልዩ ልዩ የፈተና ቁሳቁሶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የፈተና ሂደቱን ሊያስተባብሩ የሚችሉ አካላትን የመምረጥ ስራ እንደሚከናወን ክልል አሳውቋል።

የዘገየው የ8ኛ ክፍል ውጤት ጉዳይ ፦

የጋምቤላ ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በሚቀጥሉት ሁለት (2) ሳምንታት ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግም የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመልክቷል፡፡

ቢሮው ለስምንተኛ ክፍል ፈተና ውጤት መዘግየት እርማቱን ለማከናወን ባለሙያዎችን በበቂ ሁኔታ አለማግኘት በምክንያትነት አስቀምጧል።

ከአሁን በፊት ክልላዊ ፈተናው በክረምት ሰዓት ይታረም ስለነበር በወቅቱ ደግሞ በርካታ መምህራንን ማሳተፍ ይቻል እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በ60 መምህራን ብቻ እንዲታረም መደረጉ እንዲዘገይ አድርጎታል ተብሏል።

በቀጣዮቹ 2 ሳምንታት የ8ኛ ክፍል የተማሪዎች ውጤት ይፋ እየተሰራ እንደሚገኝ ቢሮው ያሳወቀ ሲሆን ተማሪና የተማሪ ቤተሰቦች ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ ቀርቧል።

የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት
የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ
አቶ ሙሴ ጋጂት (የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.9K views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ