2022-09-21 09:55:11
ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦች ለተለያዩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለወሰዱ ጥያቄዎች መልስ
ስልክ ይፈቀዳል ወይ
በጭራሽ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክ አይፈቀድም ።
በመሆኑም ስልክ ቀርቶ በመፈተኛ ክላስ እስክርቢቶ አይፈቀድ የሚፈቀደው እርሳስ ብቻ ነው ምክንያቱም አንሰር ሽቱ ላይ የ እስክርቢቶ ሰረዝ ከተገኘ ማሽኑ ላያርመው ስለሚችል
በተመሳሳይ ሌሎች ህጎችን ተላልፎ ህግ ከጣሰ ቀላል እና ከባድ በሚባል የቅጣት መስፈርት የሚቀጣ ይሆናል።
የጥፋት አይነቱ ከ አንሰር ሽታችሁ ጋር በ ዲሲፕሊን ፎርም ተያይዞ የሚላክ ይሆናል።
ቀላል ሲያጠፋ የተገኘበትን ሳብጀክት ብቻ የሚያሰርዝ ሲሆን
ከባድ ሁሉነም እስከ ማሰረዝ ይደርሳል
ካልኩሌተር ይያዛል ወይ
ከ አእምሮ እገዛ ውጪ የምንም መሳሪያ እገዛ ማግኘት አይፈቀድም በጣም ክልክል ነው ።
በመሆኑም ማንኛውም አጋዥ ማሽን ነገር አይፈቀድም
ሰአት መያዝ ይቻላል ወይ
ለሰአት መቁጠሪያ ብቻ የሚያገለግል ሰአት ብቻ ከሆነ እንጂ ማንኛውም ዘመናዊ ሰአት ( ፎቶ የሚያነሳ ስልክ የሚደውል ወዘተ....) አይፈቀድም
ቻሉት እንግዲህ በተመሳሳይ ከ 30 ደቂቃ በላይ አርፍዶ መፈተን አይቻልም።
የስም፣ የፆታ ፣የስትሪም ስህተት ቢኖርስ
id card በምትቀበሉበት ሰአት የተሳሳተ የመሙያ ፎርም በ ርዕሰ መምህር እና ሱፐርቫይዘር አማካኝነት በመሙላት
ማስተካከያ ደብዳቤ ማፃፍ ይገባቸዋል ችላ አይባልም ።
የ 2013 ተፈታኞች ድጋሚ የሚፈተኑት ውጤቱ አንደ አማራጭ ነወይ የሚያዘው
እስካሁን ከ ት/ሚ የመጣ ነገር ባይኖርም የሚያዘው የ ዘንድሮ ፈተናቸው መሆኑን እና አንዳንድ አሳሳች መልክት የሚያስተላልፉትን ከመስማት በመቆጠብ የአሁኑን ጥሩ እንዲሰሩ ምክንያቱም የበለጠው ይያዝ ቢባል እንኳ የአሁኑ ስለሚያዝ የ አሁኑን ጥሩ ለመስራት ሞክሩ።
ከገቡ ቡኋላ መውጣት አይቻልም የ ሀይማኖት ተቋም መሄድ የምንፈልግስ
እንደ ኢትዮጵያ የመጣውን በጋራ መቀበል ነው ።
አንድም ተማሪ ወደ ግቢ ከገባ ቡሃላ በምንም ምክንያት ያለግቢው ፍቃድ አይወጣ፣ አይገባም። ለምሳሌ ህመም ምንምን እንደ ድንገት ብያጋጥማችሁ እዛው ውስጥ ባለው ክሊኒክ #በነፃ መታከም ነው።
በራስ ወጪ ቀድሞ መጓጓዝ የሚፈልግ ይፈቀዳል ወይ
አይቻልም ከ ት/ቤት ለ ዩንቨርስቲ ማስረከብ ያለበት የወረዳው አመራር ስለሆነ የተማሪውን ብዛት ከ ትራንስፖርት ተቋም ጋር በመነጋገር ያዘጋጃሉ
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
8.2K viewsRBST, 06:55