Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹ኢትዮ University

የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversity1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 126.74K
የሰርጥ መግለጫ

Promotion ለምትፈልጉ ....🌀 @Euads🌀
@hilwauniversity
Use this for idea and question @ethiouniversity1bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-11 19:17:14
#Update

የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡

መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች፤ ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

የአዲስ አበባ እና ሌሎች የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን የሚወስዱትን ስም ዝርዝራቸው በዚህ ቻናል ላይ ጠብቁን።
https://t.me/+jBtxz2wYv4g0ZTlk

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.6K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-11 19:16:34



በጥያቄችሁ መሰረት እነሆ

- የExitExamAI አጠቃቀም ሙሉ ቪዲዮ ተለቋል!
የመውጫ ፈተናን በAI በመታገዝ በውጤት እናሸብርቅ!

You asked and here it is

- ExitExamAI Full Video Tutorial Released!
- A step by step video guide for you to master ExitExam with tailored AI Models.

Ace your Exit Exam with AI brilliance

Website: ExitExamAI
Telegram: @ExitExamAI
13.2K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-10 19:05:19
በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘና ተሰጠ፡፡

የሙያ ብቃት የጽሁፍ ምዘናው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 18,591 መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በ15 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

ምዘናው በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች በ36 የትምህርት አይነቶች የተሰጠ ሲሆን፤ በምዘና ሒደቱ ከአንድ ሺህ በላይ ፈታኞች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና አስተባባሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

የመምህራኑን ፍቃደኝነት መሰረት በማድረግ የተሰጠው የጽሁፍ ምዘናው፤ የመምህራንን የሙያ ብቃት በማሳደግ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የጽሁፍ ምዘናው ከ80 በመቶ የሚያዝና ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የማህደረ ተግባር ምዘናን መሰረት እንደሚያደርግ ምዘናውን በጋራ የሰጡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ገልፀዋል፡፡

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
15.5K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 19:41:45
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክፍት የሥራ ቦታዎች ላይ ለማመልከት የሚረዳ የሥራ ማመልከቻ ድረ-ገፅ ይፋ አድርጓል።

ባንኩ የድረ-ገፁን አጠቃቀም አስመልክቶ የአጠቃቀም መመሪያ ያወጣ ሲሆን አመልካቾች በመጀመሪያ ስማቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ የኢሜይል አድራሻቸውን በማስገባት መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ከተመዘገቡ በኋላ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎች ሲኖሩ በድረገፁ ላይ የተመዘገቡበትን የስልክ ወይም ኢሜይል አድራሻ እና አመልካቾች ለዚሁ አላማ በመመዝገቢያ ቅፁ ላይ ያስገቡትን የግላቸውን የይለፍ ቃል (Password) በማስገባት ስራዎችን መከታተልና ማመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የስራ መከታተያ ድረገፁ https://vacancy.cbe.com.et

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.1K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 19:20:30
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃ እና በድኅረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም ለሚገቡ ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት መዘጋጀቱን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ጀሉ ዑመር (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው ከመጪው መስከረም ጀምሮ መሰጠት የሚጀመር ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚከናወን ም/ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው በሁሉም ዘርፎች ይሰጣል የተባለ ሲሆን ፕሮግራሙ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል፡፡

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ በሥራ ገበያ ያሉ ሰራተኞች እና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ፕሮፌሽናል ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል። #ENA

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
14.7K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 13:25:23
#ExitExam
#Re_Exam
#UnityUniversity

ድጋሚ የመውጫ ፈተና ሰኔ ላይ ለምትወስዱ
(June 2016 Re-Exit Exam)

1. 2015 ዓ.ም ለመፈተን ተመዝግባችሁ "Username"  ወስዳችሁ፣ ፈተናውን ያልወሰዳችሁ እና በቀጣዩ ሰኔ ላይ መውሰድ የምትፈልጉ ተማሪዎች፣ በአካል እስከ አርብ ድረስ ቢሮ ቁጥር 02 ማመልከት ይኖርባችኋል።

2. በ2016 የካቲት ላይ "username" ወስዳችሁ ያልተፈተናችሁ ቀጥታ መመዝገብ ስለምትችሉ ቢሮ መምጣት አይጠበቅባችሁም።

3. ፈተናውን በድጋሚ የምትወስዱ ተማሪዎች፣ ምዝገባና ክፍያ በራሳችሁ ሲሆን፣ ቀኑን እንዳሳወቁን እናሳውቃለን።

4. ክፍያ የሚከፈለው በቀጥታ በቴሌብር ለትምህርት ሚኒስቴር ነው።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
15.4K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 12:14:23
በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ከነገ ጀምሮ ይሰጣል።

የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ እንደሚሰጡት ተገልጿል።

ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,591 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ከነገ ሐሙስ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ይጀምራል ተብሏል።

ተመዛኞች ስልክና የትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ይዘው ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት አይችሉም።

ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ በመያዝ ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት (2:30) አንድ ሰዓት ቀደም ብለው በምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.7K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 12:13:36 ለ 1ኛ አመት ተማሪዎች በ 2ኛ ሴሚስተር ቲቶሪያል የምንሰጣቸው ኮርሶች

የ ሁለተኛ ሴሚስቴር ምዝገባ ተጀምሯል።

የ 2ኛ ሴሚስተር #Common_Course ትቶሪያላችን መማር ለምትፈልጉ ምዝገባው ተጀምሯል።

ሁለተኛ ሴሚስተር 
Economics,
Emerging Technology,
Communictive English 2,
anthropology,
Civics,
Global,
C++ እና 
Applied Maths 1,

በነዚህ Coursoች ላይ ትቶሪያሎች እየተዘጋጁ ስለሆነ መማር የምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ።

የክፍያ ሁኔታ
  3ት ኮርስ መርጠው ለሚማሩ 100 ብር ብቻ
  4ት ኮርስ እና ከዛ በላይ 150 ብር ብቻ ከፍላችሁ መማር ነው።

ለመመዝገብ @Ethiounads ላይ ከፍላችሁ መቀላቀል ነው።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.4K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 19:20:51 ትምህርት ሚኒስቴር ለስድስት ተጨማሪ የምርምር ጆርናሎችን እውቅና ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ በ2012 ዓ.ም ለሦስት ዓመት የሚቆይ እውቅና የተሰጣቸው ጆርናሎችን እንዲሁም ሌሎች ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና ለማግኘት ያመለከቱ በድምሩ 35 የአገር ውስጥ ጆርናሎች ላይ ፍተሻ ሲያካሒድ መቆየቱን አስታውሷል።

በዚህም በ2012 ዓ.ም እውቅና አግኝተው ከነበሩ ጆርናሎች መካከል አስራ አንድ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015 ዓ.ም ካመለከቱ ጆርናሎች መካከል ስድስት (ከታች ከቁጥር 12-17 የተገለፁት) በድምሩ አስራ ሰባት የምርምር ጆርናሎች መስፈርት ማሟላታቸው ተገልጿል።

ለጆርናሎቹ የተሰጠው እውቅና ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ዓመት የሚቆይ ነው ተብሏል።

1. Bahir Dar Joumal of Education
2. East African Journal of Sciences
3. East African Journal of Social Sciences and Humanities
4. Ethiopian Journal of Agriculture Sciences
5. Ethiopian Journal of Education
6. Ethiopian Journal of Social Sciences and Language Studies
7. Ethiopian Journal of the Social Sciences and Humanities
8. Haramaya Law Review
9. Jimma University Law Journal
10. Journal of Ethiopian Studies
11. Oromia Law Journal
12. Ethiopian Association of Civil Engineers Journal
13. Ethiopian Journal of Business and Economics
14. Ethiopian Journal of Business Management and Economics
15. Ethiopian Journal of Development Research
16. Ethiopian Journal of Higher Education
17. Journal of Indigenous Knowledge and Development Studies

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.1K viewsedited  16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-06 19:01:37
መምህራኑ ላለፉት 2 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም አሉ።

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ፣ ላለፉት 2 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ መምህራን የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ።

መምህራኑ በቁጥር ከ1 ሺሕ በላይ ይሆናሉ።

በወረዳው በሚገኙ 52 የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩት እኚህ መምህራን ፤ ኑሯቸውን የሚገፉት በወርሃዊ ደመወዛቸው ብቻ በመሆኑ ፣ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ ልጆቻቸው የሚላክ ገንዘብን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እንደተሳናቸው ገልጸዋል፡፡

የቆንጂ ቆለላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ጌታቸው ደገፋው ችግሩ መሆኑን አምነዋል።

በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር የሒሳብ ሠራተኞች ወደ ቢሮ ገብተው ለመሥራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት፣ ከመምህራን ማኅበር ጋራ በመነጋገር አዲስ ሠራተኞች ተመድበው ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። #ቪኦኤ

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
15.8K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ