ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦች ለተለያዩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለወሰዱ ጥያቄዎች መልስ ስልክ ይፈቀዳል ወይ በጭራሽ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክ አይፈቀድም ። በመሆኑም ስልክ ቀርቶ በመፈተኛ ክላስ እስክርቢቶ አይፈቀድ የሚፈቀደው እርሳስ ብቻ ነው ምክንያቱም አንሰር ሽቱ ላይ የ እስክርቢቶ ሰረዝ ከተገኘ ማሽኑ ላያርመው ስለሚችል በተመሳሳይ ሌሎች ህጎችን ተላልፎ ህግ ከጣሰ ቀላል እና ከባድ በሚባል የቅጣት መስፈርት የሚቀጣ ይሆናል። የጥፋት አይነቱ ከ አንሰር ሽታችሁ ጋር በ ዲሲፕሊን ፎርም ተያይዞ የሚላክ ይሆናል። ቀላል ሲያጠፋ የተገኘበትን ሳብጀክት ብቻ የሚያሰርዝ ሲሆን ከባድ ሁሉነም እስከ ማሰረዝ ይደርሳል ካልኩሌተር ይያዛል ወይ ከ አእምሮ እገዛ ውጪ የምንም መሳሪያ እገዛ ማግኘት አይፈቀድም በጣም ክልክል ነው ። በመሆኑም ማንኛውም አጋዥ ማሽን ነገር አይፈቀድም ሰአት መያዝ ይቻላል ወይ ለሰአት መቁጠሪያ ብቻ የሚያገለግል ሰአት ብቻ ከሆነ እንጂ ማንኛውም ዘመናዊ ሰአት ( ፎቶ የሚያነሳ ስልክ የሚደውል ወዘተ....) አይፈቀድም ቻሉት እንግዲህ በተመሳሳይ ከ 30 ደቂቃ በላይ አርፍዶ መፈተን አይቻልም። የስም፣ የፆታ ፣የስትሪም ስህተት ቢኖርስ id card በምትቀበሉበት ሰአት የተሳሳተ የመሙያ ፎርም በ ርዕሰ መምህር እና ሱፐርቫይዘር አማካኝነት በመሙላት ማስተካከያ ደብዳቤ ማፃፍ ይገባቸዋል ችላ አይባልም ። የ 2013 ተፈታኞች ድጋሚ የሚፈተኑት ውጤቱ አንደ አማራጭ ነወይ የሚያዘው እስካሁን ከ ት/ሚ የመጣ ነገር ባይኖርም የሚያዘው የ ዘንድሮ ፈተናቸው መሆኑን እና አንዳንድ አሳሳች መልክት የሚያስተላልፉትን ከመስማት በመቆጠብ የአሁኑን ጥሩ እንዲሰሩ ምክንያቱም የበለጠው ይያዝ ቢባል እንኳ የአሁኑ ስለሚያዝ የ አሁኑን ጥሩ ለመስራት ሞክሩ። ከገቡ ቡኋላ መውጣት አይቻልም የ ሀይማኖት ተቋም መሄድ የምንፈልግስ እንደ ኢትዮጵያ የመጣውን በጋራ መቀበል ነው ። አንድም ተማሪ ወደ ግቢ ከገባ ቡሃላ በምንም ምክንያት ያለግቢው ፍቃድ አይወጣ፣ አይገባም። ለምሳሌ ህመም ምንምን እንደ ድንገት ብያጋጥማችሁ እዛው ውስጥ ባለው ክሊኒክ #በነፃ መታከም ነው። በራስ ወጪ ቀድሞ መጓጓዝ የሚፈልግ ይፈቀዳል ወይ አይቻልም ከ ት/ቤት ለ ዩንቨርስቲ ማስረከብ ያለበት የወረዳው አመራር ስለሆነ የተማሪውን ብዛት ከ ትራንስፖርት ተቋም ጋር በመነጋገር ያዘጋጃሉ @Free_Education_Ethiopia Stay Safe 8.2K viewsRBST, 06:55