Get Mystery Box with random crypto!

Free Education Ethiopia ✔️︎

የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎
የሰርጥ አድራሻ: @free_education_ethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 39.06K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Student’s Center
Our groups different grades
@EthioGrade6
@EthioGrade7
@EthioGrade8
@EthioGrade9
@EthioGrade10
@EthioGrade11
@EthioGrade12
Online school bot
@Education_Ethiopia_Bot
📮For paid promotion @Free_Education_Ethiopia_Bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-09-16 08:41:19
* ጥንቃቄ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቃረብን ተከትሎ የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ በመሆኑ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል።

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሸጋገረ " እየተባለ በአንዳንድ የማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ የማይታወቅ በትምህርት ሚኒስቴር ሆነ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያልተገለፀ ነው።

ተማሪዎች ከፈተና ጋር በተያያዘ ማንኛውም አዲስ መረጃ ሲኖር በትምህርት ሚኒስቴር / በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚገለፅ መሆኑን በማወቅ በሀሰተኛ መረጃ ሳትረበሹ ተረጋግታችሁ ዝግጅታችሁን ልታደርጉ ይገባል።

የተማሪ ወላጆችም ትክክለኛና የተረጋገጡ መረጃዎች በትክክለኛ የመስሪያ ቤቶቹ አድራሻ እንዲሁም በህዝብ መገናኛ ብዙሃን የሚነገሩት መሆናቸውን በማስገንዘብ ልጆቻችሁ እንዳይረበሹ ልታድርጉ ይገባል።

ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲረበሹ እና ብዙ የለፉበት ዝግጅታቸው እንዲደናቀፍባቸው የሚያደርጉ ሀሰተኛ የፈጠራ ወሬዎችን የምታሰራጩ አካላት ድርጊታችሁ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ፤ በትውልድ ላይም አሉታዊ ተፅእኖ ያለው መሆኑን በማወቅ ከድርጊታችሁ ልትታቀቡ ይገባል።

ተማሪዎች ምንጩ የማይታወቅ እና የተለያዩ አካላት ተከታይ ለማፍራት እንዲሁም ሆን ብለው ተማሪ እንዲረበሽ ለማድረግ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሰራጩትን መረጃ ወደ ጓደኞቻችሁ ባለመላክ ሀሰተኛ መረጃዎችን ተከላከሉ።
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
12.0K viewsπ, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 21:12:51
በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተመሳሳይ፣ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ከኹሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሙከራ ትግበራ ይጀመራል ሲሉ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ሥራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ለሚጀመረው ትምህርት የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ሰኞ ዕለት በይፋ ለሚጀመረው ትምህርት በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ስርዓት እንደሚያካሄድም አመለወርቅ ገልጸዋል።

ተማሪዎች ደስ ብሏቸው የትምህርት ቀኑን እንዲጀምሩ የተለያዩ ዝግጅቶች በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄዱ የገለጹት ኃላፊዋ፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ በክልል ያሉ ትምህርት ቢሮዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ድርጅቶች በትምህርት ቤት ውስጥ መዝናኛ ዝግጅት አዘጋጅተው ተማሪዎችን የመቀበል ሥነ ስርዓት ያካሄዳሉ ብለዋል።

የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ መምህራንን እና ማህበረሰቡ በትምህርቱ የጊዜ ሰሌዳ እና በሥርዓተ ትምህርቱ አፈጻጸም ላይ ውይይቶችን እንዳደረጉ ወ/ሮ አመለወርቅ መጠቆማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን ያወሱት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዋ፣ በዚህም የትምህርት ቤቶች እድሳት፣ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የመጽሐፍት ማስተዋወቅ እና የትምህርት ጉባዔ የማካሄድ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
11.3K viewsπ, 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:50:09
በአዲስ አበባ ከተማ የ2015 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስከረም 3 ቀን 2015 እንዲሁም የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማሩ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ነገር ግን በከተማ ደረጃ ወጥ አድርጎ ማስጀምር በማስፈለጉ ፤ ከመስከረም 2 እስከ 6 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ለአጀማመሩ ሙሉ ዝግጅታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

መስከረም 3 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የ2014 ዓ.ም የ12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች #ማጠናከሪያ_ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

በሁሉም የትምህርት ተቋማት መስከረም 9 ቀን 2015 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ሃደት እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.3K viewsπ, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:11:49   የሚጨመሩና የሚቀነሱ የትምህርት አይነቶች ይኖራሉ በ አዲሱ የሥርዓተ-ትምህርት

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸው ተገለጸ።የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል  ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ እንደገለጹት አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን በከፊል በተወሰኑ በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤቶች ላይ ይተገበራል።

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።በ7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ላይ ከዚህ በፊት ሦስቱ ሳይንሶች ተብለው ይሰጡ የነበሩት (ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባዮሎጂ) አሁን  አጠቃላይ ሳይንስ ተብለው በአንድ ይሰጣሉ ብለዋል።

  በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የኢኮኖሚክስ ትምህርት አሁን ላይ “ፐርፎርም ኤንድ ቪዥዋል አርት” በሚል መተካቱንም ጠቁመዋል።በተመሳሳይ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በድጋሚ ከሚሰጡ የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ ሥራና ቴክኒክ ላይ የሚያተኩሩ የማኑፋክቸሪንግና ኮንስትራክሽን  የትምህርት አይነቶች በየደረጃው ተለይተው መጨመራቸውን ገልጸዋል።
  
   በ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ዩኒፎርሞችና የመማሪያ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን የትምህርት ቤቶችን አካባቢ ከአዋኪ ነገሮች ነፃ ማድረግም ትኩረት ተሰጥቶታል ተብሏል።ለአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ስኬታማነት ከወላጆችና አጠቃላይ ከትምህርት ማኅበረሰቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም ስኬታማነት በትምህርት ቢሮ በኩል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው የገለጹት።በየደረጃው ካሉ የወላጅ ኮሚቴዎች፣ የትምህርት አመራሮችና የግል ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ሰፊ ውይይት ስለመደረጉም አብራርተዋል። አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ መሆኑም ታውቋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
4.7K viewsπ, 06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:43:57
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት እንደሚቻል አስታወቀ።

ቢሮው የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መውጣቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በክልሉ 451 ሺሕ 21 ተማሪዎች ለፈተና የተመዘገቡ ሲሆን 98 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ፈተና መውሰዳቸውን ገልጿል።

በዚህም የ9ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ እና ለሴቶች 47 በመቶ ነው ብሏል።

በአርብቶ አደሩ አካባቢ የ9ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት በመቶኛ ለወንዶች 47% ለሴቶች 44% ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44% እና ለሴቶች 41% መሆኑም ተገልጿል።

ማለፊያው ውጤት በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ እና በትምህርት ጥራት ላይ ተመስርቶ መወሰኑን የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ገልጸዋል::

ሴት ተማሪዎች የተሻለ የፈተና ውጤት በማምጣት ለውጥ አምጥተዋልም ነው ያሉት።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኢንተርኔት ላይ ‘https://oromia.ministry.et/#/home ላይ መመልከት ይችላሉም ነው የተባለው።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.8K viewsπ, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 00:02:15
የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

ለወንዶች 41፣
ለሴቶች 40 እና
ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

ለወንዶች 39፣
ለሴቶች 38 እና
ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

#ENA

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
8.3K viewsπ, 21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 23:59:46
የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
10.4K viewsπ, edited  20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:55:58
“የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” መባሉ ስህተት ነው - ኢትዮጵያ ቼክ

ከ865 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና "Mereja TV" የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ “የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” የሚል መረጃ ማጋራቱን ታይቷል። ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማጣራት የተጋራውን ቡክሌት የመረመረ ሲሆን መረጃው ሀሠተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት “የዘንድሮ” ነው ተብሎ የተጋራውን የታሪክ ፈተና ቡክሌት በ2013/14 ዓ.ም የተሰጠ እንጂ አዲስ አለመሆኑን ተመልክተናል። በተጨማሪም ጉዳዩን በተመለከተ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የተሰራጨውን መረጃ መመልከታቸውን ገልጸው ሀሠተኛ መሆኑንና የተጋራው የፈተና ቡክሌት በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
12.2K viewsπ, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:04:23 #ExitExam

በ2015 የትምህርት ዘመን ከሚጀምረው የመውጫ ፈተና (ለመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ብቻ) ጋር በተያያዘ ከፈተናው በፊት ሊቀድሙ የሚባቸው ነገሮች አሉ በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ።

የግብዓት አቅርቦት ችግር ባለበት ሁኔታ ፣ የትምህርት ተቋማት አቅም በሚፈለገው ደረጃ ባልሆነበት ፣ የመምህራን ብቃት በራሱ ሳይመዘን / መምህራን ሳይመዘኑ ተማሪዎችን መመዘን እንዴት ይሆናል ፤ እንዴትስ ውጤት ያስገኛል በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ላይ ምላሽ አለኝ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) ከተናገሩት ፦

" አቻ ምሳሌ ላይሆን ይችላል ግን አንድ ምሳሌ ላንሳ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አሉ ከሺህ በላይ የሚሆኑ በሁሉም ት/ቤቶች ያለው አቅም ፣ የመምህራን፣ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰረተ ልማት አቅም እና መምህራኑ የተመዘኑ / ምዘናውን ያለፉ መሆን አለመሆናቸው ያለው ምጣኔ በጣም የተለያየ ነው። እንደዛም ሆኖ ግን አንድ ወጥ የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ያስፈልገናል እንደ ሀገር።

የ2ኛ ደረጃ ፈተና የምንሰጠው አንድ ሰው በሁለተኛ ደረጃ የሚሰጠውን ትምህርት በእርግጥ አጠናቋል ለሁለተኛ ደረጃ አጠናቃቂ ነው ተብሎ በቅቷል ወይ ለማለትና ለመለካት ነው።

ይሄ ፈተና ስታንዳርድ ፈተና ነው። በየሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አቅም አይደለም የሚዘጋጀው ፣ በሁለተኛ ደረጃ ያሉ መምህራንን አቅም ብቻ አይደለም ታሳቢ የሚያደርገው፤ እንደ ሀገር ሁለተኛን ደረጀን የጨረሰ ሰው ምን አይነት እውቀት እና ስብዕና ሊኖረው ይገባል የሚለውን የሚፈትሽ ነው።

መምህራኑ ሁሉም ተፈትነው ብቁ ሆነው እስኪያልፉ ፣ ያለን መሰረተ ልማት በትምህርት ቤቶች ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ያለን አቅም ተመጣጣኝ እስክናደርግ ድረስ አንድን ሪፎርም አንጀምርም ካልን ዝንተዓለም ያንን ሪፎርም አናደርግም።

ሪፎርሙ መጀመር አለበት የሆነ ጊዜ ላይ መጀመር አለበት የተባሉ ጉድለቶች እንዳሉ አውቃለሁ፤ እንደ ትምህርት ሴክተርም እንደትምህርት ሚኒስቴርም እንገነዘበዋለን።

የመምህራኖቻችንን ብቃት ለማሳደግ በየአመቱ ከልማት አጋሮችም ፣ ከመንግስትም ግምጃ በሚሊዮኖች እያፈሰስን መምህራን በ2ኛ ፣ 3ኛ ዲግሪ እናስተምራለን።

እንደሚታወቀው መንግስት ለትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት በሀገራችን 4ኛው ትልቁ በጀት የሚመደብለት ሴክተር ነው ሰፊውን የሚወስደው የከፍተኛ ትምህርት ነው የውስጥ መሰረተ ልማታቸውን፣ አደረጃጀታቸውን ለማሳደግ የሚውል ሀብት አለ እነዚህ ቁርጠኝነቶች በመንግስት በኩል የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሚውል ነው።

መምህራኖቻችን በቀጣይነት እያበቃን መሄድ አለብን እርግጥ ነው እንደዛም ሆኖ ግን ይሄ ስራ መጀመር አለበት ፤ አሁን ካልጀመርነው ከበቂ በላይ ጉዳት ደርሷል የትምህርት ጥራቱ ላይ።

በፈተና ብቻ አይደለም ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ በትኩረት በመለየት ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ፣ የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና በጥራት በመስጠት ፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን አነስተኛውን መስፈርት በፖሊሲው መሰረት 50 ፐርሰንት በማድረግ እነኚህ ሪፎርሞች መምህራን ልማት ላይ የምንሰራውን ፤ የዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያን ገድበን የወሰድናቸውን ሪፎርሞች ድምር ውጤት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው ፤ ይሄንን ማድረግ ተገቢ ነው ጊዜው አሁን ነው ብለን ነው የገባንበት። "
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
11.1K viewsπ, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:29:03 በአዲስ አበባ ትምህርት መስከረም 9 ይጀምራል

በ2015 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሆኖ ይሰጣል ተባለ

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሀገር አቀፍ ሆኖ ይሰጣል።

የ2015 ዓመት መደበኛ የትምህርት ዘመን መስከረም 9 ቀን እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በ2015 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ተናግረዋል።
በአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ላይ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ በ2014 የትምህርት ዘመን ላይ የተከናወነ ሲሆን አዲሱ ስረዓተ ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ በሁሉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ተግበራዊ ይሆናል።

በሌላ በኩል በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በከፊል በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 የትምህርት ዘመን የሙከራ ትግበራ ከተከናወነ በኃላ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ ይደረገል።

በ2015 ዓመት የትምህርት ዘመን 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፣የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እንዲሁም 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል ፡፡በ2015 የትምህርት ዘመን ላይ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲተገበር በተለይ የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ እና ከዚህ ቀደም በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም በጋራ መሰራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የመጽሀፍ ስርጭትን በተመለከተ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በተማሪዎች እጅ እንዲደርስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ አበበ ቸርነት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
11.6K viewsπ, edited  17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ