Get Mystery Box with random crypto!

Free Education Ethiopia ✔️︎

የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎
የሰርጥ አድራሻ: @free_education_ethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 38.83K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Student’s Center
Our groups different grades
@EthioGrade6
@EthioGrade7
@EthioGrade8
@EthioGrade9
@EthioGrade10
@EthioGrade11
@EthioGrade12
Online school bot
@Education_Ethiopia_Bot
📮For paid promotion @Free_Education_Ethiopia_Bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-06-06 12:40:41
#DillaUniversity

በ2014 ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሰኔ 15 እና 16/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በቅጣት ምዝገባ ሰኔ 17/2014 ዓ.ም ብቻ እንደሚከናወን ተገልጿል።

የመመዝገቢያ ካምፓሶች፦

• በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ
ኦዳ ያኣ ግቢ
• በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ
ሀሴ ዴላ ግቢ
• በመምህርነት ሙያ ዘርፋ የተመደባችሁ
በዋናው ግቢ

(ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

via: tikvah university

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
2.8K viewsAyal, 09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 12:37:23
#DebarkUniversity

በ2014 ዓ/ም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሰኔ 8-9 ቀን 2014 ዓ/ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

via: tikvahethiopia

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
2.6K views,,,,, edited  09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 12:17:06
ኢትዮ ቴሌኮም 66 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ትምህርት ማዕከል ፕሮጀክት አስጀምሯል።

ፕሮጀክቱ በአገር ዐቀፍ ደረጃ 66 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን 48 ትምህርት ቤቶች በክልሎች እና 18 ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

Bridging Divide Digital Center የተባለው ፕሮጀክቱ፤ 140 ሺህ 596 ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቶቹ የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸው መሆኑን የገለጹት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ለትምህርት ቤቶቹ የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት እና የትምህርት መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.8K viewsπ, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 15:32:30
A+ Tutorial Class በተማሪዎች ጥያቄ መሰረት 2ኛ ዙር ምዝገባ ጀመረ

A+ Tutorial ለዘንድሮ ፍሬሾች ክስተት ሆኗል! ከ ሁሉም ዮኒቨርስቲዎች የተወጣጡ በሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች የፍሬሽማን ኮርስ ግልፅ በሆነ መንገድ እያስተማረ ሺዎችን ለ Mid Exam ና Final Exam ብቁ እያደረገ እያዘጋጀ ይገኛል።

በአዲሱ ፍኖተ ካርታ መሰረት A+ Tutorial Class የ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ና የ ኮሌጅ ተማሪዎች የሚወስዱትን ፍሬሽማን ኮርስ ልምድ ባካበቱ መምህራን እጅግ ጠቃሚ ቲቶሪያል በመስጠት ብዙ ተማሪዎች በየአመቱ ወደ ሚፈልጉት ዲፓርትመንት እንዲቀላቀሉ እያደረገ ይገኛል።

General Physics, Mathematics, Logic and critical thinking, General Psychology, Social Anthropology እና Emerging Technology ኮርሶችን ጥራቱን በጠበቀ እንግሊዝኛ - አማርኛ ኖት ፣ በድምፅ ( )፣ በምስል (Diagram ) ለSocial እንዲሁም ለNatural Science ተማሪዎች በTelegram ሚስጥራዊ ቻናል እያስተማርን እንገኛለን። እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተመዝግበው ለ Mid Exam በቂ ዝግጅት አድርገዋል።

በተጨማሪም ለተማሪዎች ጥራት ያለው ትምህርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ፣ በዩኒቨርሲቲ ስታንዳርድ የወጡ Mid እና Final Exam'ኦችን በመፈተን ፣ የሲኒየር ተማሪዎችን ልምድ በማካፈል ፣ ላይ ይገኛል።

ከላይ ለናሙና የቀረቡት ፎቶዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በ A+ Tutorial Class እየተሰጡ ያሉት ኮርሶች ሲወስዱ የሚያሳይ ነው።

ለመመዝገብ
@Register_Freshman_2014Bot

ለጥያቄና አስተያይት
@Ucan_Scorebot

ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!
3.0K viewsRBST, 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 22:57:06
#ማስታወሻ

የህንድ መንግስት በ2022/23 ለ55 ኢትዮጵያዊያን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።

በህንድ ባህላዊ ግንኙነት ም/ቤት (ICCR) የቀረበው ነፃ የትምህርት ዕድሉ፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድህረ ዶክትሬት የትምህርት ፕሮግራሞች የተካተቱበት ነው።

በህንድ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት የሚሰጠው ዕድሉ፤ ከክፍያ ነፃ የትምህርት አገልግሎቶች እና ነፃ የአየር በረራ ትኬት ለአሸናፊዎች ያቀርባል።

አመልካቾች ዕድሚያቸው ከ18 እስከ 30 መሆን ያለበት ሲሆን እስከ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች/ተቋማት ማልከት እንደሚችሉም ተገልጿል።

የማመልከቻ ጊዜው ነገ ግንቦት 23/2014 ዓ.ም ያበቃል።

ለማመልከት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦

http://a2ascholarships.iccr.gov.in/home/register


#scholarship
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
1.0K viewsπ, edited  19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 23:53:54
የቴክኒክና ሙያ ምዘናን ወደ ዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚያሸጋግር ስምምነት ተፈረመ።

በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ መካከል ሲደረግ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ምዘናን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሳድጋል የተባለው ፕሮጀክት በሦሥቱ አገሮች ተፈርሞ ጸድቋል።

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሚመረቁ ተማሪዎችና መምህራን በሦሥቱ አገሮች ተንቀሳቅሰው የመስራት ዕድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡

ስምምነቱ በዘርፉ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም ዐቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያላቸው ምሁራንን ለማፍራት ያስችላል መባሉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

የሦሥቱ አገሮችን የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለማሳደግ በዓለም ባንክ የሚደገፍ "የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የክህሎት ሽግግር (EASTRIP)" የተባለ ፕሮጀክት ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት ላይ እንደተገለጸው፤ ሦሥቱ አገሮች የተስማሙበት ወጥ የሆነ የጋራ የምዘና ሥርዓት ሲሠራ ቆይቶ የኬንያ እና ታንዛኒያ ሚኒስትሮች በተገኙበት ስምምነት ሆኖ ጸድቋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ቀጠናዊ የምዘና መስጫ ማዕከል እንደምትሆን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እስካሁን በቴክኒክና ሙያ እስከ ደረጃ ስምንት ሥልጠና ትሰጥ የነበረ ሲሆን ስምምነቱ እስከ 10 እና 11 ደረጃዎች ከሚሰጡ አገሮች ጋር መደረጉ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን ደረጃ እንደሚያሳድገው ሪፖርተር ዘግቧል።

Via ሪፖርተር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
548 viewsπ, 20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 09:29:40
#የኢጋድ_የትምህርት_ብቃት_ማረጋገጫ_ማዕቀፍ

የኢጋድ አባል አገራት የተጣጣመ የትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ መተግበር ሊጀምሩ ነው።

ይህም የአባል አገራቱ ተማሪዎች በየትኛውም የድርጅቱ አባል አገር ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉበትን ሁኔታ ይፈጥራል።

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን (ኢጋድ) የተጣጣመ የትምህርት ብቃት ማዕቀፍ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በኬንያ ተካሂዷል።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አንዱዓለም አድማሴ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል በመድረኩ ተሳትፈዋል።

ሁሉም የኢጋድ አባል አገራት የራሳቸውን የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ የሚያዘጋጁ ሲሆን ድርጅቱ ከሚያዘጋጀው ማዕቀፍ ጋር እንዲጣጣም ይደረጋል።

አባል አገራቱ የየራሳቸው የትምህርት ስርዓት ያላቸው መሆኑ ችግር እንደማይፈጥር ተነስቷል።

የማዕቀፉ መዘጋጀት ከፍተኛ የህዝብ እንቅስቃሴ በሚታይበት የኢጋድ አካባቢ ዜጎች ያለምንም ችግር ለመስራት እና ለመማር ያስችላቸዋል ተብሏል።

ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ በማዕቀፉ የሚካተቱ የኢጋድ አባል አገራት ናቸው። #TheStandard

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
3.0K viewsπ, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 17:12:18
#GambellaUniversity

በ2014 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 29 እና 30/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (6)
• አንሶላ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.gmu.edu.et ይመልከቱ።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
3.2K viewsRBST, 14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 15:24:34
#Fake_News_Alert

በ2015 ዓ.ም የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናገሩ በሚል በማኅበራዊ የትስስር ገጾች የሚዘዋወረው መረጃ #ሐሰት መሆኑን እንገልጻለን።

ቲክቫህ እንደዚህ አይነት ዘገባ አለመስራቱንም ልናረጋግጥ እንወዳለን።

ሀሰተኛ፣ የተዛቡ እና ያልተረጋገጡ መረጃ ከሚያሰራጩ የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ራስዎን ይጠብቁ፡፡


ምንጭ: Tikvah-University
4.3K views,,,,, 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 23:38:42
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የአካዳሚክ ካላንደር ማሻሻያ አድርጓል።

የ8ኛ ክፍል ከተማ ዐቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29/2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 20 እስከ 23/ 2014 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የውጤት ማስረጃ የሚሰጥበት ቀን ሐምሌ 05/2014 ዓ.ም።

(ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።)

#Addis_Ababa_Education_Bureau

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
707 viewsπ, 20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ