Get Mystery Box with random crypto!

“የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” መባሉ ስህተት ነው - ኢትዮጵያ | Free Education Ethiopia ✔️︎

“የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” መባሉ ስህተት ነው - ኢትዮጵያ ቼክ

ከ865 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና "Mereja TV" የሚል ስያሜ ያለው የፌስቡክ ገጽ “የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” የሚል መረጃ ማጋራቱን ታይቷል። ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማጣራት የተጋራውን ቡክሌት የመረመረ ሲሆን መረጃው ሀሠተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት “የዘንድሮ” ነው ተብሎ የተጋራውን የታሪክ ፈተና ቡክሌት በ2013/14 ዓ.ም የተሰጠ እንጂ አዲስ አለመሆኑን ተመልክተናል። በተጨማሪም ጉዳዩን በተመለከተ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የተሰራጨውን መረጃ መመልከታቸውን ገልጸው ሀሠተኛ መሆኑንና የተጋራው የፈተና ቡክሌት በ2013/14 (2021) ዓ.ም የተሰጠ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!