Get Mystery Box with random crypto!

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ | Free Education Ethiopia ✔️︎

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!