Get Mystery Box with random crypto!

Free Education Ethiopia ✔️︎

የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎
የሰርጥ አድራሻ: @free_education_ethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 38.83K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Student’s Center
Our groups different grades
@EthioGrade6
@EthioGrade7
@EthioGrade8
@EthioGrade9
@EthioGrade10
@EthioGrade11
@EthioGrade12
Online school bot
@Education_Ethiopia_Bot
📮For paid promotion @Free_Education_Ethiopia_Bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-08-07 10:47:18
#NationalExam

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
14.7K viewsπ, edited  07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 23:37:14
በመጪው 2015 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የመውጫ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።

በ2015 ዓ.ም መጨረሻ መተግበር በሚጀምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ከሰሞኑን የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ሚኒስትር ዴኤታው ካነሳሷቸው ሃሳቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው

• የመውጫ ፈተና ምዘና የሚሰጠው ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ብቻ ነው።

• በግልም ሆነ በመንግስት የትምህርት ተቋም የሚማር ተማሪ ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ሲያልፍ ብቻ ነው፡፡

• የመውጫ ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበት እና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

• በየዓመቱ ከ150 እስከ 180 ሺህ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ተማሪዎችን ምዘና ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለ፡፡

• የሙያ ማኅበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፤ የመውጫ ፈተና ሥራን ከመንግስት ይረከባሉ።

• ፈተናውን የሚያሰናዱ ተቋማትና መምህራን ዝግጅት ሥራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ፡፡

• የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት ነው።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
11.5K viewsπ, 20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 22:26:48
በክፍል ዉስጥ የነበሩ 85 ተማሪዎችን ከጎርፍ አደጋ መታደጉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ዛሬ ከቀኑ 7፡00 ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታዉ ፊጋ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኘዉ ኒዉ ፖራዳይ መዋለ ህጻናት ትምህርት ቤት በክፍል ዉስጥ የነበሩ እድሜያቸዉ ከ4 እስከ 7 የሆኑ 85 ተማሪዎች ከዋናዉ መንገድ ጥሶ በክፍል ዉስጥ በገባዉ ጎርፍ ተከበው እንደነበር ተገልጿል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ቦታዉ በመገኘት ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ሰማናንያ አምስቱንም ተማሪዎች ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸዉ በጎርፍ ከተያዙበት ክፍል ዉስጥ በሰላም ማዉጣት መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረው ክረምቱ የሚበረታ በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱና ከሚመለከታቸዉ ተቋማት የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
1.7K viewsπ, 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 21:02:08
#AddisAbabaUniversity

የፀጥታ ችግር ካለባቸው ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ መደበኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች የክረምት እረፍት ጊዚያቸውን በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠበቅ ላይ ናቸው።

ቲክቫህ በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ማቲዎስ እንሰርሙ (ዶ/ር) ጠይቋል።

"የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ጥያቂያቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት በማመልከቻ በማቅረብ ምላሽ እንደሚሰጣቸው" ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

"ከተማሪዎች ዲን ጋር በመሆን እያንዳንዱን ጥያቄ ኬዝ በኬዝ በማየት እና አመልካቾቹን ቃለመጠይቅ በማድረግ ምላሽ ይሰጣል" ብለዋል።

በተጨማሪም አካል ጉዳተኛ የሆኑ እና የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎችንም በመለየት ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በግቢው ስለሚቆዩ እና የክረምት ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስለሚገቡ የዶርም እጥረት መኖሩን በመግለጽ የተማሪዎቹ ጥያቄ ኬዝ በኬዝ እንደሚታይ ተናግረዋል።

Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.3K viewsπ, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 20:45:58
Study abroad and make a better version of yourself.

If you've always had this interest of studying or working international then you are in the right place.

(በውጭ አገር ለመማር ወይም ለመስራት ይፈልጋሉ?)

በትክክለኛው ቦታ ላይ ነዎት.

For more info:

@euroscholarships

+251963438324
+1651-291-1122

#advertisement
2.1K viewsπ, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 23:08:33 በአዲስ አበባ በትናንትናዉ እለት ሁለት ታዳጊዎች 9፡00 ሰዓት አካባቢ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስር በተለምዶ " ቀይ አፈር " ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል። ህይወታቸው ያለፈው ታዳጊ ትንሳኤ ጌታቸው እድሜ የ9 ሲሆን ሙባረክ ኸይሪ ደግሞ የ14 ዓመት ታዳጊ ነበር፡፡ ወቅቱ የክረምት ወቅት እንደመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን ሊጠብቁና መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱም ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል።

በዝናብ ወቅት ከቤት ወይም ከት/ቤት ባለመውጣት እንዲሁም ዝናብ ውስጥ ባለመጫወት ራሳችሁን ጠብቁ!

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
1.9K viewsπ, 20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 16:08:46
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም የተመደቡ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎቹን ከረቡዕ ሰኔ 15/2014 ዓ.ም ጀምሮ መቀበል ይጀምራል።

የዩኒቨርሲቲው 'ሀሴዴላ' ግቢ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ተገልጿል።

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መመዝገቢያ ካምፓሶች፦

• በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ
ኦዳያኣ ግቢ
• በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ
ሀሴዴላ ግቢ
• በመምህርነት ሙያ ዘርፋ የተመደባችሁ
በዋናው ግቢ
3.9K viewsRBST, edited  13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 16:54:18 #NEAEA

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ብሄራዊ ፈተና ምዝገባ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2014 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል ብሄራዊ ፈተናውን የምትፈተኑ ተማሪዎች እስከ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን እስካሁን ሳትመዘገቡ ለቀራችሁ ተፈታኝ ተማሪዎች በቀረው ጊዜ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡

በየደረጃው የምትገኙ የትምህርት አመራሮች በተለይም የት/ቤት ር/መምህራን ተፈታኝ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን ጥረት እንድታደርጉ እየጠየቅን፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ችግር አገልግሎቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.9K viewsπ, 13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 21:56:59
የግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የአደረጃጀት ለውጥ በማድረግ ለትርፍ ያልተቋቋመ ትምህርት ቤት ሆኖ እንዲቀጥል ከስምምነት ተደርሷል፡፡

በዛሬው እለት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ( ፕሮፌሰር) የግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት አመራሮችን በቢሯቸው አነጋግረዋል።

ትምህርት ቤቱ ቀድሞ ከተቋቋመለት አላማ ጋር አለመጣጣም በመታየቱ ምክንያት ከተማሪ ወላጆች እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥያቄዎች ሲነሱ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የትምህርት ቤቱን እጣ ፈንታ ለመወሰን የትምህርት ሚኒስቴር ከግሪክ አምባሳደር፣በኢትዮጵያ ከሚገኙ ከግሪክ ማህበረሰብ አባላት ተወካዮች፣ ከግሪክ ትምህርት ቤት አመራሮች እና ከተማሪ ወላጆች ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በተደረገው ውይይትም ትምህርት ቤቱ የግል ትምህርት ቤትነትንና የማህበረሰብ ትምህርት ቤትነትን ባህሪ አጣምሮ በመያዝ መቀጠል እንደማይችል በማሳወቅ አንዱን መርጦ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በየደረጃው ካሉ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ ትምህርት ቤቱ ከግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤትነት ለትርፍ ወደ አልተቋቋመ ትምህርት ቤትነት ለመቀየር ከውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
1.7K viewsπ, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 20:50:51
#Update

የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የጤና ሚኒስቴር ከግንቦት 01 - 04/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ከሰኔ 10/2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራቸውን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋቃ።

በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936/ 0118275337 በመደወል ወይም በኢሜይል hpcald@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄያቸድን ማቅረብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.3K viewsπ, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ