Get Mystery Box with random crypto!

የ ዘንድሮ የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምኑ ለየት ያረገዋል ? የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎ | Free Education Ethiopia ✔️︎

የ ዘንድሮ የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምኑ ለየት ያረገዋል ?


የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፈተናውን ሊያሰሩ አይችልም!

የግል ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤታቸውን ስም ለማስጠራት ሲሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ እንዲሰሩ ተጨማሪ መልስም እንዲሰጣቸው ሲደረግ ሰንብቷል! እስካሁን ድረስ ግቢ ላይ የተዋወኳቸው የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ያረጋገጡልኝ ያንን ነው!  ዘንድሮ ማን ሰርቶ ይሰጣቸው ይሆን ማንም! በደምብ ያላጠና የሃብታም ልጅ ከሰረ

ተማሪዎች ስልክ ይዘው አይገቡ ፤ ከግቢ መውጣት አይችሉ ፣ ጉዳዩ ተዘጋ!

የአምናውን ፈተና ብቻ ለማስታወስ ስንሞክር ፈተናውን ከመፈተናቸው በፊት የፈተናው ሙሉ ጥያቄ በ Pdf ፋይል ለግቢ ተማሪዎች ሲላክ እንደነበር አይዘነጋም! የግቢ ተማሪዎች ጥያቄውን  ለዘመድ አዝማድ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እየሰሩ ሲልኩም ነበር!ዘንድሮ ማንም ለማንም አይልክም ፣ ስልክ የለማ! ፤ ውጪ እንኳን ሲወጡ ይሰጣቸዋል እንዳይባል ፤ ማንም ተማሪ ከግቢ ውጪ ዝር ማለት አይችልም! ሰው ይሰራልኛል ፤ የግቢ ተማሪ ሰርቶ ይልክልኛል ብሎ ሲያስብ የነበረ ተማሪ ከሰረ !

ፈተኞችን በሬ እያረዱ የሚያበሉ ፣ የገጠር ትምህርት ቤቶች ከሰሩ!

ከዚህ በፊት በነበሩ ፈተናዎች ላይ selfie እየተነሱ የሚልኩ ተማሪዎች ነበሩ! ኸረ ፈተናው ላይ የሚሳሳሙ ጥንዶች እራሱ ሳይኖሩ አይቀሩም!ምንንም ቁጥጥር የለም እኮ በቃ ገበያ ነው!ይህ ለምንድነው ብለን ስንጠይቅ ለካ ፈታኞቹ በሬ እየታረደላቸው ፤ ጠጅ እያጠጧቸው ነው! የትምህርት ቤት ዳይሬክተር እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉላቸው ስለሚፈልጉ ፤ ደግሰው ፈተኞቹን ያበሏቸዋል! ፈታኞቹ ጮማቸውን ወጥቀው ወጥቀው ሲደክማቸው እንቅልፋቸውን ሊተኙ ሁላ ይችላሉ ፣ መፈተኛ ክፍል ውስጥ! ኸረ እንደውም አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ሰልፍ ላይ ለፈታኛችሁ ድግስ ስለምንደግስ ሁለት መቶ ሁለት መቶ አዋታችሁ በአለቆቻችሁ በኩል ቢሮ እንድትልኩ ፤ በደምብ ተክራርጃችሁ እንድትሰሩ የሚባሉ እራሱ አሉ በድግስ ለማለፍ ያቀደ የገጠር ተማሪ ጉዱ ፈላ!


ፈተናው ከ በፊቱ ኮድ ነው የበለጠ ነው የሚሆነው ፣ ጎበዝ ተማሪዎች አረፉ!

ከዚህ በፊት በነበሩ ፈተናዎች ላይ ጎበዝ ተማሪ እየተደበደበ መልስ እንዲሰጥ ይደረግ ነበር ፤ ኸረ ሽት የሚነጥቁ ተማሪዎች እራሱ ተማሩ! ዘንድሮ ግን በ 12/8 ኮድ ሲሆን ፣ ሰነፍ ተማሪ ምን ይዋጠው! ፈተናው ሊቀራረብበት የሚችልበት እድል የሞተ ነው! በጉልበቱ የሚመካ ሰነፍ ተማሪ ከዛ አይኑ ፋጥጥ ጥርሱ ግጥጥ ....ቀለም ተማሪዎች መልሱን ግልብጥ

የዘንድሮ ፈተና እጅግ ልዩ ከመሆኑም በላይ ፤ ጎበዝ ተማሪዎች ብቻ የሚያልፉበት ነው! አይኑን እያቃጠለ ያነበበ የደሃ ልጅ ፤ እምባው በውጤቱ ይታበሳል ፤ አቅሙን በሙሉ አሟጦ የተጠቀመ የሃብታም ልጅ እንዲሁ በውጤቱ ይኮራል ፤ የሰራ እና የሰራ ብቻ መልካሙን ፍሬ የሚበላበት ፈተና ይሆናል! ዘንድሮ ውጤት የሚቀርበት ተማሪ በምንም ምክንያት ሊያማሃኝ አይችልም ፣ ሙሉ ሃላፊነቱን እራሱ ይወስዳል! የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ ማለት አይሰራም
Via QesemAcademy

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!